መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኤፌሶን 1

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በእግዚአብሔር ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ፥ ለእግዚአብሔር ለተለዩት በክርስቶስ ኢየሱስ ለሚያምኑ በኤፌሶን ለሚኖሩ ቅዱሳን፤
2ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
3በክርስቶስ ኢየሱስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባትና አምላክ ይባረክ።
4እግዚአብሔር በክርስቶስ የምናምነውን እኛን ዓለም ከመፈጠሩ በፊት መርጦናል። ይህም በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን እንሆን ዘንድ ነው
5እግዚአብሔር በፍቅር በኢየሱስ ክርስቶስ የራሱ ልጆች አድርጎ ሊቀበለን አስቀድሞ ወሰነን። ይህንንም የፈጸመው ሊያደርግ የፈለገውን ነገር ለማድረግ ደስ ስለተሰኘ ነበር።
6ይህ ሁሉ የተፈጸመው በሚወደው ልጁ እንዲያው በነጻ ስለ ተሰጠን ክቡር ጸጋው እግዚአብሔር ይመሰገን ዘንድ ነው።
7እንደ ጸጋው ባለጠግነት መጠን በሚወደው ልጁ ደም ቤዛነትን ይኸውም የሐጢአት ይቅርታን አገኘን።
8ይህም ጸጋ በጥበብና በማስተዋል ሁሉ ተትረፍርፎ ተሰጠን።
9በክርስቶስ በተገለጠው ፈቃዱ መሠረት እግዚአብሔር በዕቅዱ ውስጥ ያለውን የተሰወረውን እውነት እንድናውቅ አድርጎናል፤
10ዕቅዱን የሚፈጽምበት ጊዜ ሲድርስ በሰማይና በምድር ያሉትን ነገሮች ሁሉ በአንድ ላይ በክርስቶስ ስር ይጠቀልላል።
11ሁሉንም ነገር እንደ ገዛ ፈቃዱ በሚያደርገው ዕቅድ መሠረት በክርስቶስ ተመረጥን፤ አስቀድሞም ተወሰንን
12ይህም የሆነው በክርስቶስ በማመን ቀዳሚ የሆንነው እኛ ለክብሩ ምስጋና ይሆን ዘንድ እንድንኖር ነው።
13ባመናችሁበትና እንደ ተሰጠው ተስፋ በመንፈስ ቅዱስ በታተማችሁበት በክርስቶስ አማካይነት የመዳናችሁ ወንጌል የሆነውን የእውነት ቃል የሰማችሁት በክርስቶስ ነው
14ለክብሩ ምስጋና እንዲሆን ተስፋ የተደረገው ሀብት በእጅ እስገሚገባ ድረስ መንፈስ ቅዱስ የርስታችን ዋስትና የሚሆን መያዣ ነው።
15ስለዚህ በጌታ ኢየሱስ ስላላችሁ እምነትና ለእርሱም ቅዱሳን ሁሉ ስላላችሁ ፍቅር ከሰማሁበት ጊዜ አንስቶ
16ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ማመስገንና እናንተንም በጸሎቴ ማስታወስ አላቋረጥሁም ።
17የክብር አባት፥የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን ለማወቅ የሚያስችላችሁን የጥበብ እና የመገለጥ መንፈስ እንዲሰጣችሁ እጸልያለሁ፤
18የምጸልየውም የመጠራታችን አስተማማኝነት እና በእርሱ ቅዱሳን መካከል የርስቱ ክብር ባለጠግነት ምን እንደሆነ ታውቁ ዘንድ የልባችሁ ዐይኖች እንዲበሩ
19እንዲሁም እንደ ኀይሉ ብርታት አሠራር በእኛ በምናምነው ውስጥ የሚሠራው የኀይሉ ታላቅነት ምን እንደሆነ እንድትረዱ ነው።
20ይህም እግዚአብሔር ከሙታን ባስነሳውና በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ እንዲቀመጥ ባደረገው ጊዜ በክርስቶስ ውስጥ የታየው ኀይል ነው።
21ክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በአብ ቀኝ የተቀመጠውም ከማንኛውም ግዛት፥ ሥልጣን፥ኀይልና ጌትነት እንዲሁም በዚህ ዘመን ብቻ ሳይሆን በሚመጣውም ዘመን ቢሆን ሊሰየም ከሚችለው ስም ሁሉ በላይ ነው።
22እግዚአብሔር ሁሉም ነገር በክርስቶስ እግር ሥር እንዲገዛ አድርጓል፤ እርሱንም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሁሉም ነገር ላይ ራስ አድርጎ ሾሞታል
23ቤተ ክርስቲያንም ሁሉንም ነገር በሁሉም መንገድ የሚሞላው የእርሱ ሙላት የሆነች አካሉ ናት።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።