መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

1 ተሰሎንቄ 1

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከጳውሎስ፣ ስልዋኖስና ጢሞቴዎስ በእግዚአብሔር አብና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላሉ ለተሰሎንቄ ቤተክርስቲያን፤ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን!
2በጸሎታቻን እያሳሰብን እግዚአብሔርን ሁልጊዜ ስለ ሁላችሁም እናመሰግናለን።
3በእምነት ስለምትሠሩት ሥራ፣ በፍቅር ስለምትደክሙት ድካምና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ባላችሁ ተስፋ በመታመን ስለመጽናታችሁ በእግዚአብሔር በአባታችን ፊት ሳናቋርጥ እናስታውሳችኋለን።
4በእግዚአብሔር የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ! መመረጣችሁን እናውቃለን፣
5ወንጌላችን በቃል ብቻ ወደ እናንተ አልመጣምና፥ ነገር ግን በኃይል፣ በመንፈስ ቅዱስና በብዙ መረዳትም እንጂ፥ ስለእናንተ ስንል በመካከላችሁ ደግሞ እንዴት እንደነበርን ታውቃላችሁ።
6በብዙ መከራ ውስጥ ቃሉን ከመንፈስ ቅዱስ ደስታ ጋር ስትቀበሉት እኛንና ጌታን የምትመስሉ ሆናችሁ፣
7በመቄዶንያ ሁሉና በአካይያ ላሉ ለሚያምኑት ምሳሌ ሆናችሁላቸዋል።
8የጌታ ቃል ከእናንተ ተነሥቶ በመቄዶንያና አካይያ ብቻ ሳይሆን ምንም መናገር እስከማያስፈልገን ድረስ በእግዚአብሔር ላይ ያላችሁ እምነት በሁሉ ሥፍራ ተወርቷል።
9እኛን በሚመለከት እንዴት ያለ አቀባበል እንዳደረጋችሁልን፣ ሕያውና እውነተኛ የሆነውን አምላክ ታገለግሉ ዘንድ ከጣዖታት እንዴት ወደ እግዚአብሔር ዘወር
10እንዳላችሁ፣ደግሞም ከሰማይ የሚመጣውን ልጁን፣ ያም ከሙታን ያስነሳውን፣ ሊመጣ ካለው ቁጣ የሚያድነንን ኢየሱስን እንደምትጠባበቁ እነርሱ ራሳቸው ይመሰክራሉ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።