መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሩት 4

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ቦዔዝም ወደ ከተማይቱ በር ሄደና በዚያ ተቀመጠ፡፡ ወዲያውኑ ቦዔዝ ሲናገርለት የነበረው የቅርብ ዘመድ መጣ፡፡ ቦዔዝም ለእርሱ “ወዳጄ ሆይ፣ ና በዚህም ተቀመጥ” አለው፡፡ ሰውየውም መጣና ተቀመጠ፡፡
2ቦዔዝም ከከተማይቱ ሽማግሌዎች አሥር ሰዎች ወሰደ፣ “በዚህ ተቀመጡ” አላቸው፡፡ እነርሱም ተቀመጡ፡፡
3ቦዔዝም የቅርብ ዘመድ ለሆነው፣ “ከሞዓብ ምድር የተመለሰችው ኑኃሚን የወንድማችንን የአቤሜሌክን ቁራሽ መሬት ትሸጣለች፡፡
4እኔም ለአንተ አስታውቅህ ዘንድ አሰብሁ እንዲህም አልሁ፡- ‘ይህንን መሬት በዚህ በተቀመጡት በሕዝቤ ሽማግሌዎች ፊት ግዛው፡፡’ መቤዠት ብትፈልግ ተቤዠው፡፡ ነገር ግን መቤዠት የማትፈልግ ከሆነ ግን ከአንተ በቀር ሌላ የሚቤዥ የለምና፣ እኔም ከእአንተ በኋላ ነኝና እንዳውቀው ንገረኝ” አለው፡፡ የዚያን ጊዜ ሌላኛው ሰው “እቤዠዋለሁ” አለው፡፡
5ቦዔዝም “ከኑኃሚን እጅ እርሻውን በምትገዛበት ቀን፣ የሞተውን ሰው ስም በርስቱ ላይ እንድታስነሣለት የምዋቹን ሰው ሚስት ሞዓባዊቱን ሩትን ደግሞ መውሰድ አለብህ” አለ፡፡
6የቅርብ ዘመድ የሆነውም “የራሴን ርስት ሳልጎዳ እርሻውን ለራሴ መቤዠት አልችልም፡፡ እኔ ልቤዠው አልችልምና የእኔን የመቤዠት መብት ለራስህ ውሰድ” አለ፡፡
7በጥንት ዘመን መቤዠትና የሸቀጦች መለዋወጥ በተመለከተ በእስራኤል ዘንድ አንድ ልማድ ነበረ፡፡ ሁሉንም ነገር ለማጽናት ሰው ጫማውን ያወልቅና ለባልንጀራው ይሰጠዋል፤ በእስራኤል ውስጥ ሕጋዊ ስምምነት የሚኖረው በዚህ ሁኔታ ነበር፡፡
8ስለዚህ የቅርብ ዘመዱ ቦዔዝ፣ “አንተ ለራስህ ግዛው” አለው፡፡ እርሱም ጫማውን አወለቀ፡፡
9ቦዔዝም ለሽማግሌዎቹና ለሕዝቡ ሁሉ፣ “ለአቤሜሌክ የነበረውን ሁሉ እንደዚሁም ለኬሌዎንና ለመሐሎንም የነበረውን ሁሉ ከኑኃሚን እጅ እኔ መግዛቴን እናንተ ዛሬ ምስክሮች ናችሁ፡፡
10ከዚህም በላይ ስለ መሐሎን ሚስት ስለ ሞዓባዊቷ ሩት፡- የምዋቹን ሰው ስም በርስቱ ላይ እንዳስነሣ፣ ስሙ ከወንድሞቹ መካከልና ከአገሩም ደጅ እንዳይጠፋ፣ እኔ ደግሞ እርስዋ ሚስቴ እንድትሆን ወስጃታለሁ፡፡ እናንተም ዛሬ ምስክሮች ናችሁ” አላቸው፡፡
11በበሩ የነበሩ ሕዝብ ሁሉና ሽማግሌዎቹም እንዲህ አሉ፡- “እኛ ምስክሮች ነን፡፡ እግዚአብሔር ወደ ቤትህ የመጣችውን ሴት የእስራኤልን ቤት እንደ ገነቡት እንደ ሁለቱ እንደ ራሔልና ልያ ያድርጋት፡፡ አንተም በኤፍራታ ባለጠጋ ሁን፣ በቤተ ልሔምም እንደገና የታወቅህ ሁን፡፡
12ቤትህ እግዚአብሔር ከዚህች ወጣት ሴት በሚሰጥህ ዘር በኩል ትዕማር ለይሁዳ እንደወለደችለት እንደ ፋሬስ ቤት ይሁን” አሉት፡፡
13ስለዚህ ቦዔዝ ሩትን ወሰደ፣ ሚስቱም ሆነች፡፡ እርሱም ከእርስዋ ጋር ተኛ፣ እግዚአብሔርም ልጅ እንድትፀንስ ፈቀደላት፣ እርዋም ወንድ ልጅ ወለደች፡፡
14ሴቶችም ለኑኃሚን፣ “ዛሬ የሚቤዥ የቅርብ ዘመድ ያላሳጣሽ እግዚአብሔር ይባረክ፡፡ ይህ ሕጻን ስሙ በእስራኤል ውስጥ የገነነ ይሁን፡፡
15ይህ ልጅ ለአንቺ ሕይወትሽን የሚያድስ እርጅናሽንም የሚመግብ ይሁን፣ የምትወድሽ፣ ከሰባትም ወንዶች ልጆች ይልቅ ለአንቺ የምትሻል፣ ምራትሽ ይህን ልጅ ወልዳለችና፡፡
16ኑኃሚንም ሕፃኑን ወሰደችው፣ በእቅፍዋም አስቀመጠችው፣ እርሱንም ተንከባከበችው፡፡
17ጎረቤቶቿ የሆኑት ሴቶችም “ለኑኃሚን ወንድ ልጅ ተወለደላት” እያሉ ስም ሰጡት፡፡እነርሱም ስሙን ኢዮቤድ ብለው ጠሩት፡፡ እርሱም የዳዊት አባት የሆነው፣ የእሴይ አባት ሆነ፡፡
18አሁንም እነዚህ የፋሬስ ትውልድ ነበሩ፡- ፋሬስ የኤስሮም አባት ሆነ፣
19ኤስሮምም የአራም አባት ሆነ፣ አራምም የአሚናዳብ አባት ሆነ፣
20አሚናዳብም የነአሶን አባት ሆነ፣ ነአሶንም የሰልሞን አባት ሆነ፣
21ሰልሞንም የቦዔዝ አባት ሆነ፣ ቦዔዝም የኢዮቤድ አባት ሆነ፣
22ኢዮቤድ የእሴይ አባት ሆነ፣ እሴይም የዳዊት አባት ሆነ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።