መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሶፎንያስ 3

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ለዐመፀኛዋ፣ ለጨቋኛና ለረከሰች ከተማ ወዮላት፡፡
2እርሷ የእግዚአብሔርን ድምፅ አልሰማችም፤ የያህዌንም ተግሣጽ አልተቀበለችም፤ በያህዌ አትታመንም፤ ወደ አምላኳም አትቀርብም፡፡
3መሪዎቿ እንደሚያገሡ አንበሶች፣ ዳኞችዋም ለነገ ሳያስተርፉ ያገኙት ሁሉ በልተው እንደሚጨርሱ እንደ ተራቡ የማታ ተኩላዎች ናቸው፡፡
4ነቢያቶችዋ ትዕቢተኞችና ተንኰለኞች ናቸው፡፡ ካህናትዋ የተቀደሰውን አርክሰዋል፤ ሕጉንም ተላልፈዋል፡፡
5ጻድቁ ያህዌ በእርሷ ውስጥ አለ፤ እርሱ ፈጽሞ አይሳሳትም፤ በየማለዳው ፍርዱን ይሰጣል፤ በየቀኑም ይህን ከማድረግ አይቆጠብም፤ ዐመፀኞች ግን ዕፍረት አያውቁም፡፡
6ሕዝቦችን አጥፍቻለሁ፤ ምሽጐቻቸውንም ደምስሻለሁ፡፡ ማንም እንዳያልፍባቸው መንገዶቻቸውን አፈራርሻለሁ፡፡ ከተሞቻቸው ስለ ተደመሰሱ ከእንግዲህ የሚኖርባቸው አይኖርም፡፡
7እኔም፣ «በእርግጥ ትፈሪኛለሽ፣ እርምትም ተቀበዪ፤ ላደርግብሽ እንዳሰብኩት ከመኖሪያሽ አትነቀዪ አልኩ፡፡ እነርሱ ግን በሚያደርጉት ሁሉ ክፋትን እያበዙ ሄዱ፡፡
8ስለዚህ ያህዌ እንዲህ ይላል፣ «እስከምፈርድበት ቀን ድረስ ጠብቁኝ፤ ምድሪቱ ሁሉ በቁጣዬ እሳት እንድትጠፋ አሕዛብን ለመሰብሰብ፣ መንግሥታትን ለማከማቸት፤ ቁጣዬንና ጽኑ መዓቴን እነርሱ ላይ ለማፍሰስ ወስኛለሁ፡፡
9በዚያ ጊዜ ሰዎች የያህዌን ስም እንዲጠሩ፣ አንድ ልብ ሆነውም እንዲያገለግሉት ንጹሑን አንደበት እሰጣቸዋለሁ፡፡›
10ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ ያሉት እኔን የሚያመልኩ የተበተኑ ሕዝቤ ለእኔ የሚገባውን ቁርባን ያመጡልኛል፡፡
11በዚያ ቀን በእኔ ላይ ከፈጸማችሁት በደል ሁሉ የተነሣ አታፍሩም፤ በትዕቢታቸው የሚደሰቱትን ከመካከላችሁ ስለማስወግድ ከእንግዲህ ወዲያ በቅዱሱ ተራራዬ ላይ አትታበዩብኝም፡፡
12ሆኖም፣ የዋሃንንና ትሑታንን አስቀራለሁ፤ እናንተም በያህዌ ስም ትተማመናላችሁ፡፡
13የእስራኤል ትሩፋን ከእንግዲህ ፍርድ አያጐድሉም፤ ሐሰትንም አይናገሩም፤ በአንደበታቸው ሐሰት አይገኝም፡፡ ይበላሉ፤ በሰላምም ያርፋሉ፤ የሚያስፈራቸውም አይኖርም፡፡»
14የጽዮን ልጅ ሆይ፣ ዘምሪ፤ እስራኤል ሆይ፣ እልል በዪ፤ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፣ በፍጹም ልብሽ ደስ ይበልሽ ደስ ይበልሽ፤ ሐሤትም አድርጊ፡፡
15ያህዌ ቅጣትሽን አስወግዷል፤ ጠላቶችንም አስወጥቷል፤ የእስራኤል ንጉሥ ያህዌ በመካከልሽ ነው፡፡ ከእንግዲህ ክፉን አትፈሪም፡፡
16በዚያ ቀን ኢየሩሳሌምን እንዲህ ይሏታል፤ «ጽዮን ሆይ አትፍሪ፤ እጆችሽም አይዛሉ፡፡
17አንቺን ለማዳን ብርቱ የሆነው አምላክሽ ያህዌ በመካከልሽ ነው፡፡ በአንቺ እጅግ ደስ ይለዋል፤ በፍቅሩም ያሳርፍሻል፡፡ በዝማሬ በአንቺ ደስ ይለዋል፡፡
18ለታወቁ ክብረ በዓላት ሐዘንን ከአንቺ አርቃለሁ፤ በመካከልሽ ሸክምና ዕፍረት ሆነውብሻል፡፡
19በዚያ ቀን የበደሉሽን ሁሉ እቀጣለሁ፤ ያነከሱትን እታደጋለሁ፤ የተጣሉትንም እሰበስባለሁ፡፡ ዕፍረታቸውን አስወግጄ በምድር ሁሉ ላይ ለምስጋናና ለክብር አደርጋቸዋለሁ፡፡
20በዚያ ቀን እመራችኃለሁ፤ በዚያ ቀን በአንድነት እሰበስባችኃለሁ፡፡ እኔ እንደ ሰበሰብኃችሁ፣ ምርኮአችንም እንደ ሰበሰብሁ ስታዩ የምድር ሕዝቦች ሁሉ ያመሰግኗችኃል፤ ያከብራችኃል ይላል ያህዌ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።