1ከተራራው ሳይወርድ እንደ ዘገየ ሕዝቡ ሲመለከቱ፣ በአሮን ዙሪያ ተሰብስበው እንዲህ አሉት፤ “በፊታችን የሚሄድ ጣዖት ሥራልን። ከግብፅ ያወጣን ሙሴ ምን እንዳጋጠምው አናውቅም።”
2እንዲህ አላቸው፤ “በሚስቶቻችሁ ጆሮዎች፣ በወንድና በሴት ልጆቻችሁ ጆሮዎችም ላይ ያሉ የወርቅ ቀለበቶችን አውልቁና ወደ እኔ እምጧቸው።”
3ሁሉም በጆሮዎቻቸው ላይ ያሉ የወርቅ ቀለበቶችን አውልቀው ወደ አሮን አመጧቸው።
4ወርቁን ከእነርሱ ተቀብሎ በማቅለጥ ቅርጽ ሰጠው፤ የጥጃ ምስልም አደረገው። ሕዝቡም፣ “እስራኤል፣ ይህ ከግብፅ ምድር ያወጣህ አምላክህ ነው” አሉ።
5ይህን ባየው ጊዜ፣ በጥጃው ምስል ፊት መሠዊያ ሠራ፤ “ነገ ለእግዚአብሔር ክብር በዐል ይሆናል” ብሎም ዐወጀ።
6ሕዝቡ በማግስቱ ማልደው በመነሣት የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችንና የኅብረት መሥዋዕቶችን አቀረቡ። ሊበሉና ሊጠጡም ተቀመጡ፤ ለመዝፈንም ተነሡ።
7ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ከግብፅ ያወጣሃቸው ሕዝብህ ራሳቸውን በክለዋልና ቶሎ ሂድ።
8መንገድ ፈጥነው ወጥተዋል። ለራሳቸው የጥጃ ምስል ሠርተው ሰግደውለታል፤ መሥዋዕትም አቅርበውለታል። ‘እስራኤል፣ ከግብፅ ያወጣህ አምላክህ ይህ ነው ብለውም ተናግረዋል።’”
9እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ይህን ሕዝብ አይቼዋለሁ። ተመልከት፣ ዐንገተ ደንዳናዎች ናቸው።
10በእነርሱ ላይ እንዲቀጣጠልና እንዳጠፋቸው ተወኝ። ከአንተም ታላቅ ሕዝብ አደርጋለሁ (አንተንም ለታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ) ።”
11ግን አምላኩ እግዚአብሔር ዝም እንዲልለት ፈለገ፤ እንዲህም አለ፤ “እግዚአብሔር ሆይ፣ በታላቁ ኀይልና በኀያል እጅ ከግብፅ ባወጣሃው ሕዝብህ ላይ ቊጣህ ለምን ይቀጣጠላል?
12‘እግዚአብሔር በተራሮች ላይ ሊገድላቸውና ከገጸ ምድር ሊያጠፋቸው ዐስቦ ነው ያወጣቸው’ ለምን ይበሉ? ከሚነድደው ቊጣህ ተመለስ፤ በሕዝብህ ላይ ይህን ቊጣ ከማምጣትም ታገሥ።
13‘ዘራችሁን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛዋለሁ፣ የተናገርሁትን ይህንም ምድር ሁሉ ለዘራችሁ እሰጠዋለሁ፤ የዘለዓለም ርስታቸው ይሆናል’ ያልሃቸውንና በራስህ የማልህላቸውን ባሪያዎችህ አብርሃምን፣ ይስሐቅንና እስራኤልን ዐስብ።”
14ከዚያም እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ አመጣባቸዋለሁ ካለው ቊጣ ታገሠ።
15ተመለሰ፤ የምስክሩን ሁለት ጽላት በእጁ ይዞ ከተራራው ወረደ። ጽላቱ በሁለቱም ጎኖቻቸው፣ በፊትም በኋላም ተጽፎባቸው ነበር።
16የእግዚአብሔር ሥራ ነበር፤ በጽላቱ ላይ የተቀረጸው ጽሕፈትም የእግዚአብሔር ጽሕፈት ነበር።
