መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ነህምያ 1

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እኔ የሐካልያ ልጅ ነህምያ ነኝ፡፡ ንጉስ አርጤክስስ የፋርስን መንግስት መግዛት በጀመረበት በሃያኛው አመት፣ ካሴሉ በተባለው ወር፤ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሼ ያደረግሁትን ይህን ነገር ጻፍሁ፡፡ እኔም በፋርስ ዋና ከተማ በሱሳ ነበርሁ፡፡
2ወንድሜ አናኒ እኔን ለማየት መጣ፡፡ እርሱና ሌሎች ጥቂት ሰዎች ከይሁዳ መጥተው ነበር፡፡ ከባቢሎን ምርኮ ስላመለጡ ጥቂት አይሁዶች፣ እና ስለ ኢየሩሳሌም ከተማ ጥያቄዎችን ጠየቅኳቸው፡፡
3እነርሱም እንዲህ አሉኝ፣ “ከምርኮ ያመለጡት አይሁዶች በዚያ በታላቅ መከራ እና ውርደት እየኖሩ ይገኛሉ፡፡ የከተማዋ ቅጥሮች በብዙ ስፍራዎች ተገፍተው ስለወደቁ ጠላት በቀላሉ ይገባባታል፣ ይህም ብቻ ሳይሆን፣ ነገር ግን የከተማዋ በሮች ሙሉ በሙሉ በእሳት ተቃጥለዋል፡፡”
4ይህንን በሰማሁ ጊዜ፣ ተቀምጬ አለቀስኩ፡፡ ለብዙ ቀናት በሰማይ ወዳለው አምላክ በለቅሶ ጾምኩ ጸለይኩ፡፡
5እንዲህ ስል ጸለይኩ፣ “ያህዌ፣ አንተ በሰማይ ያለህ አምላክ ነህ፡፡ አንተ ታላቅና አስደናቂ አምላክ ነህ፣ ለሚወዱህና ህግጋትህንና ትዕዛዛትህን ለሚጠብቁ ሁሉ የተቀደሰውን አብሮነትህንና ቃልኪዳንህን ትጠብቃለህ፡፡
6እባክህ አሁን ወደ እኔ ተመልከት ወደ ጸሎቴም አድምጥ፡፡ በቀንና በለሊት ለህዝብህ ለእስራኤል እጸልያለሁ፡፡ ኃጢአት መስራታችንን እናዘዛለሁ፡፡ እኔና ቤተሰቤ ጭምር አንተን በድለናል፡፡
7በጣም ክፉ አድርገናል፡፡ ከብዙ አመታት አስቀድሞ ባሪያህ ሙሴ አንተ እናደርገው ዘንድ ያዘዝከውን ህግጋትና ስርዓቶች ሰጥቶናል፣ እኛ ግን ህግጋትህን አልጠበቅንም፡፡
8እባክህ ለአገልጋይህ ለሙሴ የተናገርከውን አስብ፡፡ እንዲህ ብለሃል፣ ‘በፊቴ በታማኝነት እና በመታዘዝ ባትመላለሱ በአገራት መሃል እበትናችኋለሁ፡፡
9ነገር ግን ወደ እኔ ብትመለሱ እና ትዕዛዞቼን ብትጠብቁ፣ ወደ ሩቅ ሥፍራዎች ብትጋዙም እንኳን፣ ሁላችሁንም ሰብስቤ የእኔን ታላቅነትና ክብር ወደማሳያችሁ ወደዚህ ስፍራ እመልሳችኋለሁ፡፡
10እኛ የአንተ አገልጋዮች ነን፡፡ በታላቁ ሀይልህ ከባርነት ነጻ ያወጣኸን ህዝብ ነን፡፡ አንተ ያንን ያደረግከው ማድረግ የምትፈልገውን ሁሉ ማድረግ ስለምትችል ነው፡፡
11ያህዌ፣እባክህ የእኔን የአገልጋይህን ፀሎት ስማ፡፡ እባክህ በማንነትህና በስራህ አንተን ሲያከብሩ፣ ታላቅ ሀሴት የሚያደርጉትን የህዝብህን ሁሉ ጸሎት ስማ፡፡ ወደ ንጉሱ ፊት ስቀርብ መከናወንን እንድትሰጠኝ እጸልያለሁ፤ ለንጉሱ ጥያቄዬን ሳቀርብ ህይወቴ አደጋ ላይ እንዳትወድቅ ጠብቃት፡፡ ምህረትህ ይከተለኝ፡፡” እኔ ለንጉሱ እጅግ ከታመኑት አገልጋዮች አንዱ ሆኜ አገለግል ነበር፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።