1በይሁዳ ንጉሥ በኢዮአቄም ዘመነ መንግሥት በሦሥተኛው ዓመት፥አቅርቦቶቿን ሁሉ ለማስቆም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፥ ከበባትም።
2ጌታም ለናቡከደነፆር በይሁዳ ንጉሥ በኢዮአቄም ላይ ድል ሰጠው፥እርሱም ከእግዚአብሔር ቤት የተቀድሱ ዕቃዎች ጥቂቱን ሰጠው። እርሱም ወደ ባቢሎን ምድር፥ ወደ አምላኩ ቤት አመጣቸው፥የተቀደሱትንም ዕቃዎች በአምላኩ ግምጃ ቤት ውስጥ አኖራቸው።
3ንጉሡም ዋና አለቃውን አስፋኔዝን፥ ከነገሥታቱና ከመሳፍንቱ ቤተስብ የሆኑትን፥ ከእስራኤል ሰዎች አንዳንዶችን፦
4ነውር የሌለባቸውን ወጣት ወንድች፥ መልከ መልካሞችን፥ ጥበበኞችን፥ በዕውቀትና በማስተዋል የተሞሉትንና በንጉሡ ቤት ለማገልገል ብቁዎች የሆኑትን እን ዲያመጣ ተናገረው። የባቢሎናውያንን ሥነ ጽሑፍና ቋንቋ እንዲያስተምራቸው ተናገረው።
5ንጉሡ ከምግቡና ከሚጠጣው ወይን በየዕለቱ ድርሻ መደበላቸው። እነዚህ ወጣት ወንዶች ለሦሥት ዓመት መሠልጠንና ከዚያ በኋላ ንጉሡን ማገልገል ይጠበቅባቸዋል።
6ከእነዚህም መካከል አንዳንድ የይሁዳ ሰዎች፥ ዳንኤል፥ አናንያ፥ ሚሳኤልና አዛሪያ ነበሩ።
7ዋና አለቃውም ስም አወጣላቸው፦ ዳንኤልን ብልጣሶር፥ አናንያን ሲድራቅ፥ ሚሳኤልን ሚሳቅ፥ አዛሪያንም አብድናጎ ብሎ ጠራቸው።
8ነገር ግን ዳንኤል በንጉሡ ምግብና በሚጠጣውም ወይን ራሱን እንዳያረክስ በውስጡ አሰበ። ራሱን እንዳያረክስ ከዋናው አለቃ ፈቃድ ጠየቀ።
9ዋና አለቃው ለእርሱ ባለው አክብሮት አማካይነት እግዚአብሔር ለዳንኤል ሞገስንና ጸጋን ሰጠው።
10ዋና አለቃውም ዳንኤልን አለው፥ «እኔ ጌታዬን ንጉሥን እፈራለሁ። ምን ዓይነት ምግብና መጥጥ ማግኘት እንዳለባችሁ አዞኛል። በእናንተ እድሜ ካሉ ወጣቶች ይልቅ ከስታችሁ ስለ ምን ይመለከታል? ንጉሡ ከእናንተ የተነሳ በሞት ይቀጣኝ ይሆናል።»
11ዳንኤልም ዋናው አለቃ በዳንኤል፥በአናንያ፥በሚሳኤልና በአዛሪያ ላይ ለሾመው መጋቢ ተናገረ።
12እርሱም አለ፥«እባክህ፥እኛን አገልጋዮችህን ለአሥር ቀናት ፈትነን። የምንመገብው ጥቂት አትክልትና የምንጠጣው ውኃ ብቻ ስጠን።
13ከዚያም የእኛን ፊት የንጉሡን ምግብ ከሚመገቡ ወጣቶች ጋር አስተያይ፥ባየኽውም መሠረት በአገልጋዮችህ ላይ አድርግ።»
14መጋቢውም ይህን ለማድረግ ከእርሱ ጋር ተስማማ፥ለአሥር ቀናትም ፈተናቸው።
15ከአሥርም ቀን በኋላ የንጉሡን መብል ከተመገቡ ወጣቶች ይልቅ ጤነኞችና የተሻለ የተመገቡ ሆነው ታዩ።
16ስለዚህ መጋቢው የተመደበላቸውን የተመረጠ ምግብና ወይን አስቀርቶ አትክልት ብቻ ሰጣቸው።
17ለእነዚህ አራት ወጣቶች፥ እግዚአብሔር በሁሉም ሥነ ጽሑፍና በጥበብ ዕውቀትና ማስተዋል ሰጣቸው፥ ዳንኤልም ሁሉንም ዐይነት ራዕይና ሕልም መረዳት ይችል ነበር።
18እንዲያስገቡአቸው ንጉሡ የመደበው ጊዜ እንዳበቃ፥ዋናው አለቃ በናቡከደነፆር ፊት አቀረባቸው።
19ንጉሡም ከእነርሱ ጋር ተነጋገረ፥አብረዋቸው ከነበሩት ሁሉ መካከል ከዳንኤል፥ሐናንያ፥ ሚሳኤልና አዛርያ ጋር የሚወዳድር ማንም አልነበረም። በንጉሡ ፊት ቆሙ፥ ሊያገለግሉት ዝግጁዎች ነበሩ።
20ንጉሡ በጠየቃቸው የጥበብና የማስተዋል ጥያቄዎች ሁሉ፥በግዛቱ ሁሉ ከሚገኙ አስማተኞችና ሙታን ሳቢዎች አሥር እጥፍ በልጠው ተገኙ።
21ዳንኤልም እስከ ንጉሥ ቂሮስ የመጀመሪያ ዓመት ድረስ እዚያው ነበረ።