መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

የዮሐንስ ራእይ 22

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከዚያም መልአኩ፣ እንደ መስተዋት የጠራውን የሆነውን የሕይወት ውሃ ወንዝ አሳየኝ። ወንዙም የሚወጣው ከእግዚአብሔርና ከበጉ ዙፋን ነበር
2በከተማዋ ዋና መንገድ መካከል ያልፍ ነበር። በወንዙ ግራና ቀኝ አሥራ ሁለት ወር ሙሉ አሥራ ሁለት ዓይነት ፍሬ የሚሰጥ የሕይወት ዛፍ ነበር። የዛፉ ቅጠሎች ሕዝቦችን ሁሉ ይፈውሱ ነበር።
3ከእንግዲህ ምንም ዐይነት መርገም አይሆንም። የእግዚአብሔርና የበጉ ዚፋን ከተማው ውስጥ ይሆናሉ፤ አገልጋዮቹም ያገለግሉታል።
4ፊቱን ያያሉ፤ ስሙም ግንባሮቻቸው ላይ ይሆናል።
5ከእንግዲህ ሌሊት አይሆንም፤ ጌታ አምላክ ስለሚያበራላቸው የመብራት ወይም የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም። ከዘላለም እስከ ዘላለም ይነግሣሉ።
6መልአኩም እንዲህ አለኝ፤ “እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛ ናቸው። ጌታ፣ የነቢያት መናፍቅ አምላክ ቶሎ መሆን ያለበትን ለአገልጋዮቹ እንዲያሳያቸው መልአኩን ላከ።”
7“እነሆ፣ ቶሎ እመጣለሁ! ለዚህ መጽሐፍ የትንቢት ቃሎች የሚታአእ የተባረከ ነው።
8እነዚህን ነገሮች የሰማሁና ያየሁ እኔ ዮሐንስ ነኝ። እነዚህን በሰማሁና ባይብሁ ጊዜ እነዚህን ነገሮች ላሳየኝ መልአክ ለመስገድ በፊቱ ተደፋሁ።
9እርሱ ግን፣ “እንዳታደርገው! እኔ ራሴ ከወንድሞችህ ከነቢያት ጋር፣ ለዚህ መጽሐፍ ቃል ከሚታዘዙት ጋር አብሬ አገልጋይ ነኝ። ይልቅ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ!”
10እንዲህም አለኝ፤ ጊዜው በጣም ቅርብ ስለሆነ የዚህን መጽሐፍ የትንቢት ቃሎች በማኅተም አትዝጋው።
11ዐመፀኛው ማመፁን ይቀጥል። ርኩሱም ርኩሰት ማድረጉን ይቀጥል። ጻድቁም ጽድቅ የሆነውን ማድረጉን ይቀጥል። ቅዱስም ቅዱስ መሆን ይቀጥል።
12“እነሆ፣ ቶሎ እመጣለሁ። ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው የምከፍለው ዋጋ ከእኔ ዘንድ አለ።
13እኔ አልፋና ዖሜጋ፣ ፊተኛውና ኋለኛው፤ የመጀመሪያውና የመጨረሻው ነኝ።
14ከሕይወት ዛፍ ለመብላትና በበሮቿ ወደ ከተማዋ ለመግባት መብት እንዲኖራቸው ልብሳቸውን የሚያጥቡ የተባረኩ ናቸው።
15ውሾች፣ ጠንቋዮች፣ አመንዝራዎች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ ጣዖት አምላኪዎችና ሐሰትን የሚወዱና የሚያደርጉ ግን በውጭ አሉ።
16እኔ ኢየሱስ ለእናንተ እንዲመሰክር መልአኬን ወደ አብያተ ክርስቲያናት ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥርጥ ዘር ነኝ፤ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።”
17መንፈሱና ሙሽራይቱ፣ “ና!” ይላሉ፤ የሚሰማ ሁሉ፣ “ና!” ይበል። ማንም የተጠማ ቢኖር ይምጣ፣ የሚፈልግ የሕይወትን ውሃ በነጻ ይውሰድ።
18የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ለሚሰሙ ሁሉ እኔ እመሰክራለሁ፣ ማንም ትንቢቱ ላይ ቢጨምር እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን መቅሠፍቶች ይጨምርበታል።
19ማንም ከዚህ መጽሐፍ ትንቢት ቢያጎድል እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ ከተጻፈው የሕይወት ዛፍና ቅድስት ከተማ ዕድሉን ያጎልበታል።
20ለእነዚህ ነገሮች የሚመሰክር እርሱ፣”አዎን! ቶሎ እመጣለሁ” አሜን! ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና! ይላል።
21የጌታ ኢየሱስ ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።