መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘሌዋውያን 26

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1“እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፤ ጣኦታትን አታብጁ፣ የተቀረጸ ምስልንም አታቁሙ፣ ወይም ለአምልኮ የድንጋይ አምዶችን አታቁሙ፣ እንደዚሁም ልትሰግዱላቸው ማናቸውንም የቀረፀ የድንጋይ ምስል በምድራችሁ አታድርጉ፡፡
2ሰንበቴን ጠብቁ የተቀደሰውን ስፍራዬን አክብሩ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
3በህጌ ብትኖሩና ትዕዛዛቴን ብትጠብቁ ብትታዘዟቸውም፣
4ዝናብን በወቅቱ እሰጣችኋለሁ፤ ምድር ምርቷን ትሰጣችኋለች፣ የሜዳ ዛፎችም ፍሬያቸውን ይሰጧችኋል፡፡
5የወቃችሁት እስከ ወይን አዝመራችሁ ድረስ ይቆያል፣ የወይን ፍሬ አዝመራችሁም እስከምትዘሩበት ወቅት ድረስ ይቆያል፡፡ እንጀራችሁን በምድሪቱ ቤታችን በሰራችሁበት ጠግባችሁ ትበላላችሁ በእረፍት ትኖራላችሁ፡፡
6በምድሪቱ ሰላምን እሰጣለሁ፣ ምንም ነገር ሳያስፈራችሁ ተዘልላችሁ ትቀመጣላችሁ፡፡ ከምድሪቱ አደገኛ እንስሳትን አስወጣለሁ፣ በምድራች ሰይፍ አያልፍም፡፡
7ጠላቶቻችሁን ታሳድዳላችሁ፣ እነርሱም በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ፡፡
8ከእናንተ አምስታችሁ መቶውን ታሳድዳላችሁ፣ ከእናንተ መቶው አስር ሺኅ ያሳድዳል፤ ጠላቶቻች በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ፡፡
9ወደ እናንተ በሞገስ እመለከታለሁ፣ ፍሬያማም አደርጋችኋለሁ፣ አበዛችሁማለሁ፤ ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳኔን አደርጋለሁ፡፡
10ለረጅም ጊዜ የተከማቸ እህል ትበላላችሁ፡፡ ለአዲሱ ምርታችሁ ስፍራ ስለሚያስፈልጋችሁ የተከማቸውን እህል ታወጣላችሁ፡፡
11ማደሪያዬን በመካከላችሁ አደርጋለሁ፣ እኔም እናንተን አልጣላችሁም፡፡
12በመካከላችሁ እሆናለሁ አምላካችሁም እሆናለሁ፣ እናንተም የእኔ ህዝብ ትሆናላችሁ፡፡
13ከግብጽ ምድር ያወጣኋቸው፣ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፣ ስለዚህም የእነርሱ ባሮች አትሆኑም፡፡ የቀንበራችሁን ብረት ሰብሬያሁ፣ ቀና ብላችሁ እንድትሄዱ አድርጌያለሁ፡፡
14ነገር ግን እኔን ባትሰሙኝ፣ እነዚህን ትዕዛዛቴን ሁሉ ባትጠብቁ፣
15ትዕዛዛቴን ብትተዉና ህግጋቴን ብትጠሉ፣ እናም ትዕዛዞቼን ሁሉ ሳትፈጽሙ ብትቀሩ፣ ነገር ግን ቃልኪዳኔን ብታፈርሱ
