መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

2ኛ ጴጥሮስ 1

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ክርስቶስ አገልጋይና ሐዋርያ ከሆነው ስምዖን ጴጥሮስ፤ በአምላካችንና በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ አማካይነት የተቀበልነውን ዐይነት ክቡር እምነት ለተቀበሉት፤
2እግዚአብሔርንና ጌታችንን ኢየሱስን በማወቅ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።
3በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን እግዚአብሔርን በማወቅ እንድንኖር ለሕይወትና ለእውነተኛ መንፈሳዊነት የሚያስፈልገን ሁሉ በመለኮቱ ኀይል ተሰጥቶናል።
4በእነዚህ ነገሮች አማካይነት እጅግ የከበረና ታላቅ ተስፋ ሰጠን፤ ይህንም ያደረገው በክፉ ምኞቶች ሰበብ በዓለም ካለው ምግባረ ብልሹ ሕይወት አምልጣችሁ ከመለኮታዊ ባሕርይ ተካፋዮች እንድትሆኑ ነው።
5በዚህም ምክንያት፣ የሚከተሉትን ነገሮች ለመጨመር ትጉ፣ በእምነታችሁ ላይ ደግነትን፣ በደግነት ላይ ዕውቀትን፣
6በዕውቀት ላይ ራስን መግዛት፣ ራስን በመግዛት ላይ መጽናትን፣ በመጽናት ላይ እግዚአብሔርን መምሰልን፤
7እግዚአብሔርን በመምሰል ላይ ላይ ወንድማዊ መዋደድን፣ በወንድማዊ መዋደድ ላይ ፍቅርን ጨምሩ።
8እነዚህ ነገሮች በውስጣችሁ ቢኖሩና በውስጣችሁ ቢያድጉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በማወቅ ዳተኞችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጉአችኋል።
9እነዚህ ነገሮች የሌሉት ግን ዕውር ነው፤ በቅርብ ያለውን ብቻ ያያል፤ ከቀድሞው ኀጢአቱ መንጻቱንም ረስቶአል።
10ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፤ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ለማጽናት ትጉ፤ ይህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉም፤
11በዚህም ወደ ጌታችንና አዳኛችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘላለማዊ መንግሥት መግባት በሙላት ይሰጣችኋል።
12ስለዚህ ምንም እንኳ እነዚህን ነገሮች ብታውቋቸውና በያዛችሁት እውነት ብትጸኑም፣ ስለ እነዚህ ነገሮች ዘወትር እናንተን ከማሳሰብ ቸል አልልም።
13በዚህ ምድራዊ ድንኳን ውስጥ እስካለሁ ድረስ ስለ እነዚህ ነገሮች እናንተን ማሳሰብ ትክክል ነው ብዬ አስባለሁ፤
14ምክንያቱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ገለጠልኝ ይህን ምድራዊ ድንኳን ቶሎ ለቅቄ እንደምሄድ ዐውቃለሁ፤
15ከተለየኋችሁም በኋላ እነዚህን ነገሮች ዘወትር እንድታስቡ የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ።
16ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኀይልና ስለ ዳግም መምጣቱም በነገርናችሁ ጊዜ ግርማውን በዐይናችን አይተን መሰከርን እንጂ በብልሃት የተፈጠረውን ተረት ተከትለን አይደለም።
17«በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው» የሚል ድምፅ ከግርማዊው ክብር በመጣለት ጊዜ፣ ከእግዚአብሔር አብ ክብርንና ሞገስን ተቀብሎአል።
18ከእርሱ ጋር በተቀደሰው ተራራ ላይ በነበርንበት ጊዜ ይህን ከሰማይ የመጣውን ድምፅ ሰምተነዋል።
19ትንቢታዊው ቃል ይበልጥ ተረጋግጦልናል፤ ሌሊቱ እስኪነጋ ድረስ በጨለማ ስፍራ ለሚያበራ መብራት እንደምትጠንቀቁ፣ የንጋቱ ኮከብ በልባችሁ እስኪበራ ድረስ ለዚህ ቃል ብትጠነቀቁ መልካም ታደርጋላችሁ።
20ይህን በመጀመሪያ ዕወቁ፤ በቅዱሳት መጻሕፍት የሚገኘውን የትንቢት ቃል ማንም ሰው በራሱ መንገድ የሚተረጒመው አይደለም፤
21ምክንያቱም ትንቢት ከእግዚአብሔር የተላኩ ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው ተናገሩት እንጂ ከቶ በሰው ፈቃድ የመጣ አይደለም።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።