መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘፍጥረት 29

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ያዕቆብ ጉዞውን ቀጥሎ በስተ ምሥራቅ ወዳለው አገር ደረሰ፤
2እዚያም በሜዳ ላይ አንድ የውሃ ጉድጓድ አየ፤ በሦስት የተከፈሉ የበግ መንጋዎች በጉድጓድ ዙሪያ ነበሩ፤ መንጋዎቹ ውሃ የሚጠጡት ከዚሁ ጉድጓድ ነበር፤ ጉድጓዱም የሚዘጋበት ድንጋይ ትልቅ ነበር፤
3መንጋዎቹ ሁሉ እዚያ ከተሰበሰቡ በኋላ እረኞቹ ድንጋዩን አንከባለው ከጉድጓዱ ውሃ ያጠቱአቸው ነበር፤ መንጋዎቻቸውን ካጠጡ በኋላ ግን ድንጋዩንም መልሰው በጉድጓዱ አፍ ላይ ይከዱኑታል።
4ያዕቆብም እረኞቹን "ወዳጆቼ ሆይ! ከየት ነው የመጣችሁት?" ብሎ ጠየቃቸው። እነሱም "እኛ የመጣነው ከካራን ነው" አሉት።
5እርሱም "የናኮርን የልጅ ልጅ ላባን ታውቁታላችሁን?" ብሎ ጠየቃቸው። እነሱም "አዎ እናውቀዋለን" አሉት።
6እርሱም "ለመሆኑ እርሱ ደኅና ነውን?" አላቸው። እነርሱም "አዎ፣ ደኅና ነው፤ እንዲያውም ልጁ ራሔል ያችውልህ! በጎች እየነዳች በመምጣት ላይ ነች" አሉት።
7ያዕቆብም "ጊዜው ገና ቀን ነው፤ መንጋዎቻቸውንም ወደ ቤት የምታስገቡበት ሰዓት ገና አልደረሰም፤ ታዲያ ለምን ውሃ አጠጥታችሁ አታሰማሩአቸውም? ፤ አለ።
8እነርሱም "እረኞች ሁሉ መንጋዎቻቸውን ይዘው እዚህ ከመሰብሰባቸው በፊት ምንም ማድረግ አንችልም፤ ሁሉም እዚህ ከመጡ በኋላ ግን ድንጋዩን በኅብረት አንከባለን በጎቹን እናጠጣቸዋለን" አሉት።
9ያዕቆብም ከእረኞቹ ጋር በመነጋገር ላይ ሳለ ራሔል የአባትዋን በጎች ይዛ ወደዚያ መጣች፤ ምክንያቱም እርስዋ የበጎች እረኛ ነበረች።
10ያዕቆብ ያጉቱን የላባን በጎች እየነዳች ስትመጣ ራሔልን አይቶ ወደ ጉድጓድ ሄደ፤ ጉድጓዱ የተከደነበትንም ድንጋይ አንከባሎ በጎቹን አጠጣቸው።
11ከዚያ በኋላ ራሔልን ሳማት። ከደስታውም ብዛት የተነሣ አለቀሰ፤
12"እኔ የአባትሽ እኅት የሆነችው የርብቃ ልጅ ሄደች።
13ላባም የእኅቱ ልጅ ያዕቆብ መምጣቱን በሰማ ጊዜ ሊቀበለው ፈጥኖ ሄደ፤ አቅፎ ከሳመውም በኋላ ወደ ቤት አመጣው፤ ያዕቆብ የሆነውን ሁሉ ለላባ ነገረው፤
14ላባም "በእርግጥ አንተ ቅርብ የሥጋ ዘመዴ ነህ" አለው፤ ያዕቆብም አንድ ወር ያህል ከአጎቱ ጋር ተቀመጠ።
15ላባ ያዕቆብን "ዘመዴ በመሆንህ ብቻ በነፃ ልታገለግለኝ አይገባህም፤ ስለዚህ ምን ያህል ደመወዝ ላስብልህ? አለው።
16ላባ ሁለት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ ታላቂቱ ልያ፤ ታናሽቱ ራሔል ይባሉ ነበር።
17ልያ ዐይነ ልም ስትሆን፣ ራሔል ግን ቁመናዋ የሚያምር የደስ ደስ ያላት ነበረች።
