1የነገዶችም ስም ይህ ነው። የዳን ነገድ አንድ የዕጣ ክፍል ይወስዳል፡ ድንብሩም በሔትሎን መንገድ አጠገብ ወደ ሐማት መግቢያ በደማስቆም ድንበር ባለው በሐጸርዔናን በሐማትም አጠገብ በሰሜን በኩል ካለው ከሰሜን ድንበር ይጀምራል። ወርዳቸውም ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ይሆናል።
2ከዳንም ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለአሴር አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል።
3ከአሴርም ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለንፍታሌም አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል።
4ከንፍታሌም ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለምናሴ አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል።
5ከምናሴም ደቡብ ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለኤፍሬም አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል።
6ከኤፍሬምም ደቡብ ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለሮቤል አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል።
7ከሮቤልም ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለይሁዳ አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል።
8ከይሁዳም ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለመባ የሆነ የዕጣ ክፍል ይሆናል ወርዱ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ይሆናል ርዝመቱም ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ከዕጣ ክፍሎች እንደ አንዱ ይሆናል፥ መቅደሱም በመካከሉ ይሆናል።
9ለእግዚአብሔር የምታቀርቡት መሬት ርዝመቱ ሃያ አምስት ሺህ ወርዱም ሃያ ሺህ ክንድ ይሆናል።
10ይዚህም ቅዱስ ስፍራ አገልግሎት ይህ ነው፡ ለካህናቱ በሰሜን በኩል ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ፥ በምዕራብም በኩል ወርዱ አሥር ሺህ፥ በምሥራቅም በኩል ወርዱ አሥር ሺህ፥ በደቡብም በኩል ርዝመቱ ሃያ አምስት ሺህ ክንድ የሆነ ቦታ ይለይላቸዋል። የእግዚአብሔርም መቅደስ በመካከሉ ይሆናል።
11ይህም የእስራኤል ልጆች በሳቱ ጊዜ፥ ሌዋውያን እንደ ሳቱት ላልሳቱት ሥርዓቴንም ለጠበቁት ከሳዶቅ ልጆች ወገን ለተቀደሱት ካህናት ይሆናል።
12ለእነርሱም የሚሆነው መባ እስከ ሌዋውያን ድንበር የሚደርስ የዚህ የተቀደሰ ሥፍራ ክፍል ነው።
13የሌዋውያን መሬት በካህናቱም ድንበር አንጻር ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ወርዱም አሥር ሺህ የሆነ ዕጣ ይሆናል። የእነኚህ ኩታ ገጠም መሬቶች ጠቅላላ ርዝመት ሀያ አምስት ሺህ ወርዱም ሀያ ሺህ ክንድ ይሆናል።
14ለእግዚአብሔርም የተቀደሰ ነውና ከእርሱ ምንም አይሸጡም አይለውጡምም፥ የምድሩም በኵራት አይፋለስም።
15የቀረው ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ስፋትና አምስት ሺህ ክንድ ርዝመት ያለው ስፍራ ለከተማይቱ የጋራ ጉዳይ ፥ ለመኖሪያና ለማስማርያም ይሆናል ከተማይቱም በመካከሉ ትሆናለች።
16የከተማይቱም ልኬት ይህ ነው፡ በሰሜን በኩል አራት ሺህ አምስት መቶ፥ በደቡብም በኩል አራት ሺህ አምስት መቶ፥ በምሥራቅም በኩል አራት ሺህ አምስት መቶ፥ በምዕራብም በኩል አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ ይሆናል።
17ለከተማይቱም በሰሜን በኩል ሁለት መቶ አምሳ፥ በደቡብም በኩል ሁለት መቶ አምሳ፥ በምሥራቅም በኩል ሁለት መቶ አምሳ፥ በምዕራብም በኩል ሁለት መቶ አምሳ ክንድ ጥልቀት ያለው ማሰማርያ ይኖራታል።
