1ያህዌ ሆይ፣ ስለ ታማኝነትህና ስለ ትክክለኛ ፍርድህ ምስጋና እዘምራለሁ፡፡
2ነቀፋ በሌለበት መንገድ እሄዳለሁ አንተ ወደ እኔ የምትመጣው መቼ ነው? በቤቴ ውስጥ ያለ ነቀፋ እመላለሳለሁ፡፡
3በዐይኖቼ ፊት በደል አላኖርም የክፉዎችን ሥራ እጠላለሁ ከቶም አልተባበራቸውም፡፡
4ጠማማ ሰዎች ከእኔ ይርቃሉ ከክፋት ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም፡፡
5ባልንጀራውን በስውር የሚያማውን አጠፋለሁ፡፡ ትዕቢተኛ ዐይንና እብሪተኛ ልብ ያለውን ሰው አልታገሠውም፡፡
6ከእኔ ጋር እንዲኖሩ፣ ዐይኖቼ በምድሪቱ ያሉ ታማኞች ላይ ናቸው በንጹሕና የሚሄድ እርሱ ያገለግለኛል፡፡
7አታላይ ሰው ቤቴ ውስጥ አይኖርም ሐሰተኛም በዐይኖቼ ፊት አይከብርም፡፡
8በምድሪቱ ያሉትን ክፉ አድራጊዎች በየማለዳው አጠፋቸዋለሁ፤ ክፉ አድራጊዎችን ሁሉ ከያህዌ ከተማ አስወግዳቸዋለሁ፡፡