መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

1ኛ ዜና 9

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እስራኤል ሁሉ በየትውልድ ሐረጋቸው ተቁጥረው ስማቸው በእስራኤል ነገሥታት መዝገብ ላይ ሰፈረ።የይሁዳ ሕዝብ ከፈፀሙት በደል የተነሣ ተማርከው ወደ ባቢሎን ተወሰዱ።
2በመጀመሪያ በየርስታቸውና በየከተሞቻቸው ተመልሰው የሰፈሩት ጥቂት እስራኤላውያን፣ካህናት፣ሌዋውያንና ቤተመቅደሱ ውስጥ የጉልበት ሥራ የሚሠሩ አገልጋዮች ነበሩ።
3በእየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩ የይሁዳ፣የብንያም፣የኤፍሬምና ምናሴ ነገዶች የሚከተሉት ናቸው፤
4ከሰፋሪዎችም መካከል ይሁዳ ልጅ፣ከፋሬስ ዘሮች፣የባኒ ልጅ፣የአምሪ ልጅ፣የዖምሪ ልጅ፣የዓሚሁድ ልጅ ዑታይ።
5ከሴሎናውያን፦የበኩር ልጁ ዓሣያና ወንዶች ልጆቹ።
6ከዛራውያን ዝርያዎች መካከል ይዑኤል፤ የሕዝቡ ቁጥር 690 ነበረ።
7ከብንያማዊን፦የሐስኑኤ ልጅ፣የሆዳይዋ ልጅ፣የሜሱላ ልጅ ስሉ።
8የይሮሐም ልጅ ብኔያ፣የሚክሪ ልጅ፣የኦዚ ልጅ ኤላ፣የይብንያ ልጅ፣የራጉኤል ልጅ፣የሰፋ ጥያ ልጅ ሜሱላም።
9በትውልድ ሐረግ መዝገቡ ላይ በተጻፈው መሠረት ከብንያም ነገድ የሕዝቡ ቁጥር ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ስድስት ነበረ፤እነዚህ ሁሉ ወንዶች የቤተሰብ አለቆች ነበሩ።
10ከካህናቱ፦ ዮዳኤ፣ዮአሪብ፣ያኪን፣
11የእግዚአብሔር ቤት አለቃ የሆነው የአኪጦብ ልጅ፣የጳስኮር ልጅ፣የይሮሐም ልጅ፣የሜሱላም ልጅ፣የኬልቅያስ ልጅ ዓዛርያስ።
12የመልክያ ልጅ፣የጳስኮር ልጅ፣የሳዶቅ ልጅ፣ዓዳያ፣የኢሜር ልጅ፣የምሺላሚት ልጅ፣የሜሴላም ልጅ፣የየሕዜራ ልጅ፣የዓዲኤል ልጅ መዕሣይ።
13የቤተሰብ አለቃ የነበሩ ካህናት ቁጥር አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሥልሳ ነበረ፤እነዚህም በእግዚአብሔር ብት ለሚከናወነው አገልግሎት ብቁ ሰዎች ነበሩ።
14ከሌዋውያን ወገን፦ ከሜራሪ ዘሮች የአሳብያ ልጅ፣የዓዝሪቃም ልጅ፣የአሱብ ልጅ፣ሽማያ፣
15በቅበቃር፣ኤሬስ፣ጋላልና የአሳፍ ልጅ የዝክሪ፣የሚካ ልጅ፣መታንያ።
16የኤዶም ልጅ፣የጋላል ልጅ፣ይችሰሙስ ልጅ፣አብድያ።እንዲሁም በነጦፋውያን ከተሞች የኖረው የሕልቅና ልጅ፣የአሳ ልጅ በራክያ።
17የቤተ መቅደስ በር ጠባቂዎች፦ሰሎም፣ዓቁብ፣ጡልሞን፣አሂማንና ወንድሞቻቸው፣አለቃቸው ሰሎም ነበረ፤
18እነርሱም በስተ ምስራቅ በሚገኝው በንጉስ በር እካሁን ድረስ ተመድቦአል።እነዚህ የሌዋያኑ ሰፈር በር ጠባቂዎች ነበሩ።
19የቆሬ የአብያሳፍ ልጅ፣የቆሬ ልጅ ሰሎምና ክእነሱም ቤተሰብ የሆኑት ቆሬያውያን ወደ እግዚአብሔር ማደሪያ የሚያስገባውን በር ይጠብቁ እንደ ነበር ሁሉ፣እነዚህም ወደ ቤተ መቅደሱ የሚያስገባውን በር ይጠብቁ ነበር።
20በቀድሞ ጊዜ የበር ጠባቂዎቹ አለቃ የአላዓዛር ልጅ ፊንሐስ ነበረ፥እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረ።
21ወደ መገኛው ድንኳን የምያስገባው በር የሚጠብቀው ደግሞ የሜሱላም ልጅ ዘካሪያስ ነበረ።