18ያዕቆብ ራሔልን እጅግ ስለወደዳት "ራሔልን ብትድርልኝ ሰባት ዓመት አገለግልሃለሁ" አለ።
19ላባም "ለሌላ ሰው ከምሰጣት ይልቅ ለአንተ ብሰጥህ ይሻለኛል፤ እሺ ተስማምቼአለሁ፤ እዚሁ ከእኔ ጋር ኑር" አለው።
20ያዕቆብ ራሔልን ለማግባት ሰባት ዓመት አገለገለ፤ ይሁን እንጂ ራሔልን በጣም ይወዳት ስለነበር የቆየበት ጊዜ ጥቂት ቀን ብቻ መስሎ ታየው።
21ከዚያ በኋላ ያዕቆብ ላባን "እነሆ የአገልግሎት ዘመኔ ተፈፅሞአል፤ ሚስት እንድትሆነኝ ልጅህን ስጠኝ" አለው።
22ላባም የሠርግ ድግስ አዘጋጅቶ በአቅራቢያው የሚገኙትን ሰዎች ሁሉ ጠራ።
23ነገር ግን ላባ በራሔል ምትክ ልያን ለያዕቆብ ሰጠው፤ ያዕቆብም ከልያ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት አደረገ።
24ላባ ሴት አገልጋዩን ዚልፋን አገልጋያዋን እንድትሆን ለልጁ ለልያ ሰጣት።
25በማግስቱ ጠዋት ያዕቆብ አብራው ያደረችው ልያ መሆንዋን ባወቀ ጊዜ ወደ ላባ ሄዶ "ይህ ያደረግህብኝ ነገር ምንድን ነው? ያገለገልሁህ ራሔልን ለማግኘት አልነበረም? ታዲያ ለምን አታለልከኝ"አለው።
26ላባም "ታላቂቱ ሳትዳር፤ ታናሺቱን መዳር የአገራችን ልማድ አይደለም፤
27የልያ ሠርግ ሰባት ቀን እስኪሞላው ድረስ ጠብቅ፤ ከእንግዲህ ወዲይ ሰባት ዓመት የምታገለግለኝ ከሆነ ራሔልን እሰጥሃለሁ" አለው።
28ያዕቆብም ነገሩ ተስማማ፤ ከልያ ጋር ሰባት ቀን ተሞሽሮ ከቆየ በኋላ፤ ላባ ልጁን ራሔልን ለያዕቆብ ሳረለት።
29ላባ ሴት አገልጋዩን ባላን አገልጋይዋ እንድትሆን ለልጁ ለራሔል ሰጣት።
30ያዕቆብ ከራሔልም ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት አደረገ፤ ከልያም አብልጦ ወደዳት፤ ከዚያ በኋላ ላባን ሰባት ዓመት አገለገለው።
31ልያ የራሔልን ያህል እንዳልተወደደች እግዚአብሔር ባየ ጊዜ መውለድ እንድትችል ማሕፀንዋን ከፈተላት፤ ራሔል ግን መኻን ሆነች፤
32ልያ ርርግዛ ወንድ ልጅ ወለደች፤ "እግዚአብሔር መከራዬን ተመለከተ፤ ከእንግዲህስ ወዲያ ባሌ ይወደኛል" ስትል ስሙን ሮቤል አለችው።
33እንደገና አረገዘችና ሌላ ወንድ ልጅ ወደች፤ "እግዚአብሔር እንዳልተወደድሁ ሰማ፤ ይህንንም ልጅ ደግሞ ሰጠኝ' ስትል ስሙን ስምዖን አለችው።
34እንደገና 'አረገዘችና ሌላ ወንድ ልጅ ወለደች፤ "እንግዲህ ሦስት ወንዶች ልጆች ስለ ወለድሁለት ባሌ ከእኔ ጋር በፍቅር ይጠመዳል" ስትል ስሙን ሌዊ አለችው፤
35እንደገና አረገዘችና ውንድ ልጅ ወለደች፤ "አሁንስ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ" ስትል ስሙን ይሁዳ አለችው፤ ከዚህ በኋላ መውለድ አቋረጠች።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።