መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኢሳይያስ 52

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ጽዮን ሆይ፣ ተነሺ፣ ተነሺ፣ ኃይልሽን ልበሺ፤ ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ያልተገረዘና ርኩስ ከእንግዲህ ወዲህ አይገባብሽምና ጌጠኛ ልብስሽን ልበሺ።
2ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ትቢያን አራግፊ፤ ተነሺና ተቀመጪ፤ ምርኮኛይቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፣ የአንገትሽን እስራት ፍቺ።
3እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ "በከንቱ ተሽጣችሁ ነበር፣ ያለ ገንዘብም ትቤዣላችሁ።"
4ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ወገኔ በዚያ እንግዳ ሆኖ ይቀመጥ ዘንድ አስቀድሞ ወደ ግብጽ ወረደ፣ አሦርም ቅርብ ጊዜ ላይ ያለ ምክንያት በደለው።
5ወገኔ በከንቱ ተወስዶአልና አሁን ከዚህ ምን አለኝ? ይላል እግዚአብሔር፤ የሚገዙአቸው ይጮኻሉ፣ ይላል እግዚአብሔር፣ ስሜም ሁልጊዜ ቀኑን ሁሉ ይሰደባል።
6ስለዚህ ወገኔ ስሜን ያውቃል፤ ስለዚህም የምናገር እኔ እንደ ሆንሁ በዚያ ቀን ያውቃሉ፤ አዎን፣ እኔ ነኝ!"
7የምስራች የሚናገር፣ ሰላምንም የሚያወራ፣ የመልካምንም ወሬ የምስራች የሚናገር፣ መድኃኒትንም የሚያወራ፣ ጽዮንንም፣ "አምላክሽ ነግሦአል!" የሚል ሰው እግሩ በተራሮች ላይ እጅግ ያማረ ነው።
8አድምጪ፣ ጕበኞችሽ ጮኸዋል፤ እግዚአብሔር ወደ ጽዮን በተመለሰ ጊዜ ዓይን በዓይን ይተያያሉና ድምፃቸውን ያነሣሉ፣ በአንድነትም ይዘምራሉ።
9እናንተ የኢየሩሳሌም ፍርስራሾች ሆይ፣ እግዚአብሔር ሕዝቡን አጽናንቶአልና፤ ኢየሩሳሌምንም ታድጎአልና ደስ ይበላችሁ፣ በአንድነትም ዘምሩ።
10እግዚአብሔር የተቀደሰውን ክንዱን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ገልጦአል፤ በምድር ዳርቻ የሚኖሩትም ሁሉ የአምላካችንን መድኃኒት ያያሉ።
11እናንተ የእግዚአብሔር ዕቃ የምትሸከሙ ሆይ፣ ትታችሁ ውጡ፣ ትታችሁ ውጡ፤ ከዚያ ውጡ፣ ርኩስን ነገር አትንኩ፣ ከመካከልዋ ውጡ፣ ንጽሐን ሁኑ።
12እግዚአብሔር ይቀድማችኋልና፣ የእስራኤልም አምላክ ይከተላችኋልና በችኰላ አትወጡም በመኰብለልም አትሄዱም።
13ተመልከቱ፣ ባሪያዬ በማስተዋል ያደርጋል፤ ይከብራል ከፍ ከፍም ይላል፣ እጅግ ታላቅም ይሆናል።
14ፊቱ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ፣ መልኩም ከሰዎች ልጆች ይልቅ ተጐሳቍሎአልና ብዙ ሰዎች ስለ አንተ እንደ ተደነቁ፣ እንዲሁ ብዙ አሕዛብን ያስደንቃል፤
15ያልተነገረላቸውንም ያያሉና፣ ያልሰሙትንም ያስተውላሉና ነገሥታት ስለ እርሱ አፋቸውን ይዘጋሉ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።