1«ከልጅነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ አስጨነቁኝ» ይበል እስራኤል፡፡
2በእርግጥ፣ ከልጅነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ አስጨነቁኝ ይሁን እንጂ አላሸነፉኝም፡፡
3አራሾች ጀርባዬን አረሱት ትልማቸውንም አስረዘሙት፡፡
4እግዚአብሔር ጻድቅ ነው የክፉዎችን ገመድ በጣጥሶ ጣለ፡፡
5ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ ይፈሩ ወደ ኃላቸውም ይመለሱ፡፡
6ገና ከመብቀሉ እንደሚደርቅ ቤት ጣር ላይ እንዳለ ሣር ይሁኑ፡፡
7ደግሞ ለዐጫጁ እጁን ለነዶ ሰብሳቢ እቅፉን እንደማይሞላ ነዶ ይሁኑ፡፡
8መንገድ ዐላፊዎችም፣ «የያህዌ በረከት እናንተ ላይ ይሁን፤ በያህዌ ስም ባረክናችሁ አይበሉ፡፡»