22መግቢያ በሮቹን እንዲጠብቁ የተመረጡ ባጠቃላይ ሁለት መቶ ዐሥራ ሁለት ነበሩ።እነርሱም በትውልድ ሐረጋቸው መሠረት በሚኖሩባቸው መንደሮች ተቁጥረው ተመዘገቡ፤በር ጠባቂዎቹን በዚያ ቦታ ላይ የመደቡላቸው ዳዊትና ባለ ራእዩ ሳሙኤል ነበሩ።
23የማደሪያውን ድንኳን ምማለትም የእግዚአብሔርን ቤት የሚጠብቁትንም እነርሱና ዘሮቻቸው ነበሩ።
24በር ጠባቂዎቹም በምሥራቅ፣በምዕራብ፣በሰሜንና፣በደቡብ በሚገኙት በአራቱም ማዕዘኖች ላይ ነበሩ።
25ወንድሞቻቸውም በየመንደሮቻቸው ሆነው በየጊዜው እየወጡ የጥበቃውን ሥራ ሰባት ሰባት ቀን ያግዙአቸው ነበር።
26ሌዋውያን የነበሩት አራቱ የበር ጠባቂ አለቆች ግን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የሚገኙትን ክፍሎችና ግምጃ ቤቶች በኃላፊነት ይጠብቁ ነበር።
27የጥበቃውን ሥራ የሚያከናውኑት እነርሱ በመሆናቸው የሚያድሩትም በዚያው በእግዚአብሔር ቤት አካባቢ ነበረ፤ጠዋት ጠዋትም ደጆቹን የሚከፋፍቱት እነርሱ ነበሩ።
28ከእነርሱም አንዳንዶቹ ለብቤተመቅደሱ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በኃላፊነት ይጠብቁ ነበር፤ዕቃዎቹም በሚገቡበትና በሚወቱበት ጊዜ ሁሉ ይቁትሩ ነበር፤
29ሌሎቹ ሌዋውያን ደግሞ ዕቃዎቹንና የቤተ መውደሱን ንዋያት ቅድሳት፣ዱቄቱን፣የወይን ጠጁን፣የወይራ ዘይቱን፣ዕጣኑን የሽቱውን ቅመማ ቅመም እንዲጠብቁ ተምመድበው ነበር።
30ከካህናቱም አንዳንዶቹ የሽቱውን ቅመማ ቅመም ይለውሱ ያዘጋጁ ነበር።
31የቆሬያዊው የሰሎም በኩር ልጅ ሌዋዊው ማቲትያ የቁርባኑን እንጀራ የመጋገር ኅላፊነት ተሰጥቶት ነበር።
32በየሰንበቱ የተሰጠው ከቀዓታውያን ወንድሞቻቸው መካከል ለአንዳንዶቹ ነበር።
33የሌዋውያን ቤተ ሰብ አለቆች የነበሩት መዘምራኑ ደግሞ በብይተ መቅደሱ ክፍሎች ውስጥ እንዲኖሩና ከሌላው ሥራ ሁሉ ነፃ ሌሊት የሚሠሩት ሥራ ነበራቸው።
34እነዚሁ ሁሉ የሌዋውያን ቤተ ሰብ አለቆች ሲሆኑ፣በትውልድ ሐረጋቸ መሠረት ተመዘገቡ፤የሚኖሩትም በኢየሩሳሌም ነበረ።
35የገባዖን አባት ይዒኤል የሚኖረው በገባዖን ነበረ፤የሚስቱም ስም መዓካ ይባላል።
36የበኩር ልጁ ዓብዶን ሲሆን፣የእርሱም ተከታዮች ዱር፣ቂስ፣በኣል፣ኔር፣ናዳብ፣
37ጌዶር፣አሒዮ፣ዛኩር፣ሚቅሎት ነበሩ።
38ሚቅሎት ሳምአን ወለደ፣እርሱም ከዘመዶቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ይኖሩ ነበር።
39ኔር ቂስን ወለደ፤ቂስ ሳኦልን ወለደ፤ሳኦል ዮናታን፣ሜልኪሳን፣አሚናዳብን፣አስበኣልን ወለደ።
40የዮናታ ወንድ ልጅ፤ መሪበኣል ነው፤መሪበኣል ሚካን ወለደ
41የሚካ ወንዶች ልጆች፤ፒቶን፣ሜሌክ፣ታሬዓ፣አካዝ።
42አካዝ የዕራን ወለደ፤ዘምንሪን ሞፃን ወለደ።
43ሞፃም ቢንዓን ወለደ፤ልጁ ረፋያ ነበረ፤ልጁ ኤልዓሣ፣ልጁ ኤሴል።
44ኤሴል ስድስት ወንዶች ልጆች ነበሩ፤ስማቸውም፦ ዓዝሪቃም፣ቦክሩ፣እስማኤል፣ሸዓርያ፣አብድዩ ሐናን እነዚህ የኤሴል ወንዶች ልጆች ናቸው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።