1የነዌም ልጅ ኢያሱ፦ "ሄዳችሁ ምድሪቱን፥ በተለይም ኢያሪኮን ሰልሉ ብሎ ከሰጢም ሁለት ሰዎች በስውር ላከ። እነርሱም ሄደው ረዓብ ወደምትባል ሴተኛ አዳሪ ቤት ገቡ፥ በዚያም አደሩ።
2ለኢያሪኮም ንጉሥ፦ እነሆ የእስራኤል ሰዎች አገሩን ሊሰልሉ ወደዚህ ገብተዋል ብለው ነገሩት።
3የኢያሪኮም ንጉሥ፡-አገሩን ሁሉ ሊሰልሉ ወደ አንቺ የመጡትንና ወደ ቤትሽ የገቡትን ሰዎች አውጪ ብሎ ወደ ረዓብ መልእክት ላከ።
4ነገር ግን ሴቲቱም ሁለቱን ሰዎች ወስዳ ሽሸገቻቸው። እርስዋም፦አዎን ሰዎቹ ወደ እኔ መጥተዋል፥ ነገር ግን ከወዴት እንደ ሆኑ አላወቅሁም፤
5የከተማውም በር የሚዘጋበት ጊዜ ላይ ሰዎቹ ወጡ፤ ወዴት እንደ ሄዱ አላውቅም፤ፈጥናችሁ ከተከተላችሁ ምናልባት ልትይዙአቸው ትችላላችሁ አለች።
6እርስዋ ግን ወደ ሰገንቱ አውጥታቸው፤ በዚያም በጣሪያ ውስጥ ባዘጋጀችው በተልባ እግር ውስጥ ሸሸጋቸው።
7ሰዎቹ ወደ ዮርዳኖስ መሻገሪያ በሚወስደው መንገድ አሳደዱአቸው። አሳዳጆችም እንደወጡ በሮቹ ተቆለፉ።
8ሰዎቹም ሳይተኙ ሴቲቱ ወደ እነርሱ ወደ ሰገነቱ ወጣች።
9ሰዎቹንም እንዲህ አለቻቸው፦እግዚአብሔር ምድሪቱን አሳልፎ እንደሰጣችሁ እናንተንም መፍራት በላያችን እንደ ወደቀ፤ በምድሪቱም በሚኖሩት ሁሉ ከፊታችሁ እንደ ቀለጡ አውቃለሁ።
10ከግብፅ ምድር በወጣችሁ ጊዜ እግዚአብሔር የኤርትራን ባሕር በፊታችሁ እንዳደረቀ፤ በዮርዳኖስም ማዶ በነበሩት እናንተም ፈጽማችሁ ባጠፋችኋቸው በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት፥በሴዎንና በዐግ ያደረጋችሁትን ሰምተናል።
11ይህን በሰማን ጊዜ ልባችን ቀለጠ፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር በላይ በሰማይ በታችም በምድር እርሱ አምላክ ነውና ከእናንተ የተንሣ ከዚያ ወዲያ ለማንም ነፍስ አልቀርለትም።
12እሁንም እባካችሁ እኔ ለእናንተ ቸርነት እንዳደረግሁ እናንተ
13ደግሞ ለአባቴ ቤት ቸርነት እንድታደርጉ፥ አባቴንና እናቴን፥ ወንድሞቼንና እኅቶቼንና ቤተ ሰቦቻቸውን ሁሉ እንድታድኑ፤ እንዲሁም ከሞት እንድታድኑን በእግዚአብሔር ማሉልኝ እውነተኛ ምልክትም ስጡኝ።
14ሰዎቹ፦ "ይህን ነገራችንን ባትገልጪ ነፍሳችን በነፍሳችሁ ፋንታ እስከሞት እንኳ ይሆናል፤ እግዚአብሔርም ምድሪቱን በሰጠን ጊዜ ምሕረትን እናደርጋለን እንዲሁም ታማኝ ሆነን እንገኛለን፤" አሉአት።
15ቤትዋም በከተማ ቅጥር የተጠጋ ስለነበረ በመስኮቱ በገመድ አወረደቻቸው።
16እርስዋም፦አሳዳጆቹ እንዳያገኙአችሁ ወደ ተራራው ሂዱ አሳዳጆቹም እስኪመለሱ ድረስ በዚያ ሦስት ቀን ተሰውራችሁ ተቀመጡ ኋላም መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ አለቻቸው።
17ሰዎቹም አሉአት፦ይህን የምንልሽን ካላደረግሽ እኛም ከዚህ ካማልሽን መሐላ የተነሣ የሰጠንሽን ተስፋ ከመጠበቅ ነፃ እንሆናለን።
18እነሆ እኛ ወደ አገሩ በገባን ጊዜ ይህን ቀይ ክር እኛን ባወረድሽበት መስኮት በኩል እሰሪው ፤አባትሽንም እናትሽንም ወንድሞችሽንም የእባትሽንም ቤተ ሰብ ሁሉ ወደ አንቺ ቤት ሰብስቢ።
19ከቤትሽም ደጅ ወደ ሜዳ የሚወጣ ሁሉ ደሙ በራሱ ላይ ይሆንበታል፤ እኛም ንጹሐን እንሆናለን። ነገር ግን ከአንቺ ጋር በቤቱ ውስጥ ያለውን አንድ ሰው ቢነካው ደሙ በእኛ ራስ ላይ ይሆናል።
20ነገር ግን ይህንን ጉዳያችንን ብትገልጪ እኛም ከዚህ ካማልሽን መሐላ የተነሣ የሰጠንሽን ተስፋ ከመጠበቅ ነፃ እንሆናለን።
21እርስዋም፦ እንደቃላችሁ ይሁን አለች። ሰደደቻቸውም እነርሱም ሄዱ፤ ቀዩንም ክር በመስኮቱ በኩል አንጠለጠልችው።
22እነርሱም ሄደው ወደ ተራራው ደረሱ፥ አሳዳጆቹም እስኪመለሱ ድረስ እዚያ ለሦስት ቀናት ቆዩ። በመንገዱ ሁሉ ፈልገው አላገኙአቸውም።
23ሁለቱም ሰዎች ተመለሱ፤ ከተራራውም ወርደው ተሻገሩ ወደ ነዌም ልጅ ወደ ኢያሱ መጡ፤ የደረሰባቸውንም ሁሉ ነገሩት።
24ለኢያሱም እንዲህ አሉት፦ በእውነት እግዚአብሔር ይህን አገር ሁሉ በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶናል፤ በአገሩም ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ ከእኛ የተነሣ እየቀለጡ አሉት።