መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ነህምያ 12

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ብዙ ካህናትና የሌዊ ትውልዶች ከዘሩባቤል እና ከኢያሱ ጋር ከባቢሎን ተመለሱ፡፡ እነዚህም፡ ሠራያ፣ ኤርምያስ፣ ዕዝራ፣
2አማርያ፣ ሙሉክ፣ ሐጡስ፣
3ሴኬንያ፣ ሬሁም፣ ሜሪሞት፣
4አዶ፣ ጌንቶን፣ አብያ፣
5ሚያሚን፣ መዓድያ፣ ቢልጋ፣
6ሸማያ፣ ዮያሪብ፣ ዮዳኤ፣
7ሰሉ፣ ዓሞቅ፣ ኬልቅያስና ዮዳኤ ነበሩ፡፡ እነዚህ በኢያሱ ዘመን የካህናቱና የወንድሞቸው አለቆች ነበሩ፡፡
8የተመለሱት የሌዊ ትውልዶች ዝርዝር ይህ ነው፡፡ እነርሱም ኢያሱ፣ ቢንዊ፣ ቀድምኤል፣ ሰራብያ፣ ይሁዳ እና መታንየ ነበሩ፡፡ የእነዚሀ ሀላፊነት ለእግዚአብሔር የምስጋና ዝማሬ ማቅረብ ነበር፡፡
9በቅቡቅያ፣ ዑኒም እና ሌሎች የሌዊ ትውልዶች በዝማሬ ወቅት በትይዩ የሚቆሙ የዝማሬ ቡድን አበጁ፡፡
10ከብዙ አመታት አስቀድሞ አያሱ ሊቀ ካህን ነበር፡፡ ኢያሱ የዩአቂም አባት ነበረ፣ ዮአቄም የኤልያሴብ አባት ነበረ፣ ኤልያሴብ የዩአዳን አባት ነበረ፣
11ዩአዳ የዮናታን አባት ነበረ፣ ዮናታን የያዱአን አባት ነበረ፡፡
12ዮአቂም የካህናቱ ሁሉ መሪ ነበረ፡፡ የካህናቱ ቤተሰቦች መሪዎች እነዚህ ነበሩ፡ የሠራያ ቤተሰብ መሪ ምራያ፣ የኤርምያስ ቤተሰብ መሪ ሐናንያ፣
13የዕዝራ ቤተሰብ መሪ ሜሱላም፣ የአማርያ ቤተሰብ መሪ ይሆሐናን
14የሙሊኪ ቤተሰብ መሪ ዮናታን፣ የሰብንያ ቤተሰብ መሪ ዮሴፍ
15ከካሪም ቤተሰብ ብዙዎቹ መሪዎች ዓድና ነበሩ፣ ከመራዮት ቤተሰብ ሔልቃይ
16ከአዶ ቤተሰብ ዘካርያስ ከጌንቶን ቤተሰብ ሜሱላም
17ከአብያ ቤተሰብ ዝክሪ መሪዎች ነበሩ፡፡ ከሚያሚን ቤተሰብም አንድ መሪ ነበር፡፡ ከሞዓድያ ቤተሰብ ፈልጣይ ነበር፡፡
18ከቢልጋ ቤተሰብ ሳሙስ፣ ከሸማያ ቤተሰብ ዮናታን
19ከዮያሪብ ቤተሰብ መትናይ፣ ከዮዳኤ ቤተሰብ ኦዚ፣
20ከሳላይ ቤተሰብ ቃላይ፣ ከዓምቅ ቤተሰብ ዔቤር፣
21ከኬልቅያስ ቤተሰብ ሐሽብያ፣
22ኤሊያሴብ ሌዋውያንን በሚመራበት ወቅት፣ የእነርሱ ሁሉ ዝርዝር ይህ ነው፡ ኤሊያሴብ፣ ዮአዳ፣ ዮሐና እና ያዱአ የካህናቱ ሁሉ መሪዎች ነበሩ፡፡ እነርሱ የሌዊ ትውልድ የሆኑትን ቤተሰቦች ስሞች መዘገቡ፡፡ዳርዮስ የፋርስ ንጉስ በነበረበት ዘመን የየቤተሰቡን መሪዎች የመመዝገቡ ሀላፊነት የካህናቱ ነበር፡፡
23የሌዊ ትውልድ የሆኑ የቤተሰብ መሪዎችን ስሞች ዝርዝር በታሪክ መጽሐፍ ጽፈው ነበር፡፡ የኤልያሴብ የልጅ ልጅ የሆነው ዮሐና የካህናት ሁሉ መሪ እስከ ሆነበት ጊዜ ድረስ ያሉትን ክንዋኔዎች መዝግበው ነበር፡፡
