መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ቆላስይስ 1

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በእግዚአብሔር ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስና ከወንድማችን ከጢሞቲዎስ፤
2በቆላስይስ ለሚኖሩ ለእግዚአብሔር ለተለዩና በክርስቶስ ታማኝ ለሆኑ አማኞች፤ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ጸጋና ሰላም ይሁንላችሁ።
3ለእናንተ በምንጸልይበት ጊዜ ሁሉ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔርን እናመሰግናለንን።
4በክርስቶስ ኢየሱስ ስላላችሁ እምነትና ለእግዚአብሔር ለተለዩት ሁሉ ስላላችሁ ፍቅር ሰምተናል።
5በሰማይ ከተጠበቀላችሁ ከመታመነ ተስፋ የተነሣ ይህ እምነትና ፍቅር አላችሁ። ስለዚህም ተስፋ በወንጌል የእውነት ቃል አስቀድማችሁ ሰማችሁ፤ ይህም ወደ እናንት ደርሶአል።
6ይህንም ወንጌል ከሰማችሁበትና የእግዚአብሔርን ጸጋ በእውነት ከተረዳችሁበት ቀን ጀምሮ በእናንተም ዘንድ እየሠራ እንዳለ ሁሉ በዓለም ዙሪያ ሁሉ ፍሬ እያፈራና እያደገ ነው።
7በእኛ ምትክ ለእናንተ የክርስቶስ ታማኝ አገልጋይ የሆነውና ከእኛም ጋር አብሮን ከሚያገለግል ከተወዳጁ ከኤጳፍራ ይህን ተምራችኋል።
8ደግሞም በእግዚአብሔር መንፈስ ያላችሁን ፍቅር ነግሮናል።
9ከዚህም ፍቅር የተነሣ ስለ እናንተ ከሰማንበት ቀን ጀምሮ ለእናንተ ከመጸለይ አላቋረጥንም። በፈቃዱ ዕውቀት፣ በጥበብ ሁሉና በመንፈሳዊ ማስተዋል እንድትሞሉ እንጸልይላችኋለን።
10ጌታን ደስ በሚያሰኝ መንገድ በሁሉም እንደሚገባ እንድትመላለሱ፤ በማናቸውንም መልካም ሥራ ፍሬ እንድታፈሩና በእግዚአብሔርም ዕውቀት እንድታድጉ እንጸልያለን።
11በሁሉም ነገር እንድትጽኑና ትእግሥት እንዲኖራችሁ ፣ከኅይሉ ክብር የተነሣም በሁሉ ብርታትና ጥንካሬ እንዲኖራችሁ እንጸልያለን።
12በብርሃን ከሚኖሩት አማኞች ጋር የርስቱ ተካፋይ እንድንሆን ላበቃን ለእግዚአብሔር በደስታ ምስጋና ማቅረብ እንድትችሉ እንጸልያለን።
13ከጨለማ ኅይል አዳነን፤ ወደ ተወደደውም ወደ ልጁ መንግሥት አሸጋገረን።
14በልጁም የኅጢአታችንን ይቅርታ፣ ድነትን አገኘን።
15ልጁ የማይታየው አምላክ ምሳሌ ነው። እርሱ የፍጥረት ሁሉ በኩር ነው።
16ምክንያቱም በሰማያትና በምድር፤ የሚታዩትና የማይታዩት ነገሮች ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋል። ዙፋናትም ሆኑ ኅይላት ወይም ግዛቶችች ወይም ሥልጣናት፤ሁሉም ነገር በእርሱና ለእርሱ ተፈጥረዋል።
17እርሱ ከሁሉ በፊት ነበረ፤ሁሉም ነገር የተያያዘው በእርሱ ነው።
18እርሱ አካሉ ለሆነችው ቤተ ክርስቲያን ራስ ነው። እርሱ የሁሉም መገኛና የሁሉም የመጀመሪያ፣ከሙታንም በኩር ነው።
19በመሆኑም በሁሉም ነገሮች መካከል የመጀመሪያ ነው። በእርሱ የእግዚአብሔር ሙላቱ ሁሉ እንዲኖርና እግዚአብሔር በልጁ በኩል ሁሉን ነገር
20ከራሱ ጋር ያስታርቅ ዘንድ ስለ ወደደ ነው። እግዚአብሔር ልጁ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደም በሰማያትም ሆነ በምድር ያሉትን ነገሮች ሁሉ አስታረቀ።
21እናንተም ቀድሞ ከእግዚአብሔር ርቃችሁ ነበር፤ በአሳባችሁና በክፉ ሥራችሁም ምክንያት ጠላቶች ነበራችሁ።
22አሁን ግን ቅዱሳንና ንጹሓን፤ ነቀፋም የሌለባችሁ አድርጎ በፊቱ ሊያቀርባችሁ በልጁ ሞት እግዚአብሔር ከራሱ ጋር አስታረቃችሁ። ይህም በእርሱ ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ በወንጌሉ ከተገኘው ተስፋ ሳትናወጡ
23በእምነት ጸንታችሁ እንድትኖሩ ነው። ይህም ወንጌል እናንተ የሰማችሁትና ከሰማይ በታች ላለ ፍጥረት ሁሉ ተሰብኮአል። እኔም ጳውሎስ አገልጋይ የሆንኩት ለዚህ ወንጌል ነው።
24አሁን ስለ እናንተ በምቀበለው መከራ ደስ ይለኛል። አካሉ ስለ ሆነችው ስለ ቤተ ክርስቲያንም ከክርስቶስ መከራ ከመካፈል የጎደለውን በሥጋዬ አሟላለሁ።
25የእግዚአብሔርን ቃል በሙሉ ለእናንተ እንድገልጥ ከእግዚአብሔር በተሰጠኝ ኅላፊነት ቃሉን ለመፈጸም የማገለግለው ይህችን ቤተ ክርስቲያን ነው።
26ይህም ባለፉት ዘመናትና ትውልዶች ከሰው ልጆች ተሰውሮ የቆየውና አሁን ግን እግዚአብሔር ለሚያምኑት ሁሉ የገለጠው ምስጢር ነው።
27እግዚአብሔርም በእናንተ መካከል ለአሕዛብ ሊገልጥላቸው የፈለገው የዚህ ምስጢር የክብር ብልጽግና ምን ያህል ታላቅ እንደሆነ ነው። ይህም ምሥጢር በተስፋ የምንጠባበቀው ክብር የሚገኝበት ክርስቶስ በእናንተ መካከል መሆኑ ነው።
28የምንሰብከው እርሱን ነው። እያንዳንዱን ሰው በክርስቶስ ፍጹም አድርገን ለማቅረብ ጥበብን ሁሉ በማስተማርና በመምክር ሰውን ሁሉ እንገስጻለን።
29በውስጤ በኅይል በሚሠራው መሠረት በብርቱ እየታገልኩ እደክማለሁ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።