16እነዚህን ነገሮች ብታደርጉ፣ እኔም ይህን አደርግባችኋለሁ፡ ፍርሃትን እሰድባችኋለሁ፣ ዐይኖችንና ሕይወታችሁን የሚያጠፋ በሽታና ትሳት አደርስባችኋለሁ፡፡ በከንቱ ትዘራላችሁ፣ ምክንያቱም ፍሬያቸውን ጠላቶቻችሁ ይበሉታል፡፡
17ፊቴን በጠላትነት ወደ እናንተ እመልሳለሁ፣ ከጠላቶቻችሁ ሀይል በታች ትወድቃላችሁ፡፡ የሚጠሏችሁ ሰዎች ይገዙዋችኋል፣ ማንም ሳያሳድዳችሁ እንኳን ትሸሻላችሁ፡፡
18ትዕዛዛቴን ባትሰሙ፣ ከዚህ በኋላ ስለ ሀጢአታችሁ ሰባት እጥፍ እቀጣችኋለሁ፡፡
19የትእቢታችሁን ኃይል እሰብራለሁ፡፡ ሰማይን በላያችሁ እንደ ብረት ምድራችሁንም እንደ ናስ አደርጋለሁ፡፡
20ብርታታችሁ ለአንዳች ነገር አይጠቅምም፣ ምክንያቱም ምድራችሁ አዝመራዋን አትሰጥም፣ በምድራችሁ ዛፎቻችሁ ፍሬያቸውን አይሰጡም፡፡
21በእኔ ላይ ጠላት ሆናችሁ ብትመላለሱና ከኃጢአታችሁ በላይ እኔን ባትሰሙኝ፣ በእናንተ ላይ ሰባት ዕጥፍ ድንጋጤ አመጣለሁ፡፡
22ልጆቻችን የሚነጥቁ፣ ከብቶቻችሁን የሚያጠፉ፣ እናንተን በቁጥር ጥቂት የሚያደርጉ አደገኛ አውሬዎችን እሰድባችኋሉሁ፡፡ ስለዚህም ጎዳናዎቻችሁ በረሃ ይሆናሉ፡፡
23በእነዚህ ሁሉ ነገሮች ትምህርቶቼን ባትሰሙ ነገር ግን በእኔ ላይ ጠላት ሆናችሁ መመላለሳችሁን ብትቀጥሉ፣
24እኔም በእናንተ ላይ ጠላት እሆናለሁ፡፡ እኔ ራሴ በሀጢአቶቻችሁ ሰባት እጥፍ እቀጣችኋለሁ፡፡
25ቃልኪዳን በማፍረሳችሁ በእናንተ ላይ የበቀል ሰይፍ አመጣለሁ፡፡ በከተሞቻችሁ ውስጥ በአንድነት ትሰበሰባላችሁ፣ በዚያም በማህላችሁ በሽታን እልካለሁ፣ እናንተም በጠላቶቻችሁ ሀይል ትሸነፋላችሁ፡፡
26የምግብ አቅርቦታችሁን ስቆርጥ፣ አስር ሴቶች በአንድ ምድጃ እንጀራችሁን ይጋግራሉ፣ እንጀራችሁንም በሚዛን ያካፍሏችኋል፡፡ ትበላላችሁ ነገር ግን አትጠግቡም፡፡
27እነዚህ ነገሮች ሁሉ ሆነው ባትሰሙት፣ ነገር ግን በእኔ ላይ በጠላትነት መመላሳችሁን ብትቀጥሉ፣
28እኔ በቁጣ እመጣባችኋለሁ፣ በኃጢአቶቻችሁ ሰባት እጥፍ እቀጣችኋለሁ፡፡
29ወንድ ልጆቻችሁን ስጋና የሴት ልጆቻችሁን ስጋ ትበላላችሁ፡፡
30የአምልኮ ሥፍራችሁን አጠፋለሁ፣ የእጣን መሰዊያዎቻችሁን እቆርጣለሁ፣ በድኖቻችሁን በድን በሆኑ በጣኦቶቻችሁ ላይ እጥላለሁ፣ ደግሞም እኔ ራሴ እጸየፋችኋለሁ፡፡
31ከተሞቻችሁን ፍርስራሽ አደርጋለሁ የተቀደሱ ቦታዎቻችሁን አጠፋለሁ፡፡ በመስዋዕቶቻችሁ መዓዛ ደስ አልሰንም፡፡
32ምድሪቱን አጠፋለሁ፡፡ በዚያ የሚኖሩ ጠላቶቻችሁ በጥፋቱ ይደነግጣሉ፡፡