24እነዚህ የሌዋውያን መሪዎች ነበሩ፡ ሐሽብያ፣ ሰራብያ፣ የቀድመኤል ልጅ ኢያሱ፣ እና ለእግዚአብሔር ውዳሴና ምስጋና ለማቅረብ ከእነርሱ ፊት ለፊት የቆሙ ወንድሞቸው፡፡ ይህንንም የእግዚአብሔር አገልጋይ የሆነው ንጉስ ዳዊት እንዳዘዛቸው እንደዚያው አደረጉ፡፡
25በር ጠባቀዎቹ፣ መታንያ፣ በቅቡቅያ፣ አብድዩ፣ ሜሱላም ጤልሞንና ዓቁብ ነበሩ፡፡
26አገረ ገዢው ነህምያ እና ካህኑ ዕዝራ በነበሩበት ወቅት፣ በኢዮሴዴቅ የልጅ ልጅ በኢያሱ ልጅ በዮቂም ዘመን ይህንን ሥራ ሰሩ፡፡ ዕዝራ የአይሁድን ህግጋትም በሚገባ ያውቅ ነበር፡፡
27የኢየሩሳሌምን ቅጥር ስንመርቅ፣ የሌዊን ትወልዶች ከሚኖሩባቸው የእስራኤል አካባቢዎች የቅጥሩን ምርቃት ያከብሩ ዘንድ ጠራናቸው፡፡ እነርሱም እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ብዙዎቹም በጽናጽልና፣ በበገና፣ በክራርና በሌሎች የክር ሙዚቃ መሳሪያዎች በመጫወት ይዘምሩ ነበር፡፡
28በህብረት ያለማቋረጥ የሚዘምሩትን የሌዊ ወገኖች ሰበሰብን፡፡ ከሰፈሩበት ከኢየሩሳሌም ዙሪያ ከነጦፋውያን መንደሮችና ከደቡብ ምስራቅ ኢየሩሳሌም ወደ መሃል ኢየሩሳሌም መጡ፡፡
29ከሰሜን ምስራቅ የኢየሩሳሌም ሶስት ቦታዎችም ከቤት ጌልገላ፣ ከጌባ አካባቢና ከዓዝሞት አካባቢ መጡ፡፡ መዘምራኑ ኢየሩሳሌም አቅራቢያ መንደሮችን መሰረቱ፡፡
30ካህናቱና የሌዊ ወገኖች ራሳቸውን በእግዚአብሔር ፊት የመንጻት ሥርዓት አደረጉ፣ ለህዝቡም ይህንኑ ስርዓት አደረጉ፣ ለከተማዋ መግቢያዎችና በመጨረሻም ለቅጥሩ ጭምር ስርዓቱን ፈጸሙ፡፡
31ከዚያ በቅጥሩ ጫፍ የይሁዳ መሪዎችን በአንድነት ሰበሰብኩ፣ እግዚአብሔርን እያገገኑ በቅጥሩ ላይ በከተማዋ ዙሪያ በሰልፍ እንዲዞሩ ሁለት ትላልቅ ቡድኖችን እዲመሩ ሾምኳቸው፡፡ በከተማይቱ ትይዩ ሲሆኑ፣ አንዱ ቡድን ወደ ቀኝ የቆሻሻ መጣያው በር ወደሚባለው ሄደ፡፡
32ከመሪዎቻቸው በኋላ ሆሻያና የይሁዳ እኩሌቶቹ መሪዎች ተሰለፉ፡፡
33ከእነርሱ በኋላ የተከተሏቸው ዓዛርያስ፣ ዕዝራ፣ ሜሱላም፣
34ይዳ፣ ብንያም፣ ሸማያ፣ ኤርምያስ፣
35እና መለከት የሚጫወቱ አንዳንድ የክህናቱ ወንዶች ልጆች ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የአሳፍ ትውልድ የሆኑት የዘኩር ልጅ፣ የሚካያ ልጅ፣ የመታንያ ልጅ፣ የሸማያ ልጅ፣ የዮናታን ልጅ ዘካርያስ ይገኙበታል፡፡
36ከእነዚህ በኋላ የሚገዙት የዘካርያስ ቤተሰቦች ሌሎች አባላት ነበሩ፡፡ ከእነዚህም ሸማያ፣ ኤዝርኤል፣ ሚላላይ፣ ጊላላይ፣ መዓይ፣ ናትናኤል፣ ይሁዳ፣ እና አናኒምን ያካትታል፡፡ ሁሉም ንጉስ ዳዊት ከብዙ አመታት አስቀድሞ ይጫወትበት የነበሩ እነዚያኑ አይነት የሙዚቃ መሳሪያዎችን ይጫወቱ ነበር፡፡ የአይሁድን ህግጋት በሚገባ የሚያውቀው ሰው ዕዝራ፣ ከዚህ ቡድን ፊት ሰልፉን ይመራ ነበር፡፡
