1እናቱ ያስተማረችው የንጉስ ልሙኤል ቃሎች፣
2ልጄ ሆይ፣ ምንድን ነው? የማሕጸኔ ልጅ ሆይ ምንድን ነው? የስእለቴ ልጅ ሆይ ምንድን ነው?
3ብርታትህን ለሴቶች አትስጥ፣ ነገስታትን ለሚያጠፉም መንገድህን፡፡
4ለነገስታት አይደለም፣ ልሙኤል ሆይ፣ የወይን ጠጅ መጠጣት ለነገስታት አይደለም፣ “ብርቱ መጠጥ የት ነው” ብለው ይጠይቁ ዘንድ ለገዢዎችም አይደለም፡፡
5ምክንያቱም እነርሱ መጠጥ ከጠጡ የተደነገገውን ሕጉን ይረሳሉ፣ የተጨቆኑ ሰዎችንም መብት ያጣምማሉ፡፡
6እየጠፉ ላሉ ሰዎች ብርቱ መጠጥ ስጧቸው፣ መራራ ችግር ውስጥ ላሉትም ወይን ስጧቸው፡፡
7ይጠጣል ድህነቱንም ይረሳል፣ ችግሩንም አያስታውስም፡፡
8መናገር ለማይችሉ ተናገርላቸው፣ እየጠፉም ላሉት ሁሉ ስለ ጉዳያቸው ተናገር፡፡
9ትክክል ስለሆነው ነገር ጮህ ብለህ ተናገር፣ ፍርድም ስጥ፣ ስለ ድሆችና ስለ ተቸገሩም ሰዎች ጉዳይ መልስ ስጥ፡፡
10ችሎታ ያላትን ሴት ማን ሊያገኛት ይችላል? የእርሷ ዋጋ ከእንቁ የበለጠ ነው፡፡
11የባሏ ልብ በእርሷ ይተማመናል፣ ድሃም አይሆንም፡፡
12በሕይወት ዘመኗ ሁሉ ለእርሱ መልካም ነገር ታደርግለታለች፣ ክፋትንም አታደርግበትም፡፡
13የበግ ጠጉርና የተልባ ትመርጣለች፣ በእጆቿም ደስ ብሏት ትሰራለች፡፡
14እርሷ እንደ ነጋዴ መርከብ ናት፤ መብሏን ከሩቅ ታመጣለች፡፡
15በሌሊት ተነስታ ለቤተሰቧ መብልን ታቀርባለች፣ ስራዋንም ለሴት አገልጋዮቿ ታከፋፍላለች፡፡
16እርሻን ተመልክታ ትገዛለች፣ በእጆቿም ፍሬ የወይን ተክል ትተክላለች፡፡
17ራሷን በብርታት ታለብሳለች፣ ክንዶቿንም ታጠነክራለች፡፡
18ለእርሷ ጥሩ ትርፍ የሚያመጣላትን ታውቃለች፤ ሌሊቱንም ሙሉ መብራቷ አይጠፋም፡፡
19እጆቿን በእንዝርቱ ላይ ታስቀምጣለች፣ የሚሽከረከረውንም ክር ትይዛለች፡፡
20እጇን ለድሆች ትዘረጋለች፤ ለተቸገሩትም እጆቿን ትዘረጋለች፡፡
21በረዶም ቢዘንብ ስለ ቤተሰቧ አትፈራም፣ ቤተሰቧ ሁሉ ቀይ ልብስ ለብሰዋልና፡፡
22ለመኝታዋ የአልጋ ልብስ ትሰራለች፣ ቀጭን ሐምራዊ ልብስም ትለብሳለች፡፡
23ባለቤቷም ከአገሩ ሽማግሌዎች ጋር ሲቀመጥ በበሮቹ የታወቀ ይሆናል፣ ፡፡
24የሊኖ ልብሶችን ትሰራለች፣ ትሸጣለችም፣ ለነጋዴዎችም መቀነቶችን ታስረክባለች፡፡
25ጥንካሬንና ክብርን ተላብሳለች፣ ወደፊት የሚመጣውን ጊዜ እያሰበች ትስቃለች፡፡
26አፏን በጥበብ ትከፍታለች፣ የደግነት ሕግም በምላሷ ላይ አለ፡፡
27የቤተሰቦቿን መንገዶች ትመለከታለች፣ የስንፍናንም እንጀራ አትበላም፡፡
28ልጆቿም አድገው የተባረክሽ ነሽ ይሏታል፤ ባለቤቷም እንዲህ ብሎ ያመሰግናታል፣
29“ብዙ ሴቶች መልካምን አድርገዋል፣ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡”
30ቁንጅና አሳሳች ነው፣ ውበትም ጠፊ ነው፣ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርሷ ትመሰገናለች፡፡
31የእጆቿን ፍሬ ስጧት፣ ስራዋቿም በአደባባዮች ያስመሰግኗት፡፡