መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 132

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ያህዌ ሆይ፣ ዳዊትን፣ የተቀበለውንም መከራ ሁሉ አስብ፡፡
2እርሱ ለያህዌ ማለ፣ ለያዕቆብም ኃያል አምላክ ቃል ገባ፤
3እንዲህም አለ፣ «ወደ ቤቴ አልገባም፤ አልጋዬ ላይ አልወጣም
4ለዐይኖቼ እንቅልፍን ለሽፋሽፍቶቼም ዕረፍትን አልሰጥም፤
5ለያህዌ ስፍራን፣ ለያዕቆብ ኃያል ማደሪያን እስካገኝ ድረስ፡፡
6እነሆ፣ በኤፍራታ ሰማነው፣ በይዓሪም አገኘነው፡፡
7ወደ ማደሪያው እንግባ እግሮቹ በሚቆሙበት ስፍራ እንስገድ፡፡
8ያህዌ ሆይ ተነሥ አንተና የኃይልህ ታቦታ ወደ ማደሪያህ ስፍራ ሂዱ፡፡
9ካህናትህ ጽድቅን ይልበሱ ታማኞችህ እልል ይበሉ፡፡
10ስለ ባርያህ ስለ ዳዊት ስትል የተቀባኸውን ንጉሥ አትተወው፡፡
11ያህዌ ለዳዊት በእውነት ማለ በማይታጠፍ መሐላ እንዲህ አለ «ከልጆችህ አንዱን ዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ
12ልጆችህ ኪዳኔን፣ የማስተምራቸውንም ሕጌን ቢጠብቁ፣ ልጆቻቸው ለዘላለም በዙፋንህ ላይ ይቀመጣሉ፡፡»
13ያህዌ ጽዮንን መርጧልና ማደሪያው እንድትሆን ወዶአልና፡፡
14«ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት ፈልጌአታለሁና በእርሷ እኖራለሁ፡፡
15እጅግ አትረፍርፌ እባርካታለሁ ድኾቿን እንጀራ አጠግባለሁ፡፡
16ካህናቶቿን ማዳንን አለብሳቸዋለሁ ታማኞቿም እልል ይላሉ፡፡
17በዚያ ለዳዊት ቀንድ አበቅላለሁ ለቀባሁትም ሰው መብራት አዘጋጃለሁ፡፡
18ጠላቶቹን እፍረት አከናንባቸዋለሁ እርሱ ላይ ግን አክሊሉ ያበራል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።