መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

1ኛ ዜና 10

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከዚህ በኋላ ፍልስጥኤማውያን ራኤላውያንም ከፊታቸ ሸሹ፤ብዙዎች በጊቦልቦን ተራራ ላይ ሞቱ።
2ፍልስጥኤማውያን ሳኦልንና ልጆቹን ይበልጥ አሳደዱአቸው የሳኦልም ልጆች ዮናታን፣አሚናዳብንና ሜልካሳን ገደሉ፤
3ሳኦል በተሰለፈበት ግንባር ውጊያው በረታ፤ቀስተኞችም አግኝተው አቁሰሉት።
4ሳኦል ጋሻ ጃግሬውን፣"እነዚህ ሸለፈታምፕች መሳለቂያ እንዳያደርጉኝ ሰልፍህን መዝዘህ ውጋኝ"አለው።ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ሰለ ነበር አልደፍርም፤ስለዚህ ሳኦል በገዛ ሰይፉ ላይ ወድቆ ሞተ።
5ጋሻ ጃግሬውም ሳኦል መሞቱን ሲያይ፤እርሱም በሰይፉ ላይ ወድቆ ሞተ።
6ስለዚህ ሳዖልና ሦስት ልጆቹ ሞቱ፤ቤተ ሰዎቹም ሁሉ አብረው ሞቱ።
7በሸለቆው ውስጥ የነበሩት እስራኤላዊያን ሁሉ ሰራዊቱ እንደ ሸሽ፣ሳኢልና ልጆቹም እንደ ሞቱ ባዩ ጊዜ ከተሞቻቸውን ለቀው ሸሹ፤ፍልስጥኤማውያንመጥተው ከተሞቹን ያዙ።
8በማግሥቱ ፍልስጥኤማውያን የሞቱትን ለመግፈፍ ሲመጡ፣ሳኦልና ልጆቹ በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወድቀው አገኙአቸው።
9ሳኦልን ከገፈፉ፣ረሱን ከቁረጡና መሣሪያውንም ከወሰዱ በኋላ፣ለአማልክቶቻቸውና ለሕዝቡ የምሥራቹን እንዲነግሩ ወደ መላው የፍልስጥኤም ምድር መልክዕተኞች ላኩ።
10ከዚህም መሣሪያውን በአማልክቶቻቸው ቤተ ጣዖት አኖሩ፤ራሱንም በዳጎን ቤተ ጣዖት ውስጥ አንጠለጠሉት።
11የኢያቢስ ገለዓድ ነዋሪዎች ሁሉ ፍልስጥኤማውያን በሳኦል ላይ ያደረጉትን በሰሙ ጊዜ፤
12ብርቱ የሆኑ ሰዎች ሄደው የሳኦልንና የልጆቹን ሬሳ አንሥተው ወደ ኢያቢስ አመጡ፤ዐጽማቸውንም ኢያቢስ ውስጥ በሚገኘው ትልቁ ዛፍ ሥር ቀበሩ፤ከዚህያም ሰባት ቀን ጾሙ።
13ሳኦል እግዚአብሔር ስላታዘዘ ሞተ፤የእግዚአብሔር ቃል አልጠበቀም፤ይልቁንም ከሙታን ጠሪ ምክርን ጠየቀ፤
14ይህን ከእግዚአብሔር አልጠየቀም፤ስስለዚህ እግዚአብሔር ገደለው፤መንግሥቱንም ወደ እሴይ ልጅ ወደ ዳዊት እንዲተላለፍ አደረገ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።