1ያህዌን የሚፈሩ ሁሉ በመንገዶቹም የሚሄዱ የተባረኩ ናቸው፡፡
2በእጆችህ ሥራ ደስ ይልሃል ትባረካለህ፤ ይሳካልሃልም፡፡
3በቤትህ ውስጥ ሚስትህ እንደሚያፈራ ወይን ትሆናለች ልጆችህም በማእድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ተክል ይሆናሉ፡
4አዎን፣ ያህዌን የሚፈራ እንዲህ ይባረካል፡፡
5ያህዌ ከጽዮን ይባርክህ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ የኢየሩሳሌምን ብልጽግና ያሳይህ፡፡
6የልጅ ልጆችን ለማየት ያብቃህ እስራኤል ላይ ሰላም ይሁን፡፡