መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ነህምያ 10

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በስምምቱ ላይ የፈረሙት የስማቸው ዝርዝር ይህ ነው፡
2በጽሁፉ ላይ የፈረሙ ካህናት እነዚህ ናቸው፡ ሠራያ፣ ዓዛርያስ፣ ኤርምያስ
3ፉስኮር፣ አማርያ፣ መልክያ፣
4ሐጡስ፣ ሰበንያ፣ መሉክ
5ካሪም፣ ሜሪምት፣ አብድዩ
6ዳንኤል፣ ጌንቶን፣ ባሮክ
7ሜሱላም፣ አብያ፣ ሚያሚን፣
8መዓዝያ፣ ቤልጋይ፣ ሸማያ እነዚህ ካህናት ነበሩ፡፡
9የፈረሙት ሌዋውያን ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡ የአዛንያ ልጅ ኢያሱ፣ ቤንዊ፣ ከኤንሐዳድ፣ ቀድምኤል፣
10ሰባንያ፣ ሆዲያ፣ ቆሊጣስ፣ ፌልያ፣ ሐናን
11ሚካ፣ ሪአብ፣ ሐሽብያ፣
12ዘኩርር ሰራብያ፣ ሰበንያ፣
13ሆዲያ፣ ባኒ፣ ብኒኑ፡፡
14በመጽሐፍ ጥቅሉ ላይ የፈረሙት የእስራኤል መሪዎች እነዚህ ነበሩ፡ ፋሮስ፣ ፈሐት፣ ሞዓብ፣ ኤላም፣ ዛቱዕ፣ ባኒ፡፡
15ቡኒ፣ ዓዝጋድ፣ ቤባይ፣
16አዶንያስ፣ በጉዋይ፣ ዓዲን
17አጤር፣ ሕዝቅያስ፣ ዓዙር፣
18ሆዲያ፣ ሐሱም፣ ቤሳይ
19ሐሪፍ፣ ዓናቶት፣ ኖባይ፣
20መግጲዓስ፣ ሜሱላም፣ ኤዘር
21ሜሴዜቤል፣ ሳዶቅ፣ ያጹአ፣
22ፈላጥያ፣ ሐናን፣ ዓናያ፣
23ሆሴዕ፣ ሐናንያ፣ አሱብ፣
24አሎኤስ፣ ፈልሃ፣ ሶቤቅ
25ሬሁም፣ ሐሰብና፣ መዕሤያ፣
26አኪያ፣ ሐናን፣ ዓናን፣
27ሙሉክ፣ ካሪምና በዓና፡፡
28ካህናቱን በር ጠባቂዎቹን፣ ዘማሪዎቹን እና የመቅደስ ሰራተኞቹን ጨምሮ የቀረው ሕዝብ የከበረ ስምምነት አደረጉ፡፡ እንደዚሁም አገራቸውን ለቀው የወጡትንና በእስራኤል ይኖሩ የነበሩትን ጎረቤቶቻቸው ከሆኑ ከሌሎች ህዝቦች ወንዶችን ሁሉ ጨመሩ፡፡ እነዚህ ወንዶች ከሚስቶቻቸውና የሚያደርጉትን ለይተው ከሚያውቁ ከፍ ካሉ ወንድና ሴት ልጆቻቸው ጋር ሆነው የእግዚአብሔርን ህግ እንደሚጠበቁ ቃል ገቡ፡፡
29ይህን የከበረ ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ሁሉም ከመሪዎቻቸው ጋር ተባበሩ፡፡ እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን ህግጋት ሁሉ ለመታዘዝ ተስማሙ፡፡ ያህዌ አምላካችን ያዘዘውን፣ ድንጋጌዎቹንና ትዕዛዛቱን ሁሉ ለመከተልና ለመፈፀም ተስማሙ፡፡ ተከታዩን ለማድረግ ቃል ገቡ፡፡
30“ሴቶች ልጆቻችን ያህዌን የማያመልኩትን የዚህ ምድር ሰዎች እንዲያገቡ አንሰጥም፣ ወንድ ልጆቻችን ሴት ልጆቻቸውን እንዲያገቡም አንፈቅድም፡፡
31ምድር የሚኖሩ የሌላ አገር ሰዎች በሰንበት ወይም በሌላ በተቀደሰ ቀን እህል ወይም ሌሎች ነገሮችን ሊሸጡልን ቢያመጡ፣ አንዳች ነገር አንገዛቸውም፡፡ እናም በየሰባት አመቱ አንዴ ለምድሪቱ እረፍት እንሰጣለን፤ በዚያን አንድ አመት ምንም አይነት እህል አንዘራም፤ እንዲሁም ለሌሎች አይሁዶች እዳቸውን ሁሉ እንሰርዛለን፡፡
