1ዕዝራ እየጸለየና እየተናዘዘ በእግዚአብሔር ቤት ፊት ተደፍቶ አለቀሰ። ወንዶች፥ ሴቶችና ልጆች ያሉበት እጅግ ታላቅ የእስራኤል ጉባዔ በዙሪያው ተሰበሰቡ፥ ሕዝቡም ታላቅ ልቅሶ አለቀሱ።
2የኤላም ተወላጅ የይሒኤል ልጅ ሴኬንያ ዕዝራን እንዲህ አለው፥ "እኛ ራሳችን በአምላካችን ላይ ክህደት ፈጽመናል፥ ከሌላ ምድር ሰዎችም ሚስቶችን አግብተናል። ይሁን እንጂ በዚህ ጉዳይ ላይ አሁንም ለእስራኤል ተስፋ አለ።
3አሁንም ጌታዬና የአምላካችንን ትዕዛዝ የሚፈሩት በምትሰጡን መመሪያ መሠረት ሴቶቹን ሁሉ ከልጆቻቸው ጋር ለማሰናበት ከአምላካችን ጋር ቃል ኪዳን እናድርግ፥ ይህም በሕጉ መሠረት ይፈጸም።
4ይህ አንተ ልታደርገው የሚገባህ ጉዳይ ነውና ተነሥ፥ እኛም አብረንህ ነን። በርታና አድርገው።
5ዕዝራ ተነሣና የካህናቱን ዋነኞች፥ ሌዋውያኑንና እስራኤላውያኑን በሙሉ በዚሁ መሠረት ተግባራዊ እንዲያደርጉ ቃል አስገባቸው። እነርሱም ቃል ገቡ።
6ከዚያም ዕዝራ ከእግዚአብሔር ቤት ፊት ተነሥቶ ወደ ኤልያሴብ ልጅ ወደ ዮሐናን ክፍል ገባ። በምርኮ የነበሩት እምነት የለሽ ስለመሆናቸው ያለቅስ ነበርና ምንም ዓይነት ምግብ አልተመገበም አንዳች ውሃም አልጠጣም ነበር።
7በይሁዳና በኢየሩሳሌም የሚገኙ ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች ሁሉ በኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ መልዕክት ላኩ።
8በሦስት ቀን ውስጥ የማይመጣ ማንም ቢኖር በሹማምንቱና በሽማግሌዎቹ ውሳኔ መሠረት ንብረቱ ይወረሳል፥ እርሱም ከምርኮ ከተመለስው ታላቅ የሕዝብ ጉባዔ ይለያል።
9ስለዚህ የይሁዳና የብንያም ሰዎች በሙሉ በሦስት ቀናት ውስጥ በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። ይህም የሆነው በዘጠነኛው ወር ከወሩም በሃያኛው ቀን ነበር። ሕዝቡ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት ፊት ባለው አደባባይ ላይ ቆመው ነበር፥ ከሚሰሙት ቃልና ከዝናቡ የተነሣም ይንቀጠቀጡ ነበር።
10ካህኑ ዕዝራም ተነሥቶ እንዲህ አለ፥"እናንተ ራሳችሁ ክህደት ፈጽማችኋል። የእስራኤልን በደል ለማብዛት ባዕዳን ሴቶችን አግብታችኋል።
11አሁን ግን ለአባቶቻችሁ አምላክ ክብርን ስጡ፥ ፈቃዱንም አድርጉ። ከምድሩ ሰዎችና ከባዕዳን ሴቶች ተለዩ።"
12ጉባዔውም ሁሉ በታላቅ ድምጽ፥ "እንደ ተናገርከው እናደርጋለን።
13ይሁንና ሕዝቡ ብዙ ነው፥ ወቅቱም የዝናብ ጊዜ ነው። እንዲህ ሜዳው ላይ ለመቆም አቅም የለንም፥ በዚህ ጉዳይ እጅግ ተላልፈናልና ሥራው የአንድ ወይም የሁለት ቀን ብቻ አይደለም።
14ስለዚህ ሹማምንቶቻችን ጉባዔውን በሙሉ ይወክሉ። የአምላካችን ብርቱ ቁጣ ከእኛ እስኪመለስ ድረስ ባዕዳን ሴቶች በከተሞቻችን እንዲኖሩ የፈቀዱ ሁሉ የከተማው ሽማግሌዎችና የከተማው ዳኞች በሚወስኑት ቀን ይምጡ።"
