መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

2ኛ ሳሙኤል 8

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከዚህ በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን ወጋቸው ድልም አደረጋቸው፡፡ ስለዚህ ዳዊት ጋትና መንደሮችዋን ከፍልስጥኤማውያን ቁጥጥር ነጻ አወጣት፡፡
2ከዚያ በኋላም ዳዊት ሞዓባውያንን ድል አደረገ፤ በመሬት ላይ አጋድሞ በገመድ ለካቸው፤ በገመድ ከተለኩትም ሁለት እጅ ሲገድል፣ አንድ እጅ ግን በሕይወት ይተው ነበር፡፡ ስለዚህ ሞዓባውያን የዳዊት አገልጋዮች ሆኑ፣ ግብርም ገበሩለት፡፡
3ከዚህ በኋላ ደዊት በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ ያለውን ግዛቱን ለማስመለስ ይጓዝ በነበረበት ጊዜ የሱባን ንጉሥ የረአብን ልጅ አድርአዛርን ድል አደረገው፡፡
4ዳዊትም ከእርሱ ላይ 1700 ሠረገሎችና 20, 000 እግረኞች ማረከ፡፡ ለመቶ ሠረገሎች የሚሆኑትን አስቀርቶ ዳዊት የሠረገሎቹን ፈረሶች ሁሉ ቋንጃዎች ቆረጠ፡፡
5ከደማስቆ አራማውያን የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን ለመርዳት በመጡ ጊዜ ሃያ ሁለት ሺህ አራማውያን ሰዎችን ገደለ፡፡
6ከዚያም የደማስቆ ክፍል በሆነው በአራም የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ አራማውያንም ለእርሱ አገልጋዮች ሆነው ተገዙለት፣ ግብርም ገበሩለት፡፡ ዳዊት በሄደበት ሁሉ እግዚአብሔር ድልን ሰጠው፡፡
7የአድርአዛር አገልጋዮች ይዘዋቸው የነበሩትን የወርቅ ጋሻዎች ዳዊት ወሰዳቸው ወደ ኢየሩሳሌምም አመጣቸው፡፡
8ቤጣህና ቤሮታይ ከተባሉ ከአድርአዛር ከተሞችም ዳዊት እጅግ ብዙ ናስ ወሰደ፡፡
9የሐማት ንጉሥ ቶዑ ዳዊት መላውን የአድርአዛርን ሠራዊት ድል ማድረጉን በሰማ ጊዜ፣
10ዳዊት ከአድርአዛር ጋር ስለ ተዋጋና ድል ስላደረገው ደግሞም አድርአዛር ከቶዑ ጋር ተዋግቶ ስለ ነበረ፣ ቶዑ ልጁን ዮራምን ሰላምታ ይሰጠው ዘንድና ይባርከው ዘንድ ወደ ዳዊት ላከው፡፡ ዮራምም ከእርሱ ጋር የብር፣ የወርቅና የናስ ዕቃዎች ይዞ መጣ፡፡
11ንጉሥ ዳዊትም ድል ካደረጋቸው መንግሥታት ሁሉ ማለትም
12ከአራም፣ ከሞዓብ፣ የአሞን ሕዝብ፣ ከፍልስጥኤማውያን ከአማሌቅ እንዲሁም ከሱባ ንጉሥ ከረአብ ልጅ ከአድርአዛር ከበዘበዛቸው ዕቃዎችና ካገኛቸው ብርና ወርቅ ጋር እነዚህን ለእግዚአብሔር ቀደሰ፡፡
13ዳዊት የጨው ሸለቆ በተባለው ስፍራ ከአሥራ ስምንት ሺህ ሰዎቻቸው ጋር የነበሩትን አራማውያንን ድል አድርጎ ከተመለሰ በኋላ ስሙ ገነነ፡፡
14በመላው ኤዶም የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ ኤዶማውያን ሁሉ የዳዊት አገልጋዮች ሆኑ፤ እግዚአብሔርም ዳዊት በሄደበት ስፈራ ሁሉ ድልን ሰጠው፡፡
15ዳዊት በመላው እስራኤል ላይ ነገሠ፤ ሕዝቡንም ሁሉ በፍትሐዊነትና በጽድቅ አስተዳደረ፡፡
16የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ የሠራዊቱ አለቃ ሲሆን፣ የአሒሉድ ልጅ ኢዮሣፍጥም ታሪክ ጸሐፊ ነበረ፡፡
17የአኪጦብ ልጅ ሳዶቅና የአብያታር ልጅ አቢሜሌክ ካህናት ሲሆኑ፣ ሠራያ ጸሐፊ ነበር፡፡
18የዮዳሔ ልጅ በናያስ የከሊታውያንና የፈሊታውያን አለቃ ሲሆን፣ የዳዊት ወንዶች ልጆች ደግሞ የንጉሡ ተቀዳሚ አማካሪዎች ነበሩ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።