32እንዲሁም እያንዳንዳችን ቤተ መቅደሱን ለሚያገለግሉና ለሚንከባከቡ በየአመቱ 5 ግራም ብር ለመክፈል ቃል ገባን፡፡
33በዚያ ገንዘብ እነዚህን ነገሮች መግዛት ይችላሉ፡ በእግዚአብሔር ፊት በገበታው ላይ የሚቀርብ ዳቦ፣ በእያንዳንዱ ቀን በመሰዊያው ላይ የሚቀርብ የእህል ቁርባን፣ በመሰዊያ ላይ ታርደው ሙሉ ለሙሉ የሚቃጠሉ እንስሳት፣ ለእግዚአብሔር በሰንበት የሚርቡ የተቀደሱ መስዋዕቶች እና የአዲስ ጨረቃ በዓልን ለማክበርና ለሌሎች በዓላት መስዋዕቶች፣ ለእስራኤል ህዝቦች ኃጢአት መስዋዕት የሚሆኑ እንስሳት፣ እና ማናቸውም የቤተመቅደሱን ሥራ ለመንከባከብ የሚያስፈልጉ ሌሎች ነገሮች መግዛት ይችላሉ፡፡
34በየአመቱ ካህናቱ፣ ካህናቱን የሚረዱ የሌዊ ትውልዶች እና የተቀረነው በእግዚአብሔር ሕግ እንደተፃፈው በዚያ አመት ከሌዋውያን መሃል የትኛው ቤተሰብ በአምካላችን በእግዚአብሔር ቤት መስዋዕቶቹን ለማቅረብ በመሰዊያው ላይ የሚነደውን እንጨት እንደሚያቀርቡ ለመወሰን እጣዎችን እንጥላለን፡፡
35በእያንዳንዱ አመት እያንዳንዱ ቤተሰብ በእርሻችን ካበቀልነውና ለምግብ ካጨድነው እንዲሁም በዚያ አመት ከፍራፍሬ ዛፎች የተገኘውን በኩራት መስዋዕት አድረገን ወደ ቤተ መቅደስ ለማምጣት ቃል እንገባለን፡፡
36የበኩር ወንድ ልጆችንና የላም፣ የበግና የፍየል በኩሮችን ለእግዚአብሔር መታሰበያ አድርገን ወደ እግዚአብሔር ቤት እናመጣለን፡፡ ማድረግ የሚገባን፣ በእግዚአብሔር ሕግጋት የተፃፈው ይህ ነው፡፡
37በየአመቱ ካመረትነው እህል ከበኩራቱ የተዘጋጀ ዱቄት ለካህናቱ ወደ ቤተ መቅደስ እናመጣለን፣ እንዲሁም ሌሎች የወይን፣ የወይራ ዘይትና የፍራፍሬ መስዋዕቶችንም ከበኩራቱ እናመጣለን፡፡ ካህናቱን ለሚረዱ የሌዊ ትውልዶች አስራቶችንም እናመጣለን፡፡
38የአሮን ትውልድ የሆነ አንድ ካህን፣ ከሌዋውያን ጋር ሆኖ አስራቶችን ሲሰበስቡ አብሮ ይገኛል፡፡ ከዚያ የሌዊ ትውልዶች ድርሻቸውን ይወስዳሉ፤ ህዝቡ ካመጣው ነገሮች አንድ አስረኛውን ይወስዱና በቤተ መቅደስ በግምጃ ቤት ያስቀምጣሉ፡፡
39የሌዊ ትወልዶችና አንዳንድ የእስራኤል ሰዎች በቤተ መቅደስ ለሚያገለግሉ የእህል፣ የወይን፣ እና የወይራ ዘይት ስጦታዎችን የተለያዩ መገልገያዎች ወደ ሚከማቹበት ግምጃ ቤቶች መውሰድ አለባቸው፡፡ በዚያን ጊዜ የሚያገለግሉ ካህናት፣ በር ጠባቂዎች፣ እና በቤተ መቅደስ የሚዘምሩ የዝማሬ ቡድን የሚኖሩበት ስፍራ ይህ ነው፡፡ “የአምላካችንን ቤተ መቅደስ ከመጠበቅ ቸል እንደማንል ቃል እንገባለን፡፡”
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።