1የዳዊት ልጅ፣ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ መጽሐፍ፡፡
2አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ ይስሐቅም ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብም ይሁዳንና የይሁዳን ወንድሞች ወለደ፤
3ይሁዳም ከትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደ፤ ፋሬስም ኤስሮምን ወለደ፤ ኤስሮምም አራምን ወለደ፤
4አራምም አሚናዳብን ወለደ፤ አሚናዳብም ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፤
5ሰልሞንም ከረዐብ ቦዔዝን ወለደ፤ ቦዔዝም ከሩት ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፤ እሴይም ንጉሥ ዳዊትን ወለደ፡፡
6ንጉሥ ዳዊትም ከኦርዮ ሚስት ሰሎሞንን ወለደ፤
7ሰሎሞንም ሮበዓምን ወለደ፤ ሮብዓምም አብያን ወለደ፤ አብያም አሳፍን ወለደ፤
8አሳፍም ኢዮሣፍጥን ወለደ፤ ኢዮሣፍጥም ኢዮራምን ወለደ፤ ኢዮራምም ዖዝያንን ወለደ፤
9ዖዝያንም ኢዮአታምን ወለደ፤ ኢዮአታምም አካዝን ወለደ፤ አካዝም ሕዝቅያስን ወለደ፤
10ሕዝቅያስም ምናሴን ወለደ፤ ምናሴም አሞጽን ወለደ፤ አሞጽም ኢዮስያስን ወለደ፤
11ኢዮስያስም በባቢሎን ምርኮ ጊዜ ኢኮንያንንና ወንድሞቹን ወለደ፡፡
12ከባቢሎን ምርኮ በኋላም፣ ኢኮንያን ሰላትያልን ወለደ፤ ሰላትያልም ዘሩባቤልን ወለደ፤
13ዘሩባቤልም አብዩድን ወለደ፤ አብዩድም ኤልያቄምን ወለደ፤ ኤልያቄምም አዛርን ወለደ፤
14አዛርም ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅም አኪምን ወለደ፤ አኪምም ኤልዩድን ወለደ፤
15ኤልዩድም አልዓዛርን ወለደ፤ አልዓዛርም ማታንን ወለደ፤ ማታንም ያዕቆብን ወለደ፤
16ያዕቆብም ክርስቶስ ተብሎ የሚጠራውን ኢየሱስን የወለደችውን፣ የማርያምን ባል ዮሴፍን ወለደ፡፡
17ከአብርሃም እስከ ዳዊት፣ የነበሩት ትውልዶች ሁሉ ዐሥራ አራት፤ ከዳዊት እስከ ባቢሎን ምርኮ ድረስም እንደዚሁ ዐሥራ አራት፤ ከባቢሎን ምርኮ እስከ ክርስቶስ ድረስ የነበሩትም ዐሥራ አራት ትውልዶች ናቸው፡፡
18የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በሚከተለው መንገድ ተፈጸመ፡- እናቱ ማርያም ዮሴፍን ልታገባው ታጭታ ነበር፤ ነገር ግን ሳይጋቡ በመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች፡፡
19ዮሴፍ ጻድቅ ነበረ፤ በመሆኑም እርሷን በሕዝብ ፊት ሊያዋርዳት አልፈለገም፡፡ ስለዚህ ከእርሷ ጋር የነበረውን የዕጮኛነቱን ግንኙነት በምስጢር ለማቋረጥ ወሰነ፡፡
20ዮሴፍ ስለ እነዚህ ነገሮች እያሰበ ሳለ፣ የጌታ መልአክ፣ "የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፣ ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ፤ ምክንያቱም እርሷ የፀነሰችው በመንፈስ ቅዱስ ነው።
21እርሷ ወንድ ልጅ ትወልዳለች፣ ሕዝቡንም ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ብለህ ትጠራዋለህ" በማለት ተገለጠለት።
22-23ይህ ሁሉ የሆነው፣ "እነሆ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም ዐማኑኤል ብለው ይጠሩታል፤ ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ማለት ነው" ብሎ ጌታ በነቢይ የተናገረው እንዲፈጸም ነው።
24ዮሴፍ ከእንቅልፉ ነቃ፣ የጌታ መልአክ አዝዞት እንደ ነበረውም አደረገ፡- ማርያምን እን ደሚስቱ ወሰዳት፡፡
25(ይሁን እንጂ፣ ልጅ እስከምትወልድ ድረስ ከእርሷ ጋር ግንኙነት አላደረገም፡፡) የሕፃኑንም ስም ኢየሱስ አለው፡፡