37የፋፏቴ በር ሲደርሱ፣ ወደ ዳዊት ከተማ ደረጃዎችን ወጡ፣ የዳዊትን ቤተ መንግስት አልፈው፣ ከዚያ ውሃ በር አጠገብ ወደሚገኘው ቅጥር በከተማዋ ምስራቅ አቅጣጫ ሄዱ፡፡
38ለያህዌ ይዘምርና ያመሰግን የነበረው ሌላው የዝማሬ ቡድን በቅጥሩ ላይ በግራ በኩል በሰልፍ አለፈ፡፡ እኔ ከህዝቡ ከፊሉን ይዤ ተከተልኳቸው፡፡ እኛ የእቶን ግንቡን አልፈን ወደ ሰፊው ቅጥር አለፍን፡፡
39ከዚያ ተነስተን የኤፍሬምን በር፣ የጄቫናን በር፣ የአሣን በር፣ የሐናንኤልን ግንብ፣ የመቶ ወታደሮችን በር አልፈን ወደ በጎች በር ተጓዝን፡፡ ወደ ቤተ መቅደሱ በር ስንቃረብ ሰልፋችንን ጨረስን፡፡
40ሁለቱም ቡድኖች እየዘመሩና እርሱን እያመሰገኑ ወደ እግዚአብሔር ቤት ደረሱ፡፡ በዚያም በየስፍራቸው ቆሙ፡፡ እኔና ከእኔ ጋር የነበሩ መሪዎችም በስፍራችን ቆምን፡፡
41የእኔ ቡድን መለከት የሚነፉትን እነዚህን ካህናት ያጠቃልላል፡ ኤልያቄም፣ መዕሤያ፣ ሚንያሚን፣ ሚካያ፣ ኤልዮዔናይ፣ ዘካርያስ እና ሐናንያ፣
42ሌሎቹም መዕሤያ፣ ሸማያ፣ አልዓዛር፣ ኦዚ፣ ይሆሐናን፣ መልክያ፣ ኤላም እና ኤድር ናቸው፡፡ መሪያቸው ይዝራሕያ የሆነው መዘምራኑ ድምቸውን ከፍ አድርገው ዘመሩ፡፡
43ከቤተ መቅደሱ ውጭ ከሄድን በኋላ ብዙ መስዋዕቶችን አቀረብን፡፡ እኛ ወንዶች ሁላችን እግዚብሔር በጣም ደስተኞች ስላደረገን ደስ አለን፡፡ ሴቶቹና ልጆችም እንደዚሁ ደስ አላቸው፤ በሩቅ ያሉ ሰዎች እኛ በኢሩሳሌም ውስጥ ሆነን የምናሰማውን ድምጽ መስማት ይችሉ ነበር፡፡
44በዚያን ቀን ህዝቡ ለቤተ መቅደስ የሰጠውን ገንዘብ ለሚያስቀምጡበት ግምጃ ቤት ሀላፊ የሚሆኑ ወንዶች ተሾሙ፡፡ እነዚህ ሰዎች ለአስራትና በየአመቱ ለሚሰበሰበው እህልና ፍራፍሬ በኩራቶችም ሀላፊዎች ነበሩ፡፡ እነዚሁ ሰዎች ወደ ግምጃ ቤቶቹ ከእርሻዎች ምርት ለካህናቱና ለሌዊ ትውልዶች ያመጡ ነበር፡፡ ይህ የተደረገው የይሁዳ ሰዎች በያህዌ ቤት የሚያገለግሉ አገልጋዮች እንዲኖር ይፈልጉ ስለነበር ነው፡፡
45ካህናቱና ሌዋውያኑ ነገሮችን ለማንጻት፣ በማንጻት ስርዓቱ ያህዌን ያገለግሉ ነበር፤ መዘምራኑ በቤተ መቅደስ፣ እንዲሁም በር ጠባቂዎቹ ንጉስ ዳዊትና ልጁ ሰለሞን እንዲደረግ እንደ ደነገጉት ስራቸውን ያከናውኑ ነበር፡፡
46ከዳዊትና ከአሳፍ ዘመን አንስቶ፣ የዘማሪዎች መሪዎች ነበሩ፤ መዘምራኑም እግዚአብሔርን ለማወደስና ለማመስገን ይዘምሩ ነበር፡፡
47ዘሩባቤል በነበረበት አመታትና በአገረ ገዥው ነህምያ ዘመን፣ ዘማርያኑና የቤተ መቅደስ በር ጠባቂዎች በየዕለቱ የሚያስፈልጋቸውን ምግብ መላው እስራኤል ያወጣ ነበር፡፡ ህዝቡ ለሌዋውያን ኑሮ የሚያስፈልገውን ያስቀምጡላቸውና ሌዋውያኑ ደግሞ ከካህናቱ ቀዳሚ መሪ ለሆኑት ለአሮን ትውልዶች የሚያስፈልገውን ያስቀምጡላቸው ነበር፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።