1እግዚአብሔር ሆይ የሆነብንን አስብ። እፍረታችንን እይ፥ተመልከትም።
2ርስታችን ለእንግዶች፥ ቤቶቻችን ለባዕዳን ታልፈው ተሰጡ።
3አባቶች ስለሌሉ፥ እናቶቻችንም መበለቶች ስለሆኑ ወላጅ አልባ ሆን።
4ለመጠጣት ውኃችን የብር ዋጋ ጠየቀ፥ የገዛ እንጨታችንም ተሸጠል ን።
5ጠላቶቻችን ያሳድዱናል፥ አንገታችንም ላይ ደርሰዋል። እኛ ደክመናል፥ ዕረፍትም የለንም።
6ምግብ ለመጥገብ ለግብፃውያንና ለአሦራውያን እጃችንን ሰጠን።
7አባቶቻችን ኃጢአት ሠሩ፤ እነርሱ የሉም፥እኛ ግን ኃጢአታቸውን ተሸከምን።
8ባሮች ይገዙናል፥ ከእጃቸውም የሚያድነን የለም።
9ከምድረ በዳው ሰይፍ የተነሳ እንጀራ ለማግኘት በሕይወታችን ፈረድን።
10ቆዳችን እንደ ምድጃ ሆኖአል፥ ከረሃቡ ትኩሳት የተነሳ ተቃጥሎአል።
11በጽዮን ሴቶችን፥ በይሁዳ ከተሞች ደናግላንን ደፈሩ።
12በገዛ እጆቻቸው ልዑላኑን ሰቀሉ፥ሽማግሌዎችንም አላከበሩም።
13ኃያላን ወንዶችን ወደ ወፍጮ ቤት አመጡአቸው፥ ወጣት ወንዶችም ከእንጨት በታች ተንገዳግዱ።
14ሽማግሌዎችን ከከተማይቱ ደጅ፥ ኃያላን ወንዶችንም ከዘፈናቸው አስወገዷቸው።
15የልባችን ደስታ ተወግዶአል፥ ጭፈራችንም ወደ ለቅሶ ተለውጦአል።
16አክሊል ከራሳችን ወድቋል! ወዮልን! ኃጢአት ሠርተናልና!
17ልባችን ታምሞአል፥ዓይኖቻችንም ፈዝዘዋል፤
18ምክንያቱም ባድማ በሆነችው በጽዮን ተራራ ላይ ቀበሮዎች ፈንጭተውበታልና።
19ነገር ግን አንተ እግዚአብሔር ነህ፤ ለዘላለም ትገዛለህ፥ ዙፋንህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው።
20ስለ ምን ለዘላለም ትረሳናለህ? ለረዥም ዘመናትስ ትተወናለህን?
21እግዚአብሔር ሆይ፥ወደ አንተ መልሰን፥እኛም ንስሐ እንገባልን። ቀኖቻችንን እንደ ጥንቱ ዘመን አድስ፥
22ፈጽመህ ካልጣልከንና እጅግም ካልተቆጣኽን።