መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሁለተኛ ዜና 1

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የዳዊት ልጅ ሰለሞንም በመንግሥቱ በረታ፤ አምላኩም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበር፤ እጅግም ብርቱ ንጉሥ አደረገው።
2ሰለሞንም ለእስራኤል ሁሉ፥ ለሻለቆች፥ ለመቶ አለቆችም፥ ለዳኞችም፥ በመላው እስራኤልም ሁሉ ለነበሩ መሳፍንት ሁሉ፥ ለአባቶች ቤቶች አለቆች ተናገረ፤
3የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው የእግዚአብሔር መገናኛ ድንኳን በገባኦን ስለነበር ሰለሞንና ጉባኤው ሁሉ እዚያ ወደነበረው የአምልኮ ሥፍራ ሄዱ።
4ዳዊት ግን ለእግዚአብሔር ታቦት በኢየሩሳሌም ድንኳን ተክሎለት ስለነበር ከቂርያት ይዓሪም ወዳዘጋጀለት ሥፍራ አምጥቶት ነበር።
5በተጨማሪም በሆር ልጅ በኡሪ ልጅ በባስልኤል የተሠራው የናስ መሠዊያ በዚያ በእግዚአብሔር ማደሪያ ድንኳን ፊት ነበረ፤ ሰለሞንና ጉባኤውም ወደ እርሱ ሄዱ።
6ሰለሞንም በእግዚአብሔር ፊት በመገናኛው ድንኳን ዘንድ ወደነበረው ወደ ናሱ መሰዊያ ወጣ። በዚያም አንድ ሺህ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ።
7በዚያም ሌሊት እግዚአብሔር ለሰለሞን ተገልጦ ፦ እንድሰጥህ የምትፈልገውን ማንኛውንም ነገር ለምነኝ አለው።
8ሰለሞንም እግዚአብሔርን፦ ለአባቴ ለዳዊት ታላቅ የቃል ኪዳን ታማኝነት አሳይተሃል፤ እኔንም በእርሱ ምትክ ንጉሥ አድርገኸኛል፤
9አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፦ ቁጥራቸው እንደ ምድር ትቢያ በሆነው ሕዝብ ላይ አንግሠኸኛልና ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸው የተስፋ ቃል ይፈጸም።
10አሁንም እንደዚህ ቁጥራቸው በበዛ ሕዝብህ ላይ ሊፈርድ የሚችል ማንም ስለሌለ ይህንን ሕዝብ እመራ ዘንድ ጥበብና እውቀት ስጠኝ አለው፡፡
11እግዚአብሔርም ሰለሞንን፡- በልብህ የነበረው ይህ ስለነበር ባለጠግነትን፥ ሀብትን፥ ወይም ክብርን ወይም የሚጠሉህን ሰዎች ነፍስ ወይም ለራስህ ረጅም እድሜ ስላልጠየቅህ ነገር ግን ባነገሥሁህ በህዝቤ ላይ ለመፍረድ ትችል ዘንድ ለራስህ ጥበብንና እውቀትን ስለጠየቅህ
12አሁን ጥበብና እውቀት ተሰጥተውሃል፤ ከአንተ በፊት የነበሩት ከነበራቸው እና ከአንተም በኋላ የሚመጡት ከሚኖራቸው ከየትኛውም ነገሥታት ይበልጥ ባለጠግነት፥ ሀብት፥ ክብርም እሰጥሃለሁ አለው፡፡
13ስለሆነም በገባኦን ከመገናኛው ድንኳን ፊት ከነበረው ከኮረብታው መስገጃ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፡፡ እዚያም በእስራኤል ላይ ነገሠ፡፡
14ሰለሞን ሰረገሎችን እና ፈረሰኞችን ሰበሰበ፡፡ በሰረገሎች ከተማዎችና ከራሱ ከንጉሡ ጋር በኢየሩሳሌም ያኖራቸው አንድ ሺህ አራት መቶ ሰረገሎች እና አሥራ ሁለት ሺህም ፈረሰኞች ነበሩት፡፡
15ንጉሡም ብርና ወርቅ በኢየሩሳሌም እንደ ድንጋይ እንዲበዛ አደረገው፤ የዝግባም እንጨት በቆላ እንዳሉት የሾላ ዛፎች እንዲበዛ አደረገው፡፡
16ከግብጽና ከቀዌ ለሰለሞን ፈረሶችን ስለ ማስመጣት የእርሱ ነጋዴዎች በገንዘብ እየገዙ ያመጡአቸው ነበር፡፡
17ከግብጽ አንዱን ሰረገላ በስድስት መቶ ሰቅል ብር፥ አንዱን ፈረስ በመቶ ሃምሳ ሰቅል ብር ዋጋ ያስመጡ ነበር፡፡ ለኬጢያውያንና ለሶርያ ነገሥታትም ልከው ይሸጡአቸው ነበር፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።