33በአገራት መሃል እበትናችኋለሁ፣ ሰይፌን መዝዤ አሳድዳችኋለሁ፡፡ ምድራችሁ ባድማ ትሆናለች፣ ከተሞቻችሁም ፍርስራሽ ይሆናሉ፡፡
34ከዚያም ምድሪቱ ባድማ ሆኖ እስከቆየች ድረስና እናንተ በጠላቶቻችሁ ምድር እስከቆያችሁ ድረስ የሰንበት ዕረፍቷን ታገኛለች፡፡ በነዚያ ጊዜያት፣ ምድሪቱ ታርፋለች ሰንበቶቿንም ታገኛለች፡፡
35ፍርስራሽ ሆና እስከቆየች ድረስስ እረፍት ይሆንላታል፣ እናንተ በውስጧ ስትኖሩ በሰንበቶቻችሁ ያላገኘችውን ዕረፍት ታገኛች፡፡
36እናንተ በጠላቶቻችሁ ምድር በቀራችሁት ላይ በልቦቻችሁ ውስጥ ፍርሃት እሰዳለሁ፣ ስለዚህም የቅጠል ኮሰሽታ እንኳን ያስደነግጣችኋል፣ ከሰይፍ እንደሚሸሽ ትሆናላች፡፡ ማንም ሳያሳድዳችሁ ትወድቃላች፡፡
37ማንም ባያሳድዳችሁም እንኳን ከሰይፍ እንደሚሸሽ ሰው አንዳችሁ በሌላችሁ ላይ ትደነቃቀፋላችሁ፡፡ በጠላቶቻችሁ ፊት ለመቆም ምንም ሀይል አይኖራችሁም፡፡
38ከአገራት መሀል ተለይታችሁ ትጠፋላችሁ፣ የጠላቶቻችሁ ምድር ራሱ በፍርሃት ይሞላችኋል፡፡
39ከእናንተ መሃል የቀሩት በዚያ በጠላቶቻችሁ ምድር በሀጢአቶቻቸው ይጠፋሉ፣ እንዲሁም በአባቶቻቸው ሀጢአቶች ምክንያት ይጠፋሉ፡፡
40ሆኖም የእነርሱንና የአባቶቻቸውን ሀጢአቶች ቢናዘዙ፣ ለእኔ ታማኝ ካልሆኑበት ክህደታቸው ቢመለሱ፣ ከእኔ ጋር ተላት ከሆኑበት አካሄዳቸው ቢመለሱ
41እኔ በእነርሱ ላይ እንድነሳ ካደረገንና ለጠላቶቸው ምድር አሳልፌ እንድሰጣቸው ካደረገ አካሄዳቸው ቢመለሱ ያልተገረዙ ልቦቻቸው ዝቅ ቢሉ፣ እናም በሀጢአቶቻቸው የደረሰባቸውን ቅጣታቸውን ቢቀበሉ፣
42ከያዕቆብ ጋር የገባሁትን ኪዳኔን አስባለሁ፤ እንዲሁም፣ ምድሪቱን አስባለሁ፡፡
43ምድሪቱ ለቀዋት ስለሄዱ ባዶ ትቀራለች፣ ስለዚህ ካለእነርሱ በተተወችበት ጊዜ በሰንበቶቿ ታርፋለች፡፡ እነርሱ በሀጢአታቸው ቅጣታቸውን ይቀበላሉ ምክንያቱም እነርሱ ራሳቸው ስርአቴን ትተዋል ህግጋቴንም ጠልተዋል፡፡
44ሆኖም ከዚህ ሁሉ ባሻገር፣ በጠላቶቸው ምድር ውስጥ ሲሆኑ፣ እኔ አልተዋቸውም ሙሉ በሙሉ እስካጠፋቸውም ድረስ አልጠላቸውም፣ ደግሞም ከእነርሱ ጋር የገባሁትን ኪዳኔን አልረሳም፣ እኔ አምላካቸው ነኝ፡፡
45ነገር ግን ስለ እነርሱ ስል አምላካቸው እሆን ዘንድ አሕዛብ እያዩ ከግብጽ ምድር ካወጣኋቸው ከአባቶቻቸው ጋር የገባሁትን ኪዳኔን አስባሁ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡”
46በሙሴ በኩል ያህዌ በሲና ተራራ ላይ በራሱና በእስራኤል ህዝብ መሃል ያደረጋቸው ትዕዛዛት፣ ደንቦችና ህጎች እነዚህ ናቸው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።