መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘኁልቁ 25

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እስራኤል በሰጢም ተቀመጠ፣ ወንዶቹም ከሞዓብ ሴቶች ጋር ተኙ፣
2ይህም ሞአባዊያኑ ህዝቡን ለእነርሱ አማልዕክት የተሰዋውን ስለጋበዟቸው ነው፡፡ ስለዚህ ህዝቡ ለጣኦት የተሰዋውን በሉ ደግሞም ለሞአባውያን አማልዕክት ሰገዱ፡፡
3የእስራኤል ወንዶች የፌጎርን በኣል በማምለክ ተባበሩ፣ እናም የያህዌ ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፡፡
4ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “ብርቱ ቁጣዬ ከእስራኤል ይርቅ ዘንድ የህዝቡን መሪዎች ሁሉ ግደልና እነርሱን በቀን ብርሃን ለማጋለጥ ስቀላቸው፡፡”
5ስለዚህም ሙሴ ለእስራኤል መሪዎች እንዲህ አለ፣ “እያንዳንዳችሁ የፌጎርን በኣል በማመልክ የተባበሩትን ሰዎቻችሁን ግደሉ፡፡”
6ከዚያ ከእስራኤል ወንዶች አንዱ ቀርቦ ከቤተሰቡ አባላት ጋር አንዲት ምድያማዊት ሴት አመጣ፡፡ ሙሴና መላው የእስራኤል ህዝብ እያዩ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ሆነው እያለቀሱ ሳለ ይህ ሆነ፡፡
7የአሮን ልጅ፣ የአልዓዛር ልጅ ካህኑ ፊንሀስ ይህን ሲመለከት፣ ከማህበሩ መሀል ጦሩን በእጁ ይዞ ተነሳ፡፡
8እርሱም ወደ ድንኳኑ እስራኤላዊውን ሰው ተከትሎ ገብቶ የእስራኤላዊውን ወንድና የምድያማዊቷን ሴት የሁለቱንም አካላት በአንድነት በጦሩ ወጋ፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር በእስራኤል ህዝብ ላይ የላከው መቅሰፍት አቆመ፡፡
9በመቅሰፍቱ የሞቱት በቁጥር ሃያ አራት ሺ ነበሩ፡፡
10ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣
11“ካህኑ፣ የአሮን ልጅ የአልአዛር ልጅ ፊንሀስ፣ ቁጣዬን ከእስራኤል ህዝብ አርቋል ምክንያቱም በእነርሱ መሃል የእኔን ቅንአት ቀንቷል፡፡ ስለዚህ የእስራኤልን ህዝብ በቁጣዬ ፈጽሞ አላጠፋኋቸውም፡፡
12ስለዚህ እንዲህ በል፣ ‘ያህዌ እንዲህ ይላል፣ “እነሆ፣ ለፊንሐስ የሰላሜን ኪዳን እሰጠዋለሁ፡፡
13ለእርሱና ከእርሱ በኋላ ለትውልዱ፣ ዘለዓለማዊ የክህነት ኪዳን ይሆናል፤ ምክንያቱም እርሱ ለእኔ ለአምላኩ ለእግዚአብሔር ቀንቷል፡፡ ለእስራኤል ህዝብ አስተሰርይዋል፡፡”
14ከምድያማዊቷ ሴት ጋር የተገደለው የእስራኤላዊ ሰው የሰሉ ልጅ ስም ዘንበሪ ሲባል፣ የስምኦናውያን አባቶች ቤተሰብ መሪ ነበር፡፡
15የተገደለችው የምድያም ሴት ስም ከስቢ ነበር፣ እርሷም ከምድያም ቤተሰብ የጎሳው መሪ የሱር ሴት ልጅ ነበረች፡፡
16ስለዚህም ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
17”ምድያማዊያንን እንደ ጠላት ቆጥራችሁ አጥፏቸው፣
18እነርሱ በአታላይነታቸው እንደ ጠላት አስተናግደዋችኋልና፡፡ በፌጎር በሆነውና በእናታቸው በከስቢ ጉዳይ በፌጎር ምክንያት በመቅሰፍቱ ቀን በተገደለችው በምድያም አለቃ ልጅ ወደ ክፉ መርተዋችኋል፡፡”
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።