1ያህዌ ሙሴን ተናገረው እንዲህም አለ፣
2“ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፣ ‹አንድ ሰው ለያህዌ ሰውን ለመስጠት የተለየ ስዕለት ቢሳል ተመጣጣን ዋጋ ለመክፈል ተከታዮን ዋጋዎች ተጠቀም፡፡
3ከዚያ እስከ ስልሳ አመት ዕድሜ ላለው ወንድ መደበኛው ዋጋ በቤ መቅደሱ ሰቅል መለኪያ ሃምሳ የብር ሰቅሎች ይሁን፡፡
4ለተመሳሳይ ዕድሜ ክልል ለሴቷ መደበኛው ዋጋ ሰላሳ ሰቅሎች ይሁን፡፡
5ከአምስት አመት እስከ ሀያ አመት ዕድሜ ለወንድ መደበኛው ዋጋ ሀያ ሰቅሎች ይሁን፣ ለሴቷ አስር ሰቅሎች ነው፡፡
6ከአንድ ወር ዕድሜ እስከ አምስት አመት ለወንድ መደበኛው ዋጋ አምስት የብር ሰቅሎች ይሁን፣ ለሴት ሶስት የብር ሰቅሎች ነው፡፡
7ከስልሳ አመት በላይ ለወንድ መደበኛው ዋጋ አስራ አምስት ሰቅሎች፣ ለሴት አስር ሰቅሎች ይሁን፡፡
8ነገር ግን ስዕለቱን የገባው ሰው መደበኛውን ዋጋ መክፈል ባይችል፣ በስለት የተሰጠው ሰው ወደ ካህኑ ይቅረብ፣ ካህኑም ያንን ሰው የተሳለው ሰው ሊከፍል በሚችል ዋጋ ይተምነዋል።
9አንድ ሰው ለያህዌ እንስሳ መሰዋት ቢፈልግ፣ ያህዌ ያንን ቢቀበል፣ ከዚያ ያ እንስሳ ለእርሱ ይለያል፡፡
10ሰውዬው እንዲህ ያለውን እንስሳ መለወጥ ወይም መቀየር የለበትም፣ መልካሙን በመጥፎው ወይም መጥፎውን በመልካሙ አይቀይርም፡፡ አንዱን እንስሳ በሌላው ቢለውጥ፣ ያ እንስሳና የተለወጠው ሁለቱም ንጹህ ይሆናሉ፡፡
11ሆኖም፣ ሰውዬው ለያህዌ ሊሰጥ የተሳለው ንጹህ ካልሆነ ስለዚህ ምክንያት ያህዌ ያንን አይቀበልም፣ ከዚያ ሰውዬው እንስሳውን ወደ ካህኑ ማምጣት አለበት፡፡
12ካህኑ በገበያው የእንስሳ ዋጋ ይተምነዋል፡፡ ማናቸውም ካህኑ ለእንስሳው የሰጠው ዋጋ፣ ያ የእንስሳው ዋጋ ይሆናል፡፡
13እናም ባለቤቱ እንስሳውን ሊዋጅ ቢፈልግ፣ በሚዋጅበት ዋጋ ላይ አንድ አምስተኛውን ጨምሮ ይዋጀው፡፡
14አንድ ሰው ቤቱን ለያህዌ መቀደስ ሲፈልግ፣ ካህኑ የቤቱን ዋጋ ይተምናል፡፡ ማናቸውም ካህኑ የተመነው ዋጋ ያ የዚያ ቤት ዋጋ ነው፡፡
15ነገር ግን ባለቤቱ ቤቱን ቢለይና በኋላ ሊዋጀው ቢፈልግግ በሚዋጅበት ዋጋ ላይ አንድ አመስተና ይጨመር፣ እናም ከዚያ እንደገና የእርሱ ይሆናል፡፡
16አንድ ሰው ከመሬቱ ለያህዌ ለመለየት ቢፈልግ፣ የመሬቱ ዋጋ ግምት ለመዝራት በሚያስፈልገው ፍሬ መጠን ይተመናል፡፡ አንድ ሆሜር መስፈሪያ ገብስ ሃምሳ የብር ሰቅሎች ያወጣል፡፡
17እርሻውን በኢዮቤልዩ አመት ቢለይ፣ የተገመተው ዋጋ ይፀናል፡፡
