መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሐጌ 1

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት በስድስተኛው ወር መጀመሪያ ቀን በነቢዩ በሐጌ በኩል ወደ ይሁዳ ገዢ ወደ ሰላትያል ልጅ ወደ ዘሩባቤልና ወደ ሊቀ ካህኑ ኢዮሴዴቅ ልጅ ወደ ኢያሱ የያህዌ ቃል መጣ።
2የሠራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ ይህ ሕዝብ “እኛ የምንመጣበት ወይ የያህዌን ቤት የምንሠራበት ጊዜ ገና ነው” ይላል።
3የያህዌ ቃል በነቢዩ በሐጌ በኩ መጣ፤ እንዲህም አሉ፣
4“ይህ ቤት ፈራርሶ እያለ፣ እናንተ ራሳችሁ ባማሩ ቤቶቻችሁ ለመኖር ጊዜው ነውን?
5ስለዚህ የሠራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፣ እስቲ፣ የሠራችሁትን ቤት አስቡ!
6ብዙ ዘራችሁ፤ ግን ጥቂት አጭዳችሁ፤ በላችሁ ግን አልጠገባችሁም፤ ጠጣችሁ ግን አልረካችሁም። ለበሳችሁ ግን አልሞቃችሁም፤ ደመወዝ ተቀበላችሁ ግን ብዙ ቀዳዶች በሞሉበት መያዣ የማስቀመጥ ያህል ሆነባችሁ!
7የሠራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ እስቲ የሠራችሁትን አስቡ!
8ወደ ተራራ ውጡ፤ እንጨትን አምጡና ቤቴን ሥሩ፤ ያኔ እኔ በእርሱ ደስ ይለኛል፣ እከብርበታለሁ! ይላል ያህዌ።
9ብዙ ጠበቃችሁ፤ ግን እኔ እፍ ስላልሁበት ወደ ቤት ያመጣችሁት ግን ጥቂት ነው፤ እንዲህ ያደረግሁት ለምን ይመስላችኋል? የሠራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል! ምክንያቱም የእኔ ቤት ፈርሶ እያለ፣ ሰው ሁሉ በገዛ ራሱ ቤት እጅግ ደስ በመሰኘቱ ነው።
10ከዚህ የተነሣ ሰማያት ጠል ከለከሉ፤ ምድርም ፍሬዋን ነሣች።
11እኔ በምድሪቱና በተራሮች፤ በእህሉና በአዲሱ ወይን ጠጅ፤ በዘይቱና ምድር በምትሰጠው ሁሉ ላይ፣ በሰዎችና በእንስሳት፣ በእጆቻችሁ ሥራ ሁሉ ላይ ድርቅ አመጣለሁ!
12ከዚህ በኋላ የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤልና ሊቀ ካህኑ የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ፣ ከምርኮ ከተረፉት ሕዝብ ሁሉ ጋር የአምላካቸው የያህዌን ድምጽ ሰሙ፤ አምላካቸው ያህዌ ልኮታልና ለነቢዩ ሐጌ ቃል ታዘዙ። ሕዝቡም ያህዌን ፈሩ።
13ከዚያም የያህዌ መልእክተኛ ሐጌ ለሕዝቡ የያህዌን መልእክት እንዲህ በማለት ተናገረ፤ “እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ! ይህ የያህዌ ቃል ነው!
14ስለዚህ ሄደው የአምላካቸውን የሠራዊት ጌታ የያህዌን ቤት እንዲሠሩ የይሁዳን ገዢ የሰላትያል ልጅ የዘሩባቤልን መንፈስና የኢዮሴዴቅ ልጅ የካህኑ ኢያሱን መንፈስ፣ እንዲሁም ከምርኮ የተረፉትን ሰዎች ሁሉ መንፈስ ያህዌ አነሣሣ።
15ይህ የሆነው በንጉሥ ዳርዮስ ሁለተኛ ዓመት በስድስተኛው ወር ሃያ አራተኛ ቀን ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።