መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢያሱ 1

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እንዲህም ሆነ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ከሞተ በኋላ እግዚአብሔር የሙሴ ዋና ረዳት የሆነውን የነዌ ልጅ ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦
2አገልጋዬ ሙሴ ሞቶአል። ስለዚህም ለእስራኤል ልጆች ወደምሰጣቸው ምድር አንተና ይህ ሕዝብ ሁሉ ተነሥታችሁ ይህን ዮርዳኖስ ተሻገሩ።
3የእግራችሁ ጫማ የሚረግጥውን ቦታ ሁሉ ለእናንተ ሰጥቼአለሁ።ለሙሴም ተስፋ እንደ ሰጠሁት ሰጥቻችኋለሁ።
4ከምድረ በዳው ከዚህም ከሊባኖስ ጀምሮ እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ድረስ፤ የኪጢያውያን ምድር ሁሉ እስከ ፀሐይ መግቢያ እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ዳርቻእሁ ይሆናል።
5በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ማንም ሊቋቋምህ አይችልም። ከሙሴ ጋር እንደ ነበርሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ። አልጥልህም አልትውህም።
6ለአባቶቻቸው፦እሰጣችኋለሁ ብዬ ተስፋ የሰጠ'ኋችሁውን ምድር ይህ ሕዝብ እንዲወርስ ታደርጋለህና ጽና አይዞህ።
7ስለዚህም ጽና እጅግ በርታ። አገልጋዬ ሙሴ ያዘዘህን ሕግን ሁሉ ትጠብቀው ዘንድ ተጠንቀቅ። በምትሄድበትም ሁሉ እንዲከናወንልህ ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ አትበል።
8ስለዚህ ሕግ መጽሐፍ ሁልጊዜ ተናገር። የተጻፈበትንም ሁሉ ትጠብቅ ዘንድ በቀንና በሌሊትም አሰላስለው። የዚያን ጊዜም የተከናወነልህና የተሳከልህ ትሆናለህ።
9በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና፦ "ጽና፥ አይዞህ፥ አትፍራ፥ ተስፋ አትቁረጥ ብዬ አላዘዝሁህምን?"
10ኢያሱም የሕዝቡን አለቆች እንዲህ ብሎ አዘዘ፦
11"በሰፈሩ መካከል እለፉ፤ ሕዝቡንም፦ ለራሳችሁ ስንቃችሁን አዘጋጁ ብላችሁ እዘዙአቸው። እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዲትወርሱ ወደሚሰጣችሁ ምድር በሦስት ቀናት ውስጥ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ትወርሳላችሁ።
12ኢያሱም የሮቤልን ልጆች የጋድንም ልጆች የምናሴንም ነገድ እኩሌታ እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦
13የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ እንዲህ ብሎ ያዘዛቸውን ቃል አስቡ፦አምላካችሁ እግዚአብሔር እረፍት ይሰጣችኋል፤ይህንንም ምድር ይሰጣችኋል።
14ሚስቶቻችሁ፥ ልጆቻችሁና ከብቶቻችሁ ሙሴ በዮርዳኖስ ማዶ በሰጣችሁ ምድር ይቀመጣሉ። ነገር ግን ተዋጊ የሆኑ ሰዎቻችሁ እግዚአብሔር ለእናንተ እንደሰጣችሁ
15ወንድሞቻችሁን እረፍት እስኪሰጥ ድረስ ከወንድሞቻችሁ ፊት በመሆን እነርሱንም ለመርዳት ይሄዳሉ ። እነርሱም ደግሞ አምላካችሁ እግዚአብሔር የሚሰጣቸውን ምድር ይወርሳሉ። ከዚያም በኋላ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ብዮርዳኖሴ ማዶ በፀሐይ መውጫ ወደሰጣችሁ ወደ ርስታችሁ ትመለሳላችሁ፤ ትወርሳላችሁም።
16እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ብለው መለሰለት፦ያዘዝኸንን ነገር ሁሉ እናደርጋለን፤ ወደምትልከንም ስፍራ ሁሉ እንሄዳለን።
17ለሙሴ እንደ ታዘዝን ለአንተ ደግሞ እንታዘዛለን። ከሙሴ ጋር እንደ ነበረ እግዚአብሔር አምላክህ ብቻ ከአንተጋር ይሁን።
18በትእዛዝህ ላይ የሚያምፅና ቃልህን የማይታዘዝ ማንም ቢሆን ይገደል። ብቻ ጽና፥ በርታ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።