መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘኁልቁ 36

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከዚያ ከዮሴፍ ትውልዶች ጎሣ የሆኑት፣ የአባቶቻቸው ቤተሰቦች መሪዎች፣ የምናሴ ልጅ በሆነው በሚኪር ልጅ ገለዓድ የተመሠረተው ጎሳ በሙሴና በእስራኤላዊያን አባቶች ቤተሰቦች አለቆች ፊት መጥተው ተናገሩ፡፡
2እንዲህም አሉ፣ “ጌታችን ሆይ፣ ያህዌ ለእስራኤል ህዝብ ርስታቸውን በዕጣ እንድታካፍላቸው አዞሃል፡፡ የወንድማችንን የሰለጰዓድን ድርሻ ለሴት ልጆቹ እንድትሰጥ ያህዌ አዝዞህ ነበር፡፡
3ነገር ግን ሴት ልጆቹ ከእስራኤል ሰዎች ከሌላ ጎሣ ወንዶችን ቢያገቡ፣ ድርሻቸው የሆነው መሬት ከአባቶቻችን ድርሻ ተነቅሎ ወደ ሌላ ጎሣ ይተላለፋል፡፡ መሬቱ የገቡበት የሌላ ጎሳ ድርሻ ይሆናል፡፡ በዚያ ሁኔታ፣ ከእኛ ርስትነት ይነቀላል፡፡
4ይህ ሲሆን፣ የእስራኤል ኢዮቤልዩ ሲመጣ፣ የእነርሱ ድርሻ የተጋቧቸው ጎሣዎች ርስት ይሆናል፡፡ በዚህ መንገድ የእነርሱ ድርሻ ከእኛ አባቶች ጎሣ ይወሰዳል፡፡
5ስለዚህም ሙሴ በያህዌ ቃል ለእስራኤል ሰዎች ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ እንዲህም አለ፣ “የዮሴፍ ትውልዶች ጎሣ የተናገሩት ትክክል ነው፡፡
6ያህዌ ስለ ሰለጰዓድ፣ ሴት ልጆች ያዘዘው ይህ ነው፡፡ እንዲህም አለ፣ ‘የመረጡትን ያግቡ፣ ነገር ግን ማግባት ያለባቸው ከአባታቸው ጎሣ ብቻ ነው፡፡’
7የእስራኤል ሰዎች ድርሻ ከአንድ ጎሣ ወደ ሌላው መሄድ የለበትም፡፡ እያንዳንዱ እስራኤላዊ የራሱን ጎሣ ድርሻ ይዞ መቀጠል አለበት፡፡
8ከጎሣዋ ርስት የወረሰች እያንዳንዷ የእስራኤል ሴት፣ ማግባት ያለባት ከአባቷ ጎሣ ውስጥ ብቻ ነው፡፡ ይህ የሚሆነው እያንዳንዱ እስራኤላዊ የአባቶቹን ርስት ይዞ እንዲኖር ነው፡፡
9ከአንዱ ጎሣ ወደ ሌላው ምንም ርስት መተላለፍ የለበትም፡፡ የእስራኤል ህዝብ እያንዳንዱ ጎሣ የራሱን ርስት ይዞ መቀጠል አለበት፡፡”
10ስለዚሀ የሰለጰዓድ ሴት ልጆች ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ፡፡
11የሰለጰዓድ ሴት ልጆች ማህለህ፣ ቲርጳ፣ ጌግላ፣ ሚልካ፣ ኑዔ
12ልጅ የምናሴትን ትውልዶች አገቡ፡፡ በዚህ መንገድ፣ ርስታቸው የአባታቸው ጎሣ ርስት ሆኖ ቀረ፡፡
13ያህዌ በሙሴ በኩል በሞአብ ሜዳዎች በዮርዳኖስ ኢያሪካ ላይ ለእስራኤል ሰዎች የሰጣቸው ትዕዛዛትና ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።