17ላይ የተቀረጸው ጽሕፈትም የእግዚአብሔር ጽሕፈት ነበር። 17 ኢያሱ የሕዝቡን ጫጫታ ሲሰማ፣ ሙሴን፣ “በሰፈር ውስጥ የጦርነት ድምፅ አለ” አለው።
18ሙሴም “የድል አድራጊ ድምፅ አይደለም፤ ድል የተደረገ ሕዝብ ድምፅም አይደለም፤ የምሰማው የዘፈን ድምፅ ነው” ብሎ መለሰለት።
19ወደ ሰፈሩ ሲቀርብ፣ ጥጃውንና የሚጨፍረውን ሕዝብ አይቶ በጣም ተናደደ። ጽላቱን ከእጁ ወርውሮ በተራራው ግርጌ ሰበራቸው።
20ሠርተውት የነበረውን ጥጃም ወስዶ አቃጠለው፤ ዱቄት እስከሚሆን ድረስ በመፍጨትም በውሀ ውስጥ በተነው። ከዚያም የእስራኤል ሕዝብ እንዲጠጣው አደረገ።
21“እንደዚህ ያለ ታላቅ ኀጢአት ያመጣህበት ይህ ሕዝብ ምን አድርጎህ ነው?” አለው።
22እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ “ጌታዬ ሆይ ቊጣህ አይንደድ። እነዚህ ሰዎች ለክፋት የተዘጋጁ እንደ ሆኑ ታውቃለህ።
23እንደዚህ ብለውኛል፤ ‘በፊታችን የሚሄድ አምላክ አብጅልን። ከግብፅ ያወጣን ሰውየ ይህ ሙሴ ምን እንዳጋጠመው አናውቅም።’
24እኔም፣ ‘ወርቅ ያለው ሰው ሁሉ ያውልቀው’ አልኋቸው። እነርሱም ወርቁን ሰጡኝ። በእሳት ውስጥም ጣልሁትና ይህ ጥጃ ወጣ።”
25መዘባበቻ እንዲሆኑ አሮን መረን ስለ ለቀቃቸው፣ ሕዝቡ ከቊጥጥር ውጭ መሆናቸውን ሙሴ አስተዋለ።
26በሰፈሩ መግቢያ ቆሞ፣ “የእግዚአብሔር የሆነ ሁሉ ወደ እኔ ይምጣ” አለ። ሌዋውያን ሁሉ በሙሴ ዙሪያ ተሰበሰቡ።
27ሌዋውያኑን እንዲህ አላቸው፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል፦ ‘እያንዳንዱ ሰይፉን በወገቡ ይታጠቅና በሰፈሩ ሁሉ ከበር እስከ በር ወደ ኋላና ወደ ፊት እየተመላለሰ ወንድሙን፣ ጓደኛውንና ጎረቤቱን ይግደል።’”
28ሌዋውያኑ ሙሴ ያዘዘውን ፈጸሙ። በዚያ ቀን ከሕዝቡ ሦስት ሺሕ ያህል ሰዎች ሞቱ።
29ሌዋውያኑን፣ “ዛሬ ከእናንተ እያንዳንዱ በልጁና በወንድሙ ላይ እርምጃ ስለ ወሰደ፣ ለእግዚአብሔር አገልግሎት ተቀድሳችኋል። ስለዚህም እግዚአብሔር ዛሬ ባርኳችኋል” አላቸው።
30በማግስቱም ሙሴ ሕዝቡን፣ “ታላቅ ኀጢአት ሠርታችኋል። አሁን ወደ እግዚአብሔር እወጣለሁ። ምናልባት ለኀጢአታችሁ ማስተሰረያ ማድረግ እችል ይህናል” አላቸው።
31ሙሴ ወደ እግዚአብሔር ተመልሶ ሄደ፤ እንዲህም አለ፤ “ወዮ! እነዚህ ስዎች ታላቅ ኀጢአት ሠርተዋል፤ ለራሳቸውም ከወርቅ ጣዖት አበጅተዋል።
32ግን እባክህ ኀጢአታቸውን ይቅር በል፤ ይቅር የማትላቸው ከሆነ ግን ከጻፍኸው መጽሐፍ እኔን ደምስስልኝ።”
33ሙሴን እንዲህ አለው፤ እኔን የበደለኝን ሁሉ ከመጽሐፌ እደመስሰዋለሁ።
34ሂድ፤ ሕዝቡን ወደ ነገርኋችሁ ስፍራ ምራው። እነሆ፣ የእኔ መልአክ በፊትህ ይሄዳል። ሕዝቡን በምቀጣበት ቀን ግን ስለ ኀጢአታቸው እቀጣቸዋለሁ።”
35አሮን በሠራው ጥጃ ስላደረጉት፣ እግዚአብሔር በሕቡ ላይ መቅሠፍት ላከባቸው።