1ወንድሞች ተስማምተው በአንድነት ቢኖሩ እንዴት መልካም ነው! ምንኛስ አስደሳች ነው፡፡
2በአሮን ራስና ጢም ላይ እንደሚፈስስ እስከ ልብሱን ዐንገት ጌጥ ድረስ እንደሚወርድ ውድ ሽቱ ነው፡፡
3ደግሞም በጽዮን ተራራ ላይ እንደሚወርድ እንደ አርሞንዔም ጠል ነው፡፡ ያህዌ በዚያ በረከቱን አዞአልና ሕይወትንም እስከ ዘላለም አዞአል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።