18ቀሪው የተቀደሰው በተቀደሰው የመሬት መባ ርዝመቱ ወደ ምሥራቅ አሥር ሺህ ወደ ምዕራብም አሥር ሺህ ክንድ ይሆናል። ድንበሩም በተቀደሰው የመሬት የተያያዘ ይሆናል። ፍሬውም ከተማይቱን ለሚያገለግሉ ለመብል ይሆናል።
19ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ከተማይቱን የሚያገለግሉ ምድሪቱን ያርሱታል።
20መባው ሁሉ ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ወርዱም ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ይሆናል ። በዚህም መንገድ የተቀደሰውን የመሬት መባና የከተማይቱን ይዞታ ታደርጋላችሁ።
21በተቀደሰው መባና በከተማይቱ ይዞታ በዚህና በዚያ ወገን የቀረው ሥፍራ ለአለቃው ይሆናል። በምስራቅ በኩል ያለው የአለቃው ኩታ ገጠም መሬት ከተቀደሰው የመሬት መባ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ወደ ምሥራቁ ድንበር፥ በምዕራብም በኩል ደግሞ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ወደ ምዕራቡ ድንበር ይዘልቃል። የተቀደሰውም የመሬት መባውና የቤተ መቅደሱ የተቀደሰ ስፍራ በመካከል ይሆናል።
22የአለቃውም ይዞታው ከሌዋውያን ርስትና ክከተማይቱ ይዞታ መካከል ይሆናል፤ በይሁዳ ድንበርና በብንያም ድንበርም መካከል ይሆናል።
23ለቀሩትም ነገዶች ድርሻቸው ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ይሆናል። የብንያም ነገድ አንድ የዕጣ ክፍል ይቀበላል።
24ከብንያምም ደቡባዊ ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለስምዖን አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል።
25ከስምዖንም ደቡባዊ ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለይሳኮር አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል።
26ከይሳኮርም ደቡባዊ ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለዛብሎን አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል።
27ከዛብሎንም ደቡባዊ ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለጋድ አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል።
28ከጋድም ድንበር ቀጥሎ በደቡብ በኩል ድንበሩ ከታማር ጀምሮ እስከ ሜሪባ ቃዴስ ውኃ እስከ ግብጽ ወንዝ እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ይሆናል።
29ርስት አድርጋችሁ ለእስራኤል ነገዶች በዕጣ የምታካፍሉአት ምድር ይህች ናት፥ ይህም ርስታቸው ይሆናል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
30የከተማይቱም መውጫዎች እነዚህ ናቸው፡ በሰሜን ወገን ልኩ አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ ነው።
31የከተማይቱ በሮች ሦስት ሲሆኑ እንደ እስራኤል ነገዶች ስም በሰሜን በኩል አንዱ የሮቤል በር አንዱም የይሁዳ በር አንዱም የሌዊ በር ይሆናሉ።
32በምሥራቁም ወገን አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ በሚረዝመው ሥፍራ፥ ሦስትም በሮች አሉ፡ አንዱ የዮሴፍ በር አንዱም የብንያም በር አንዱም የዳን በር ይሆናሉ።
33በምስራቅ ወገን አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ በሚረዝመው ሥፍራ፥ ሦስት በሮች አሉ፡ አንዱ የስምዖን ፥አንዱ የይሳኮር፥ እና አንዱም የዛብሎን በር ናቸው።
34በምዕራቡም ወገን ልኬቱ አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ ሲሆን፥ በዚያ ሦስት በሮች አሉ፡ አንዱ የጋድ፥ አንዱም የአሴር፥ ሌላውም የንፍታሌም በር ናቸው።
35የከተማይቱ ዙሪያም አሥራ ስምንት ሺህ ክንድ ይሆናል፥ ከዚያም ቀን ጀምሮ የከተማይቱ ስም "እግዚአብሔር በዚያ አለ" ተብሎ ይጠራል።