መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

አስቴር 10

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከዚያም ንጉሥ አርጤክስስ እስከ ባህር ጠረፍ ባለው ሀገር ላይ ግብር ጣለ።
2የኃይሉና የብርታቱ ሥራ ሁሉ፥ ንጉሡ ከፍ ከፍ ካደረገው ከመርዶክዮስ የታላቅነቱ ሙሉ ታሪክ ጋር በፋርስና በሜዶን ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ላይ ተጽፏል።
3አይሁዳዊው መርዶክዮስ ከንጉሥ አርጤክስስ ቀጥሎ በማዕረግ ሁለተኛ ነበር። የሕዝቡን ደኅንነት የፈለገና ስለ ሕዝቡም ሁሉ ሰላም የተናገረ፥ በብዙ አይሁድ ወንድሞቹም የታወቀና በአይሁድ መካከል ታላቅ የሆነ ሰው ነበር።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።