1ስለዚህ ውድ ወንድሞቼ፤ ወዳጆቼም ሆይ፤ የምናፍቃችሁ፤ ደስታዬና አክሊሎቼ የሆናችሁ በዚህ መንገድ በጌታ ጸንታችሁ ቁሙ።
2ኤዎድያና ሲንጢኪ እርስ በርሳቸው በጌታ ተስማምተው እንዲኖሩ እለምናቸዋለሁ።
3በርግጥ አንተም እዚያ ያለኸው የሥራ ባልደርባዬ እነዚህን ሴቶች እንድትረዳቸው እለምንሃለሁ። እነርሱም ወንጌልን በማሰራጨት ከእኔና ከቅሌምንጦስ ጋር እንዲሁም ስማቸው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት ከሌሎች የሥራ ባልደረቦቼ ጋር ብዙ ተጋድለዋል።
4ሁል ጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ ደግሜም እላለሁ ደስ ይበላችሁ።
5ደግነታችሁ በሰዎች ሁሉ ዘንድ ይታወቅ።
6ስለ ሁሉም ነገር በጸሎት፤ በልመናና በምስጋና ለእግዚአብሔር አስታውቁ እንጂ ስለምንም ነገር አትጨነቁ። ጌታ ቅርብ ነውና።
7ከማስተዋል በላይ የሆነው የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።
8በመጨረሻም ወንድሞችሆይ፥ እውነት የሆነውን ሁሉ፤ ክቡር የሆነውን ሁሉ፤ ትክክል የሆነውን ሁሉ፤ንጹሕ የሆነውን ሁሉ፤ ፍቅር የሆነውን ሁሉ፤ መልካም የሆነውን ሁሉ፤ በጎነት ቢሆን፤ ምስጋናም ቢሆን፤ እንደ እነዚህ ያሉትን ነገሮች ሁሉ አስቡ።
9ከእኔ የተማራችሁትንና የተቀበላችሁትን፤ የሰማችሁትንና ያያችሁትን ማናቸውንም ነገር አድርጉ። የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።
10እንደገና በመጨረሻ ጊዜ ለእኔ ማሰብ ስለ ጀመራችሁ በጌታ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል። በርግጥ ከዚህ በፊት ስለ እኔ ያሰባችሁ ቢሆንም እኔን ለመርዳት ዕድሉን አላገኝችሁም ነበር።
11ይህን የምለው ለራሴ ጥቅም አይደለም። ምክንያቱም በሁሉም ሁኔታ ባለኝ ነገር መርካትን ተምሬአለሁ።
12በማጣትም ሆነ በማግኘት እንዴት መኖር እንዳለብኝ ዐውቃለሁ። በማንኛውም መንገድ የመጥገብንና የመራብን፤ የማግኝትንና የማጣትን ምሥጢር ተምሬአለሁ።
13ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን ነገር ማድረግ እችላለሁ።
14ይሁን እንጂ፤ እናንተ የችግሬ ተካፋዮች በመሆናችሁ መልካም አድርጋችኋል።
15እናንተ የፊልጵስዩስ ሰዎች የወንጌልን ተልዕኮ በጀመርኩበት ጊዜ ከመቄዶንያ ስወጣ ከእናንተ በቀር በመስጠትም ሆን በመቀበል ከእኔ ጋር የተባበረ ሌላ ቤተ ክርስቲያን እንዳልነበረ ታውቃላችሁ።
16በተሰሎንቄ በነበርኩበት ጊዜም ቢሆን ከአንድ ጊዜ በላይ ለሚያስፈልገኝ ርዳታ ልካችሁልኛል።
17ይህንንም ስል የእናንተን ስጦታ ለማግኝት በመፈለግ ሳይሆን የልግሥናችሁ ፍሬ እንዲበዛላችሁ በመመኘት ነው።
18ሁሉንም ነገር ተቀብያለሁ፤በዝቶልኛል፤ ሞልቶልኛልም። የላካችሁልኝን ስጦታ ከኤጳፍሮዲቱስ እጅ ተቀብዬአለሁ። ይህም ስጦታ በመልካም መዓዛ እንደ ተሞላ መሥዋዕት እግዚአንሔር የሚቀበለውና ደስ የሚሰኝበት ነው።
19ደግሞም አምላኬ እንደ ክብሩ ባለጠግነቱ በክርስቶስ ኢየሱስ አማካይነት የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሰጣችኋል።
20እንግዲህ ለአባታችንና ለአምላካችን ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ክብር ይሁን፤ አሜን።
21በክርስቶስ ኢየሱስ ለሆኑት ሁሉ ሰላምታ አቅርቡልኝ። ከእኔም ጋር ያሉት ወንድሞች ሰላምታ ያቀርቡላችሁኋል።
22እዚህ ያሉት አማኞች ሁሉ በተለይም የሮማ ቤተ መንግሥት ያሉ ሠራተኞች ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
23የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከመንፈሳችሁ ጋር ይሁን።