18እርሻውን ከኢዮቤልዩ በኋላ ቢለይ ግን፣ ካህኑ የእርሻ መሬቱን ዋጋ እስከ ቀጣዩ የኢዮቤልዩ አመት ድረስ ባሉ አመታት ቁጥር ያሰላና የተገመተው ዋጋ ይቀነሳል፡፡
19እርሻውን የለየው ሰው ሊዋጀው ቢፈልግ፣ በተገመተው ዋጋ ላይ አንድ አምስተኛ ይጨምራ፣ እናም መሬቱ ተመልሶ የእርሱ ይሆናል፡፡
20እርሻውን ካልዋጀ ወይም ለሌላ ሰው ሸጦት ከሆነ፣ ከዚያ በኋላ ተመልሶ ሊዋጅ አይችልም፡፡
21ይልቁንም፣ እርሾው፣ በኢዮቤልዩ ተመልሶ ሲለቀቅ ሙሉ ለሙሉ ለያህዌ እንደተሰተ እርሻ ሁሉ ለያህዌ ቅዱስ ስጦታ ይሆናል፡፡ የካህናቱ ንብረት ይሆናል፡፡
22አንድ ሰው የገዛውን መሬት ለያዌ ቢለይ፣ ነገር ግን መሬቱ ከሰውዬው ቤተሰቦች መሬት ውስጥ ባይሆን፣
23ካህኑ የእርሻውን ዋጋ እስ ኢዮቤልዩ አመት ድረስ ባለው ጊዜ መተን ይተምናል፣ ሰውዬውም ዋጋውን በዚያ ቀን ለያህዌ ቅዱስ ስጦታ አድርጎ ይከፍላል፡፡
24በኢዮቤልዮ አመት፣ እርሻው ከገዛው ሰው ተወስዶ ወደ መሬቱ የቀድሞ ባለቤት ይመለሳል፡፡
25የሚተመኑ ዋጋዎች ሁሉ በመቅደሱ ሰቅል ዋጋ ሊተመኑ ይገባል፡፤ ሃያ ጌራ ከአንድ ሰቅል ጋር እኩል ነው፡፡
26ከእንስሳት በመጀመሪያ የሚወለደው ግን አስቀድሞም ቢሆነ የያህዌ ነው፣ ማንም ሰው ሊቀድሰው አይችልም በሬም ይሁን በግ የያህዌ ነው፣ ማንም ሰው ሊቀድሰው አይችልም በሬም ይሁን በግ የያህዌ ነው
27ንጹህ ያልሆነ እንስሳ ከሆነ፣ ባለቤቱ በተመገተው ዋጋ መልሶ ይግዛውው ደግሞም ከዋጋው በላይ አንድ አምስተኛ ይጨምርበት፡፡ እንስሳው ካልተዋጀ፣ በተተመነው ዋጋ ይሸጥ፡፡
28ሆኖም፣ አንድ ሰው ለያህዌ ከለየው ሰውም ሆነ ወይም እንስሳ፣ ወይም የቤተሰቡ ርዕስት ምንም ነገር አይሽጥ ወይም አይዋጅ ማናቸውም የተለየ ነገር ለያህዌ ቅዱስ ነው፡፡
29እንዲጠፋ ለተለየ ሰው ምንም መዋጃ አይከፈልለትም፡፡ ያ ሰው መገደል አለበት፡፡
30አስራት ሁሉ፣ በምድሪቱ ላይ የበቀለ ሰብልም ሆነ ወይም የዛፍ ፍሬ የያህዌ ነው፡፡ ለያህዌ የተቀደሰ ነው፡፡
31አንድ ሰው ከአስራቱ አንዳች ቢዋጅ፣ በዋጋው ላይ አንድ አምስተኛ ይቸምር፡፡
32ከመንጋ ወይም ከከብት አስራት ሁሉ፣ ከእረኛው በትር ስር የሚያልፍ ሁሉ፣ ከአስር አንዱ ለያህዌ ይለይ፡፡
33እረኛው የተሸለውን ወይም የከፋውን እንስሳ አይፈልግም፣ ደግሞም አንዱን በሌላው አይተካ፡፡ ቢለውጠው እኗን፣ የተለወጠውና የሚለወጠው ሁለቱም የተቀደሱ ይሆናሉ፡፡ ሊዋጅ አይችልም፡፡”
34ያህዌ በሲና ተራራ ለሙሴ የሰጣቸው ለእስራኤላውያን የተሰጡ ትእዛዛት እነዚህ ናቸው፡፡