መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሰቆቃው ኤርሚያስ 1

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በሰዎች ተሞልታ የነበረችው ከተማ አሁን ፈጽማ ብቻዋን ተቀምጣለች! ኃያል የነበረችው አገር እንደ መበለት ሆናለች! በሕዝቦች መካከል እንደ ልዕልት ነበረች፥ አሁን ግን በባርነት ውስጥ ወድቃለች!
2በሌሊት ታለቅሳለች፥ታነባለችም፤እንባዎቿም ጉንጮቿን ከድነዋል። ከፍቅረኞቿ መካከል የሚያጽናናት የለም። ጓድኞቿ ሁሉ አሳልፈው ሰጧት። ጠላቶቿም ሆነዋል።
3ከድህነቱና ከመከራዉ የተነሳ ይሁዳ ወደ ምርኮ ሄደች። በሕዝቦች መካከል ኖረች፥ ዕረፍትንም አላገኘችም። በጭንቀቷ ጊዜ አሳዳጆቿ ሁሉ በረቱባት።
4ወደ ተቀጠሩት በዓላት የሚመጣ የለምና የጽዮን መንገዶች ያለቅሳሉ። ደጆቿ ሁሉ ባዶ ናችው። ካህናቶቿ ይቃትታሉ። ደናግሎቿ ሐዘንተኞች ናቸዉ፥እራስዋም በፍጹም ጭንቀት ውስጥ አለች።
5ባላንጣዎቿ ጌቶቿ ሆኑ፥ጠላቶቿ በለጸጉ። ስለ ብዙ ኃጢአቷ እግዚአብሔር መከራን አመጣባት። ልጆቿ ለጠላቷ ተማርከው ወደ ግዞት ሄዱ።
6የጽዮን ሴት ልጅ ውበቷ ተለያት። ልዑላኖቿ መሰማሪያ እንዳላገኙ አጋዘኖች ሆኑ፥ በአሳዳጆቻቸው ፊት በድካም ሄዱ።
7በመከራዋና ቤት አልባ በሆነችባቸው ቀናት፥ ኢየሩሳሌም በቀደሙት ቀናት የነበሯትን የከበሩ ነገሮች ታስባለች፤ሕዝቦቿ በጠላት እጅ በወደቁ ጊዜ ማንም የረዳት አልነበረም። ጠላቶቿ ተመለከቷት፥ በጥፋቷም ሳቁ።
8ኢየሩሳሌም ታላቅ ኃጢአት ሠርታለች፥ ስለዚህ እንደ አደፈ ነገር ተንቃለች። ዕርቃናዋን ከተመለከቱበት ጊዜ አንስቶ ያከበሯት ሁሉ ናቋት። ታጉተመትማለች፥ ዘወር ለማለትም ትሞክራላች።
9ከቀሚሷ በታች አድፋለች። የወደፊቷን አላሰበችም። አወዳደቋ አስፈሪ ነበር። የሚያጽናት ማንም አልነበረም። «እግዚአብሔር ሆይ፥ መከራዬን ተመልከት፥ ጠላት እጅግ ታላቅ ሆኖአልና» እያለች ትጮኻለች!።
10ጠላት በከበረ ነገሯ ሁሉ ላይ እጁን አደረገ። ወደ ጉባዔህ እንዳይገቡ አዝዘህ የነበረ ቢሆንም እንኳን፥ ሕዝቦች ወደ መቅደሷ ሲገቡ አየች።
11ሕዝቦቿ ሁሉ ምግብ እየፈለጉ ይጮኻሉ። ሕይወታቸውን ለማቆየት የከበረ ኃብታቸውን ስለ ምግብ ይሰጣሉ። የማልጠቀም ሆኟለሁና፥ እግዚአብሔር ሆይ ተመልከት አስበኝም።
12እናንተ መንገደኞች ሁሉ ይህ ለእናንተ ምንም አይደለምን? እግዚአብሔር እኔን መቅጣት ከጀመረበት ከጽኑ ቁጣው ቀን አንስቶ፥ የደረሰብኝን ሐዘን የሚመስል የማንም የሌላ ሰው ሐዘን ካለ ተመልከቱ፥ እዩም።
13ወደ ዉስጥ ወደ አጥንቶቼ ከላይ እሳት ላከ፥ አሸነፋቸዉም። ለእግሮቼ መረብን ዘረጋ ወደ ኋላም መለሰኝ። ያለማቋረጥ ባዶና ደካማ አደረገኝ።
14የመተላለፌ ቀንበር በእጆቹ በአንድ ላይ ታስረዋል። በአንድ ላይ ተገምደዋል፥በአንገቴም ላይ ተደርገዋል። ብርታቴን ከንቱ አደረገው። ጌታ በእጃቸው አሳልፎ ሰጠኝ፥ መቆምም አልችልም።
15ጌታ፥የሚመክቱልኝን ኃያላን ወንዶች ሁሉ ወዲያ ጣላቸው። ጽኑዓን ወንዶቼን ለማድቀቅ ጉባዔን በላዬ ጠራብኝ። ጌታ ድንግሊቱን የይሁዳ ልጅ በወይን መጥመቂያ እንዳለ ወይን ረገጣት።
16ስለ እነዚህ ነገሮች አለቅሳልሁ። ሕይወቴን የሚያድሳት አጽናኙ ከእኔ ርቋልና ከዓይኖቼ ውኃ ይፈሳል፥ ከዓይኖቼ።
17ጽዮን እጆቿን እጅግ ዘረጋች፥ የሚያጽናናት ማንም የለም። እግዚአብሔር በያዕቆብ ዙሪያ ያሉ ጠላቶቹ እንዲሆኑ አዘዘ። ኢየሩሳሌም በእነርሱ ዘንድ እንደ ርኩስ ነገር ተቆጠረች።
18በትዕዛዙ ላይ ዐመጽ አድርጌእለሁና እግዚአብሔር ጻድቅ ነው። እናንተ ሕዝቦች ሁሉ ስሙ፥ ሐዘኔንም ተመልከቱ። ደናግሎቼና ኃያላን ወንዶቼ ተማርከዉ ሄደዋል።
19ፍቅረኞቼን ጠራኋቸው፥ ነገር ግን ከዳተኞች ሆኑብኝ። ካህናቶቼና ሽማግሌዎቼ ሕይወታችውን ለማኖር ምግብ እየፈለጉ በከተማ ውስጥ ሞቱ።
20እግዚአብሔር ሆይ ተጨንቄአለሁና ውስጤም ተንጦአልና ተመልከት። እጅግ ዓመጽ አድርጌአለሁና ልቤ በውስጤ ታውኮአል። በመንገዶች ላይ ሰይፍ ልጆቻችንን ይነጥቃል፥በቤትም እንደ ሙታን መንደር ነው።
21ሲቃዬን ስማ። የሚያጽናናኝ ማንም የለም። ጠላቶቼ ሁሉ ስለ መከራዬ ሰምተዋል። አንተ ስለ አደረግከው ደስ አላቸው። እነርሱም እንደ እኔ ይሆኑ ዘንድ ያወጅክባቸውን ቀን አምጣ።
22ክፋታቸው ሁሉ በፊትህ ይታይ። መቃተቴ ብዙ ነውና፥ ልቤም ደክሞአልና፤ስለ መተላለፌ ሁሉ እንዳሰቃየኽኝ አሰቃያቸው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።