መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ገላቲያ 5

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ክርስቶስ ነጻ ያወጣን በነጻነት እንድንኖር ነው ። ስለዚህ ጸንታችሁ ቁሙ፥ እንደገና በባርነት ቀንበር አትጠመዱ።
2እኔ ጳውሎስ የምለውን ተመልከቱ ብትገረዙ ክርስቶስ በምንም ዓይነት መልኩ አይጠቅማችሁም።
3የተገረዘ ሁሉ ህግን ሁሉ የመፈጸም ግዴታ አለበት ብዬ እንደገና እመሰክራለሁ።
4በህግ ልትጸድቁ የምትደክሙ ሁላችሁ የእግዚአብሔር ጠላቶች ሆናችኋል፤ከጸጋም ርቃችኋል።
5ምክንያቱም እኛ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት የጽድቅን ዋስትና ስለምንጠብቅ ነው።
6በክርስቶስ ኢየሱስ ከፍቅር የሆነ እምነት እንጂ መገረዝም ሆነ አለመገረዝ ምንም ትርጉም የለውም።
7በጥሩ ሁኔታ ትሮጡ ነበር። ታዲያ ለእውነት ከመታዘዝ ያስቆማችሁ ማነው?
8ይህን እንድታደርጉ የሚያደርግ ጉትጎታ ከጠራችሁ የመጣ አይደለም።
9ትንሽ እርሾ ሊጡን በሙሉ እንዲቦካ ያደርጋል።
10በሌላ መልኩ እንደማታስቡ በጌታ እተማመንባችኋለሁ። ግራ የሚያጋባችሁ ማንም ይሁን ማን ፍርዱን ይቀበላል።
11ወንድሞች ሆይ እስከአሁን ተገረዙ እያልኩ የምሰብክ ቢሆን ለምን እሰደድ ነበር? እንግዲያውስ የመስቀሉ እንቅፋት ይደመሰሳል።
12የሚያስቷችሁ እራሳቸው ሄደው በተሰለቡ ብዬ እመኛለሁ።
13ወንድሞች ሆይ እግዚአብሔር የጠራችሁ ለነጻነት ነው። ብቻ ነጻነታችሁን ለሥጋ ፈቃድ አትጠቀሙበት፥ በዚያ ፈንታ እርስ በእርሳችሁ በፍቅር አንዳችሁ አንዳችሁን አገልግሉ።
14ምክንያቱም ህግ ሁሉ «ባልንጀራህን እንደራስህ ልትወድ ይገባል»
15በሚለው ትዕዛዝ የተጠቀለለ ነው።
16በመንፈስ ተመላለሱ የሥጋን ክፉ ምኞት አትፈጽሙ እላችኋለሁ።
17ምክንያቱም ሥጋ ከመንፈስ ተቃራኒ መንፈስም ከሥጋ ተቃራኒ ነገር ይመኛሉና ነው።
18እነዚህ እርስ በእርሳቸው ስለሚቀዋወሙ በውጤቱ እናንተ የምትፈልጉትን ለማድረግ አትችሉም።
19እንግዲህ የሥጋ ስራዎች የተገለጡ ናቸው። እነዚህም አስቀድሜ እንዳስጠነቀኩዋችሁ
20ዝሙት፣እርኩሰት፣ክፉ ምኞት፣ጣዖትን ማምለክ፣ምዋርት፣ጥል፣ክርክር፣ቅናት፣ በቁጣ መገንፈል፣አድመኛነት፣መለያየት፣
21መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ስካር፥ ዘፋኝነትና የመሳሰሉት ናቸው፥ ፥አስቀድሜ እንደነገርኳችሁ እነዚህን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።
22የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፣ ሠላም፣ ትዕግሥ፣ ቸርነት፥ መልካምነት፥ እምነት፥
23የውሃት፥ ራስን መግዛት ናቸው። ህግ እነዚህን አይቃወም።
24የክርስቶስ ኢየሱስ የሆኑት ሥጋን ከክፉ ስሜቱና መሻቱ ጋር ሰቅለውታል።
25በመንፈስ የምንኖር ከሆነ በመንፈስ እንመላለስ።
26አንታበይ፣ እርስ በእርሳችን ለክፉ አንነሳሳ፣ አንቀናና።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።