1ያህዌ ሆይ፣ ለምን ርቀህ ቆምህ? በመከራ ጊዜ ለምን ራስህን ሰወርህ?
2በእብሪት ተነሳሥተው ክፉዎች ጭቁኖችን ያሳድዳሉ እባክህ ክፉዎች ባጠመዱት ወጥመድ ይጠመዱ፡፡
3ክፉ ሰው በልቡ ምኞት ይኩራራል ስግብግቡን ይባርካል፤ ያህዌን ይሰድባል፡፡
4ክፉ ሰው በራሱ ይመካል፤ እግዚአብሔርንም አይፈልግም፡፡ ስለ እርሱ ምንም ደንታ ስለሌለው ስለ እግዚአብሔር አያስብም፡፡
5ነገሩ ዘወትር ለእርሱ የተሳካ ነው የእግዚአብሔርን ፍርድ ግን ሊረዳ አይችልም፡፡ በጠላቶቹ ላይ ይሳለቃል፡፡
6በልቡም፣ «በፍጹም አልወድቅም ከትውልድ እስከ ትውልድ መከራ አያገኘኝም» ይላል፡፡
7አፉ መርገምን፣ ሸፍጥንና ግፍን የተሞላ ነው፤ በምላሱ ይጐዳል፤ ይገድላልም፡፡
8መንደሮች አጠገብ አድፍጦ ይጠብቃል በሰዋራ ቦታ ንጹሐንን ይገድላል ዐይኖቹም ምስኪኖች ላይ ያነጣጥራሉ፡፡
9ደን ውስጥ እንዳለ አንበሳ በስውር ያደባል ረዳት የሌለውን ለመያዝ ያሸምቃል፡፡ መረቡን ዘርግቶ ጭቁኖችን ያጠምዳል፡፡
10እርሱ መትቶ ይጥላቸዋል፤ ረዳት የሌላቸው ደካሞች ምስኪኖችም የእርሱ ሰለባ ሆነው ይወድቃሉ፡፡
11በልቡም፣ «እግዚአብሔር ረስቶአል እንዳያይም ፊቱን ሸፍኖአል» ይላል፡፡
12ያህዌ ሆይ፣ ተነሥ! አምላክ ሆይ ኃያል ክንድህ ይነሣ! የተጨቆኑትን ችላ አትበላቸው፡፡
13ክፉ ሰው ለምን እግዚአብሔርን ይንቃል? በልቡም ለምን፣ «እግዚአብሔር አይቀጣኝም» ይላል?
14አንተ ግን መከራንና ሐዘንን ታያለህ ምስኪኑም ራሱን በአንተ ላይ ይጥላል፤ ለድኻ አደጉም አንተ ረዳቱ ነህ፡፡
15የክፉና የበደለኛውን ክንድ ስበር አንተ እንደማታገኘው አስቦ ነበር የእጁንም ሰጠው፡፡
16ያህዌ ከዘላለም እስከ ዘላለም ንጉሥ ነው ሕዝቦችም ከምድሩ ይወገዳሉ፡፡
17ያህዌ የጭቁኖቹን ጩኸት ሰምቷል ልባቸውን ታበረታለህ፤ ጸሎታቸውንም ትሰማለህ
18ከእንግዲህ ማንም በምድር ላይ ሽብር እንዳያደርግ አንተ አባት ለሌላቸውና ለጭቁኖች መከታ ሆንህላቸው፡፡