መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዕንባቆም 3

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የነቢዩ ዕንባቆም ጸሎት
2ያህዌ ሆይ፣ ስላደረግኸው ድንቅ ሥራ ሰዎች ፈራሁ፤ የቀድሞ ዘመን ሥራህን በዚህ ዘመንም አድርግ፤ በየዘመናቱም እንዲታወቅ አድርግ፡፡ በቁጣህ ውስጥ እንኳ ምሕረት ርኅራኄኅን አስብ፡፡
3እግዚአብሔር ከቴማን፣ ቅዱሱንም ከፋራን ተራራ መጣ! ሴላ፡፡ ክብሩ ሰማያትን ሸፈነ፤ ምድር በምስጋናው ተሞላች፡፡
4ኃይሉ ከተሰወረበት እጁ የወጡ ሁለት ጨረሮች እንደ መብረቅ ደምቀዋል፡፡
5መቅሠፍት በፊቱ ሄደ፤ ቸነፈርም እግር በእግር ተከተለው፡፡
6እርሱ ሲቆም ምድር ትናወጣለች፤ እርሱ ሲመለከት ሕዝቦች ይንቀጠቀጣሉ፡፡ የዘላለም ተራሮች እንኳ ተፈረካከሱ የጥንት ኮረብቶችም ዝቅ አሉ፡፡ መንገዱ ዘላለማዊ ነው፡፡
7የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ፣ የምድያምም መኖሪያዎች ሲታወኩ አየሁ፡፡
8ያህዌ ወንዞች ላይ ተቆጥቷልን? መዓትህስ በምንጮች ላይ ነበርን? ወይስ በፈረሶችህና በድል አድራጊ ሰረገሎችህ በጋለብህ ጊዜ ባሕር ላይ ተቆጥተህ ነበርን?
9ቀስትህን ከሰገባው አወጣህ፤ ፍላጻህንም ለመወርወር አዘጋጀህ፡፡ ሴላ፡፡ ምድርን በወንዞች ከፈልህ፡፡
10ተራሮች አዩህ፤ በፍርሃትም ተጨማደዱ የውሃ ወጀብ በላያቸው አለፈ፤ ጥልቁ ባሕር ድምፁን አሰማ ማዕበሉም ወደ ላይ ከፍ ከፍ አለ፡፡
11ከሚወረወሩ ፍላጾች ብርሃን፣ ከሚያብረቀርቀው የጦርህ ነጸብራቅ የተነሣ ፀሐይና ጨረቃ በቦታቸው ቆሙ፡፡
12በቁጣህ በምድር ላይ ተመላለስህ፤ በመዓትህ ሕዝቦችን አደቀቅህ፡፡
13ሕዝብህን ለማዳን፣ የቀባኸውንም ለመታደግ ወጣህ፡፡ ዕርቃኑን ታስቀረው ዘንድ የዐመፃን ቤት ራስ ቀጠቀጥህ፡፡ ሴላ፡፡
14እንደ ዐውሎ ነፋስ ሊበታትን የመጣውን፣ ምስኪኑን በስውር ለመዋጥ የመጣውን ሰራዊት አለቃ ራስ በገዛ ፍላጻው ወጋህ፡፡
15በፈረሶችህ ባሕሩ ላይ ተራመድህ፤ ታላላቅ ውሆችን ከመርህ፡፡
16እኔ ሰማሁ ውስጤም ተናወጠ፤ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፡፡ አጥንቶቼ ይበሰብሳሉ፤ እግሮቼም ከታች ይርዳሉ ወራሪዎቻችን ላይ መከራ የሚመጣበትን ቀን በትዕግሥት እጠብቃለሁ፡፡
17ምንም እንኳ የበለስ ዛፍ ባያብብ፣ ወይን ዛፍ ላይ ፍሬ ባይገኝ፣ የወይራ ዛፍ ምንም ፍሬ ባይሰጥ፣ ከእርሻዎች ሰብል ቢጠፋ፣ የበግ መንጋዎች ሁሉ ቢያልቁ፣ በረት ውስጥ ምንም ከብት ባይገኝ፣
18ይህም ሁሉ ቢሆን፣ እኔ በያህዌ ደስ ይለኛል በመድኃኒቴም አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ፡፡
19ጌታ ያህዌ ኃይሌ ነው፤ እግሮቼን እንደ ዋሊያ እግሮች ያደርጋል፤ በከፍታዎቼም ላይ ይመራኛል፡፡ - ለመዘምራን አለቃ በባለ አውታር መሣሪያዎች የተዘመረ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።