መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢሳይያስ 62

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ስለ ጽዮን ዝም አልልም፣ ስለ ኢየሩሳሌምም ጸጥ አልልም፣ ጽድቅዋ እንደ ጸዳል መዳንዋም እንደሚበራ ፋና እስኪወጣ ድረስ።
2አሕዛብም ጽድቅሽን ነገሥታትም ሁሉ ክብርሽን ያያሉ፤ የእግዚአብሔርም አፍ በሚጠራበት በአዲሱ ስም ትጠሪያለሽ።
3በእግዚአብሔር እጅ የክብር አክሊል፣ በአምላክሽም እጅ የመንግሥት ዘውድ ትሆኛለሽ።
4ከእንግዲህ ወዲህ፣ "የተተወች" አትባዪም፤ ምድርሽም ከእንግዲህ ወዲህ፣ "ውድማ" አትባልም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በአንቺ ደስ ብሎታልና፣ ምድርሽም ባል ታገባለችና አንቺ፣ "ደስታዬ የሚኖርባት" ትባያለሽ ምድርሽም፣ "ባል ያገባች" ትባላለች።
5ጕልማሳም ድንግሊቱን እንደሚያገባ፣ እንዲሁ ልጆችሽ ያገቡሻል። ሙሽራም በሙሽራይቱ ደስ እንደሚለው፣ እንዲሁ አምላክሽ በአንቺ ደስ ይለዋል።
6ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ጕበኞችን በቅጥርሽ ላይ አቁሜአለሁ፤ ቀንና ሌሊት ከቶ ዝም አይሉም፤ እናንተ እግዚአብሔርን የምታሳስቡ፣
7ኢየሩሳሌምን እስኪያጸና በምድርም ላይ ምስጋና እስኪያደርጋት ድረስ አትረፉ ለእርሱም ዕረፍት አትስጡ።
8እግዚአብሔር፣ "ከእንግዲህ ወዲህ በእርግጥ ለጠላቶችሽ መብል ይሆን ዘንድ እህልሽን አልሰጥም፣ መጻተኞችም የደከምሽበትን ወይንሽን አይጠጡም።
9ነገር ግን የሰበሰቡት ይበሉታል፣ እግዚአብሔርንም ያመሰግናሉ፣ ያከማቹትም በመቅደሴ አደባባይ ላይ ይጠጡታል" ብሎ በቀኙና በኃይሉ ክንድ ምሎአል።
10እለፉ፣ በበሮች በኩል እለፉ! የሕዝቡንም መንገድ ጥረጉ፤ አዘጋጁ፣ ጐዳናውን አዘጋጁ፣ ድንጋዮቹንም አስወግዱ፤ ለአሕዛብም ዓለማ አንሡ!
11ተመልከቱ፣ እግዚአብሔር ለምድር ዳርቻ አዋጅ እንዲህ ብሎ ነግሮአል፣ "ለጽዮን ልጅ፣ እነሆ፥ መድኃኒትሽ ይመጣል፤ እነሆ፣ ዋጋው ከእርሱ ጋር ሥራውም በፊቱ አለ" በሉአት።
12እግዚአብሔር፣ "የተቤዣቸው፣ የተቀደሰ ሕዝብ" ብለው ይጠሩአቸዋል፤ አንቺም፣ "የተፈለገች ያልተተወችም" ከተማ ትባያለሽ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።