መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘጸአት 31

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤
2“የሖር የልጅ ልጅ የሆነውን የኡሪን ልጅ ባስልኤልን ከይሁዳ ነገድ በስሙ ጠርቼዋለሁ።
3ለሁሉም ዐይነት የእጅ ሞያ ጥበብን፣ ማስተዋልንንና ዕውቀትን እንዲሰጠው፣ ባስልኤልን በመንፈስ ሞልቼዋለሁ፤
4ይኸውም ጥበባዊ ሥራዎችን በወርቅ፣ በብርና በነሐስ እንዲሠራ፣
5ዐይነት የእጅ ሞያ ለማከናወንም ድንጋይ እንዲጠርብና ዕንጨትም እንዲቀርጽ ነው።
6ከእርሱም በተጨማሪ የአሂሳሚክን ልጅ ኤልያብን ከዳን ነገድ መርጬዋለሁ። ያዘዝሁህንም ሁሉ እንዲሠሩ የእጅ ሞያ ዐዋቂዎች በሆኑት ልብ ውስጥ ብልኀትን አስቀምጫለሁ።
7የመገናኛውን ድንኳን፣ የምስክሩን ታቦት፣ በታቦቱ ላይ ያለውን የስርየት መክደኛና የድንኳኑን ዕቃ ሁሉ፦
8ጠረጴዛውንና ዕቃውን፣ ንጹሑን መቅረዝ ከዕቃዎቹ ሁሉ ጋር፣ የዕጣኑን መሠዊያ:
9የሚቃጠለውን መሥዋዕት መሠዊያ ከዕቃዎቹ ሁሉ ጋርና ትልቁን ሰን ከነመቆሚያው የሚያካትት ይሆናል።
10የተሠሩትን ልብሶች፦ ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉኝ ለእኔ የተለዩትን የካህኑን የአሮንንና የልጆቹን የተቀደሱ ልብሶችም ይጨምራል።
11ዘይቱንና የመቅደሱን ጣፋጭ ዕጣንም ያካትታል። እነዚህ የእሥ ሞያ ዐዋቂዎች እነዚህን ሁሉ እኔ ባዘዝሁህ መሠረት ይሥሯችው።”
12ሙሴን እንዲህ አለው፤
13“ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘የእግዚአብሔርን የሰንበት ቀኖች ጠብቁ፤ እናንተን ለራሱ የለያችሁ እርሱ እግዚአብሔር መሆኑን እንድታውቁ፣ ይህ በእርሱና በእናንተ መካከል በትውልዶቻችሁ ሁሉ ምልክት ነውና።
14ስለዚህ ለእናንተ የተቀደሰ የእግዚአብሔር ሰንበት ነውና አክብሩት። ሰንበትን የሚያረክስ ሁሉ ይሞታል። በሰንበት የሚሠራም ከወገኑ ተነጥሎ ይጥፋ።
15ስድስት ቀን ይሠራል፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ክብር የተጠበቀና የተቀደሰ የፍጹም ዕረፍት ሰንበትን ያክብሩ።
16በትውልዶቻቸው ሁሉ ቋሚ ሕግ አድረገው ሰንበትን ሊያከብሩት ይገባል።
17እግዚአብሔር በስድስት ቀን ሰማይንና ምድርን ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ዐርፎአልና፣ ሰንበት በእግዚአብሔርና በእስራኤላውያን መካከል ሁልጊዜ ምልክት ይሆናል።”
18እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ ከሙሴ ጋር የሚያደርገውን ንግግር ከጨረሰ በኋላ፣ በገዛ እጁ የጻፈባቸውን የምስክሩን ሁለት የድጋይ ጽላት ለሙሴ ሰጠው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።