15የአሣሄል ልጅ ዮናታንና የቴቁዋ ልጅ የሕዝያ ይህንን ሃሳብ ተቃወሙ፥ ሌዋውያኑ ሜሱላምና ሳባታይም ደገፉአቸው።
16ስለዚህ ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች እንዲህ አደረጉ። ካህኑ ዕዝራም ከነገድ አባቶችና ከቤተሰቡ መሪዎች የሚሆኑ ሰዎችን ሁሉንም በየስማቸው መረጠ፥ እነርሱም በዘጠነኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ጉዳዩን መመልከት ጀመሩ።
17በመጀመሪያው ወር የመጀመሪያው ቀን ባዕዳን ሴቶችን ያገቡት እነማን እንደሆኑ ምርመራቸውን ጨረሱ።
18ከካህናቱ ወገን ባዕዳን ሴቶችን ያገቡ ነበሩ። ከኢዮሴዴቅ ልጅ ከኢያሱና ከወንድሞቹ ተወላጆች መካከል መዕሤያ፥ አልዓዛር፥ ያሪብና ጎዶልያስ። እነዚህ ሚስቶቻቸውን ለመፍታት ወሰኑ።
19በደለኞች ነበሩና ከመንጋዎቻቸው ስለ በደል መሥዋዕት አንዳንድ አውራ በግ አቀረቡ።
20ከኢሜር ተወላጆች አናኒና ዝባድያ።
21ከካሪም ተወላጆች መዕሤያ፥ ኤልያስ፥ ሸማያ፥ ይሒኤልና ዖዝያ።
22ከፋስኩር ተወላጆች ኤልዮዔናይ፥ መዕሤያ፥ ይስማኤል፥ ናትናኤል፥ ዮዛባትና ኤልዓሣ።
23ከሌዋውያኑ መካከል፤ ዮዛባት፥ ሰሜኢ፥ ቆሊጣስ የሚባለው ቆልያ፥ ፈታያ፥ ይሁዳና አልዓዛር።
24ከመዘምራኑ መካከል፤ ኤልያሴብ። በር ከሚጠብቁት መካከል፤ ሰሎም፥ ጤሌምና ኡሪ።
25ከተቀሩት እስራኤላውያን መካከል፤ ከፋሮስ ተወላጆች መካከል፥ ራምያ፥ ይዝያ፥ መልክያ፥ ሚያሚን፥ አልዓዛር፥ መልክያና በናያስ።
26ከኤላም ተወላጆች መካከል፤ ሙታንያ፥ ዘካርያስ፥ ይሒኤል፥ አብዲ፥ ይሬሞትና ኤልያ።
27ከዛቱዕ ተወላጆች መካከል ዔሊዮዔናይ፥ ኢልያሴብ፥ ሙታንያ፥ ይሬሞት፥ ዛባድና ዓዚዛ።
28ከቤባይ ተወላጆች መካከል፤ ይሆሐናን፥ ሐናንያ፥ ዘባይና አጥላይ።
29ከባኒ ተወላጆች መካከል፤ ሜሱላም፥ መሉክ፥ ዓዳያ፥ ያሱብና ሸዓል ራሞት።
30ከፈሐት ሞዓብ ተወላጆች መካከል፤ ዓድና፥ ክላል፥ በናያስ፥ መዕሤያ፥ ሙታንያ፥ ባስልኤል፥ ቢንዊና ምናሴ።
31ከካሪም ተወላጆች መካከል፤ አልዓዛር፥ ይሺያ፥ መልክያ፥ ሸማያ፥ ስምዖን፥
32ብንያም፥ መሉክና ሰማራያ።
33ከሐሱም ተወላጆች መካከል መትናይ፥ መተታ፥ ዛባድ፥ ኤሊፋላት፥ ይሬማይ፥ ምናሴና ሰሜኢ።
34ከባኒ ተወላጆች መካከል፤ መዕዳይ፥ ዓምራም፥ ኡኤል፥
35በናያስ፥ ቤድያ፥ ኬልቅያ፥
36ወንያ፥ ሜሪሞት፥ ኤሌያሴብ፥
37መታንያ፥ መትናይ፥ የዕሡ፥
38ባኒ፥ ቢንዊ፥ ሰሜኢ፥
39ሰሌምያ፥ ናታን፥ ዓዳያ፥
40መክነድባይ፥ ሴሴይ፥ ሸራይ፥
41ኤዝርኤል፥ ሰምምያ፥ ሰማራያ፥
42ሰሎም፥ አማርያና ዮሴፍ።
43ከናባው ተወላጆች መካከል፤ ይዔኤል፥ መቲትያ፥ ዛባድ፥ ዘቢና፥ ያዳይ፥ ኢዮኤልና በናያስ።
44እነዚህ ሁሉ ባዕዳን ሴቶችን ያገቡና አንዳንዶቹም ከእነርሱ የወለዱ ነበሩ።