መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

የማቴዎስ 6

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ሰዎች እንዲያዩአችሁ የጽድቅ ተግባሮቻችሁን በፊታቸው ከማከናወን ተጠንቀቁ፤ አለበለዚያ ከሰማይ አባታችሁ ዋጋ አታገኙም፡፡
2ስለዚህ አንተ ምጽዋት ስትሰጥ ግብዞች የሰዎችን ከበሬታ ለማግኘት በምኵራቦችና በጐዳና ላይ እንደሚያደርጉት፣ በፊትህ ጥሩንባ አታስነፋ፡፡ በእውነት እነግራችኋለሁ፣ ዋጋቸውን ተቀብለዋል፡፡
3አንተ ግን ምጽዋት ስትሰጥ፣ የቀኝ እጅህ የሚያደርገውን የግራ እጅህ እንዲያውቅ አታድርግ፤
4ይኸውም ምጽዋትህ በስውር የሚሰጥ እንዲሆንና ከዚያም በስውር የሚያይ አባትህ ዋጋህን እንዲከፍልህ ነው፡፡
5ስትጸልዩም እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ ግብዞች ሕዝብ እንዲያያቸው በምኵራቦችና በጐዳና ማእዘኖች ላይ ቆመው መጸለይ ይወዳሉና፡፡ በእውነት እነግራችኋለሁ፤ ዋጋቸውን ተቀብለዋል፡፡
6አንተ ግን ስትጸልይ ወደ ጓዳህ ገብተህ በር ዝጋና በስውር ወዳለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም ዋጋህን ይከፍልሃል፡፡
7ስትጸልይም አሕዛብ እንደሚያደርጉት ረብ የለሽ ድግግሞሽ አታድርግ፤ አሕዛብ በንግግራቸው ብዛት ምክንያት የሚሰሙ ይመስላቸዋልና፡፡
8ስለዚህ እንደ እነርሱ አትሁኑ፤ እናንተ ከመለመናችሁ በፊት ምን እንደሚያስፈልጋችሁ አባታችሁ ያውቃልና፡፡
9እንግዲህ እንደዚህ ጸልዩ፡- ‹በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ፣ ስምህ ይቀደስ፡
10መንግሥትህ ትምጣ፡፡ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች፣ እንዲሁ በምድር ትሁን፡፡
11የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፡፡
12በደላችንን ይቅር በለን፣ እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል፡፡
13ወደ ፈተና አታግባን፣ ከክፉው አድነን እንጂ፡፡› [መንግሥት፣ ኀይል፣ ክብርም የአንተ ነውና፣ ለዘላለም፣ አሜን፡፡]
14የሰዎችን ኀጢአት ይቅር ብትሉ፣ የሰማይ አባታችሁ እናንተንም ይቅር ይላችኋል፡፡
15የሰዎችን ኀጢአት ይቅር ካላላችሁ ግን፣ የሰማይ አባታችሁ የእናንተን ኀጢአት ይቅር አይልም፡፡
16ስትጾሙም ግብዞች እንደሚያደርጉት ፊታችሁን አታጠውልጉ፤ እንደ ጾመኛ ለመታየት ግብዞች ፊታቸውን ያጠወልጋሉና፡፡ በእውነት እነግራችኋለሁ፣ዋጋቸውን ተቀብለዋል፡፡
17አንተ ግን ስትጾም ራስህን ተቀባ፣ ፊትሀንም ታጠብ፣
18ይኸውም፣ በስውር ላለው የሰማይ አባትህ ብቻ እንጂ ለሰዎች ጾመኛ መስለህ እንዳትታይ ነው፡፡ በስውር የሚያይ የሰማይ አባትህም ዋጋህን ይከፍልሃል፡፡
19ብልና ዝገት በሚበላውና ሌቦችም ሰብረው በሚሰርቁበት በምድር ላይ ሀብትን ለራሳችሁ አታከማቹ፡፡
20ይልቁን ብልም ሆነ ዝገት በማያጠፋበት፣ ሌቦችም ሰብረው በማይሰርቁበት በሰማይ ሀብትን ለራሳችሁ አከማቹ፡፡
21ሀብታችሁ ባለበት ልባችሁም ይገኛልና፡፡
22ዐይን የሰውነት መብራት ነው፡፡ ስለሆነም ዐይንህ ጤናማ ከሆነ፣ መላ ሰውነትህ በብርሃን ይሞላል፡፡
23ዐይንህ ጤናማ ካልሆነ ግን፣ መላ ሰውነትህ ጨለማ ይሆናል፡፡ እንግዲህ በውስጥህ ያለው መብራት በእውነት ጨለማ ከሆነ፣ ጨለማው እንዴት ከባድ ይሆን
24! ሁለት ጌቶችን ማገልገል የሚችል ማንም የለም፤ አንዱን ይጠላል ሌላውንም ይወዳል፣ ወይም ለአንዱ ይታዘዛል ሌላውን ደግሞ ይንቃል፡፡ እግዚአብሔርንና ሀብትን ማገልገል አትችሉም፡፡
25ስለዚህ ስለ ሕይወታችሁ ምን እንደምትበሉ ወይም ምን እንደምትጠጡ፡- ወይም ስለ ሰውነታችሁ ምን እንደምትለብሱ አትጨነቁ፤ ሕይወት ከምግብ፣ ሰውነትስ ከልብስ አይበልጥምን?
26አየር ላይ የሚበርሩ ወፎችን ተመልከቱ! እነርሱ እህል አይዘሩም ወይም አያጭዱም፣ በጐተራም አያከማቹም፤ ይሁን እንጂ፣ የሰማይ አባታችሁ ይመግባቸዋል፡፡ ከወፎች ይልቅ እናንተ እጅግ የሚበልጥ ዋጋ ያላችሁ አይደላችሁምን?
27ከእናንተ መካከል ተጨንቆ በዕድሜው ላይ አንድ ቀን መጨመር የሚችል ይገኛልን?
28ስለ ልብስስ የምትጨነቁት ለምንድን ነው?
29ነገር ግን እነግራችኋለሁ፤ ሰሎሞን እንኳ በዚያ ክብሩ ሁሉ ከእነዚህ አበቦች እንደ አንዱ አልለበሰም፡፡
30እግዚአብሔር ዛሬ የሚታየውንና ነገ እሳት ውስጥ የሚጣለውን የሜዳ ሣር እንደዚህ ካለበሰ፣ እናንት እምነት የጐደላችሁ! እናንተንማ እንዴት እጅግ የበለጠ አያለብሳችሁም?
31እንግዲህ ‹ምን እንበላለን?› ወይም ‹ምን እንጠጣለን?› ወይም ‹ምን እንለብሳለን?› ብላችሁ አትጨነቁ፡፡
32አሕዛብ እነዚህን ሁሉ ይፈልጋሉና፤ የሰማይ አባታችሁ እነዚህ ሁሉ እንደሚያስፈልጓችሁ ያውቃል፡፡
33ነገር ግን በመጀመሪያ መንግሥቱንና ጽድቁን ፈልጉ፤ ከዚያም እነዚህ ሁሉ ይጨመሩላችኋል፡፡
34ስለዚህ ለነገ አትጨነቁ፤ ነገ ለራሱ ይጨነቃልና፡፡ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።