መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ትንቢተ ሚልክያስ 1

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በሚልክያስ በኩል ወደ እስራኤል የመጣው የያህዌ ቃል ዐዋጅ ይህ ነው።
2“እኔ ወድጃችኋለሁ” ይላል ያህዌ። እናንተ ግን፣ “እንዴት ወደድኸን?” ብላችኋል? “ዔሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረምን? ያዕቆብን ወደድሁ
3ዔሳውን ግን ጠላሁ። ተራራውን ባድማ አደረግሁ፤ ርስቱንም የምድረ በዳ ቀበሮዎች መኖሪያ አደረግሁ።”
4ኤዶምያስ፣ “ብንደመሰስ እንኳ፣ የፈረሰውን መልስን እንሠራዋለን” ይል ይሆናል፤ የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ “እነርሱ የሠሩ ይሆናል፤ እኔ ግን መልሼ አፈርሳለሁ።” ሌሎች ሰዎች፣ “የዐመፀኞች አገር፤ ያህዌ ለዘላለም የተቆጣው ሕዝብ” በማለት የጠሯቸዋል።
5የገዛ ዓይኖቻችሁ ይህን ያያሉ። ከእስራኤል ዳርቻዎች ወዲያ እንኳ ያህዌ ትልቅ ነው ትላላችሁ”
6ለእናንተ ስሜን ለታቃልሉ ካህናት “ልጅ አባቱን ያከብራል፤ አገልጋይም ጌታውን ያከብራል። እኔ አባት ከሆንሁ፣ ታዲያ፣ ክብሬ የታለ? ጌታስ ከሆንሁ፣ መፈራቴ የታለ? ይላል የሰራዊት ጌታ ያህዌ። እናንተ ግን፣ “ስምህን ያቃለልነው በመንድነው?” ብላችኋል።
7መሠዊያዬ ላይ የረከሰ ምግብ በማቅረብ ነው። እናንተ፣ “ያረከስንህ በምንድነው” ብላችኋል። የእግዚአብሔር ገበታ የተናቀ ነው በማለታችሁ ነው።
8የታወረውን እንስሳ መሥዋዕት ማቅረብ፣ በደል አይደለም? አንካሳውንና በሽተኛውን መሥዋዕት ማቅረብስ በደል አይደለም? እስቲ ያንኑ ለባለሥልጣን አቅርቡት፣ ይቀበላችኋልን? ወይስ በእናንተ ደስ ይለዋልን?” ይላል የሰራዊት ጌታ ያህዌ።
9አሁን ግን እንዲራራልን የእግዚአብሔርን ፊት ፈልጉ። ለመሆኑ፣ እንዲህ ዓይነቱን መሥዋዕት ይዛችሁ ስትቀርቡ እርሱ ይቀበላችኋልን? ይላል የሰራዊት ጌታ ያህዌ።
10መሠዊያዬ ላይ ከንቱ እሳት እንዳታነዱ፣ ምነው ከእናንተ አንዱ የቤተመቅደሱን ደጆች በዘጋ ኖሮ! በእናንተ ደስ አልሰኝም፤ ከእጃችሁም ማንኛውንም መሥዋዕት አልቀበልም ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ።
11ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያው ድረስ በሕዝቦች መካከል ስሜ ታላው ይሆናል፤ በየቦታው ሁሉ በስሜ ዕጣንና ንጹሕ መሥዋዕት ይቀርባል። በሕዝቦች መካከል ስሜ ታላቅ ይሆናል” የሠራዊት ጌታ ያህዌ።
12እናንተ ግን “የእግዚአብሔር ማዕድ የረከሰ ነው በማለት ታረክሱታላችሁ፤ ምግቡም የተናቀ ነው” በማለት ታቃልሉታላችሁ።
13ደግሞም፣ “ይህ ድካም ነው” በማለት ፣ “በንቀት ጢቅ አላችሁበት” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ። በዱር እንስሳ ተወስዶ የነበረውን ወይም አንካሳና በሽተኛውን መሥዋዕት ለማቅረብ ታመጣላችሁ። ታዲያ፣ ይህን ከእናንተ እጅ ልቀበል?” ይላል ያህዌ።
14“መንጋው ውስጥ ያለውን ተባዕት በግ መሥዋዕት ለማቅረብ ተስሎ ሳለ ለእኔ ነውር ያለበትን እንስሳ የሚያቀርብ አታላይ ርጉም ይሁን! እኔ’ኮ ታላቅ ንጉሥ ነኝ፤ ስሜም በአሕዛብ መካከል ይከበራል” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።