መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

2 ጢሞቴዎስ 4

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በእግዚአብሔር ፊት፣ በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ ባለው በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት፣ በመገለጡና በመንግስቱ፣ አዝዝሃለሁ፣
2ቃሉን ስበክ ሲመችህም ሳይመችህም የተዘጋጀህ ሁን፡፡ እየታገስክና እያስተማርክ ዝለፍ፣ ገስጽ፣ ምከርም፡፡
3ሰዎች እውነተኛውን ትምህርት የማይታገሱበት ዘመን ይመጣል፣ ይልቁን፣ ለፍላጎታቸው የሚስማማቸውን የሚሰብኩአቸውን አስተማሪዎችን በዙሪያቸው ይሰበስባሉ፡፡ ይህም ጆሮቻቸውን የሚያሳክክላቸው ይሆናል፡፡
4ጆሮቻቸውን እውነትን ከመስማት ይመልሳሉ፣ ወደ ስህተትም ያዘነብላሉ፡፡
5አንተ ግን፣ በነገር ሁሉ የነቃህ ሁን፣ መከራን ተቀበል፣ የወንጌላዊነትን ሥራ አድርግ፣ አገልግሎትህንም ፈጽም፡፡
6እኔ እንደ መስዋዕት ልሰዋ ነው፡፡ የምሄድበትም ጊዜ ደርሶአል፡፡
7መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፣ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፣ እምነቱንም ጠብቄአለሁ፡፡
8የጽድቅም አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፣ ይህንንም ጻድቅ ፈራጅ፣ የሆነው ጌታ፣ በዚያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፣ ለእኔ ብቻ አይደለም፣ ነገር ግን መገለጡን ለሚወዱ ሁሉ ነው፡፡
9ወደ እኔ በቶሎ ልትመጣ ትጋ፣
10ዴማስ ትቶኛልና፣ ይህንንም ዓለም ወድዶ ወደ ተሰሎንቄ ሄዶአል፡፡ ቄርቂስ ወደ ገላትያ፣ ቲቶም ወደ ድልማጥያ ሄደዋል፡፡
11ሉቃስ ብቻ ከእኔ ጋር አለ፡፡ ማርቆስን ይዘኸው ና እርሱ በሥራው እጅግ ይጠቅመኛል፡፡
12ቲኪቆስን ወደ ኤፌሶን ልኬዋለሁ፡፡
13ስትመጣ በጢሮአዳ የተውኩትን ልብሴን፣ ይልቁንም በብራና የተጻፉትን መጻሕፍት ይዘህልኝ ና፡፡
14መዳብ አንጥረኛው አሌክሳንደር እጅግ ከፋብኝ፡፡ ጌታ ስለ ክፉ ሥራው ዋጋውን ይከፍለዋል፡፡
15አንተም ደግሞ ከእርሱ ተጠበቅ፣ ቃላችንን እጅግ ተቃውሞአልና፡፡
16በፊተኛው የፍርድ ቤት ክርክሬ ከአኔ ጋር ማንም አልቆመም፣ ነገር ግን ሁሉም ተዉኝ፡፡ ይህንንም አይቁጠርባቸው፡፡
17ነገር ግን፣ አሕዛብ ሁሉ እንዲሰሙት፣ የወንጌሉ ስብከት በእኔ እንዲፈጸም፣ ጌታ በአጠገቤ ቆሞ አበረታኝ፣ ከአንበሳም አፍ ዳንኩኝ፡፡
18ጌታ ከክፉ ሥራዎች ሁሉ አውጥቶኛል፣ ለሰማያዊውም መንግሥቱ ይጠብቀኛል፡፡ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፡፡ አሜን፡፡
19ለጵርስቅላና ለአቂላ ለሄኔሲፎሩ በተ ሰብ ሰላምታ አቅርብልኝ፡፡
20ኤርስጦስ በቆሮንቶስ ቀረ፣ ነገር ግን ጥሮፊሞስ ስለታመመ በሚሊጢን ተውኩት፡፡
21ከክረምት በፊት ልትመጣ ትጋ፡፡ ኤውግሎስና ጱዴስ፣ ሊኖስና ቅላውዲያም ወንድሞች ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡልሃል፡፡
22ጌታ ከመንፈስህ ጋር ይሁን፡፡ ጸጋ ከአንተ ጋር ይሁን፡፡ አሜን፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።