መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

1ኛ ሳሙኤል 31

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ፍልስጥኤማውያን ከእስራኤል ጋር ተዋጉ። የእስራኤል ሰዎች ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፥ በጊልቦዓ ተራራ ላይም ተገድለው ወደቁ።
2ፍልስጥኤማውያንም ሳኦልንና ልጆቹን በቅርብ ርቀት ተከተሏቸው። ፍልስጥኤማውያንም ልጆቹን ዮናታንን፥ አሚናዳብንና ሜልኪሳን ገደሏቸው።
3ውጊያው በሳኦል ላይ በረታበት፥ ቀስተኞችም አገኙት። በእነርሱም ምክንያት በጽኑ ሕመም ላይ ነበር።
4ሳኦልም ጋሻ ጃግሬውን፥”ሰይፍህን ምዘዝና ውጋኝ። አለበለዚያ፥ እነዚህ ያልተገረዙ መጥተው ይሳለቁብኛል“ አለው።
5ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ስለነበረ እምቢ እለ። ስለዚህ ሳኦል የራሱን ሰይፍ ወስዶ በላዩ ላይ ወደቀበት። ጋሻ ጃግሬው ሳኦል መሞቱን ባየ ጊዜ እርሱም ደግሞ ሰይፉ ላይ ወድቆ አብሮት ሞተ።
6ስለዚህ ሳኦል፥ ሦስቱ ወንዶች ልጆቹና ጋሻ ጃግሬው ሞቱ፤ እነዚህ ሰዎች ሁሉ በአንድ ቀን ሞቱ።
7ከሸለቆው በወዲያኛው ወገን የነበሩትና ከዮርዳኖስ በላይ የነበሩት የእስራኤል ሰዎች፥ የእስራኤል ሰዎች መሸሻቸውን፥ ሳኦልና ልጆቹ መሞታቸውን ባዩ ጊዜ ከተሞቻቸውን ትተው ሸሹ፥ ፍልስጥኤማውያንም መጥተው ተቀመጡባቸው።
8በማግስቱ እንዲህ ሆነ፥ ፍልስጥኤማውያን የሞቱትን ሰዎች ትጥቅ ለመግፈፍ በመጡ ጊዜ ሳኦልና ሦስቱ ልጆቹ በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወድቀው አገኟቸው።
9እነርሱም ራሱን ቆረጡት፥ የጦር መሣሪያውንም ገፈፉት፥ ወደ ፍልስጥኤማውያን ምድር ሁሉ ለጣዖት መቅደሶቻቸውና ለሕዝቡ ወሬውን እንዲያደርሱ መልዕክተኞችን ላኩ።
10የጦር መሣሪያውን በአስታሮት መቅደስ ውስጥ አስቀመጡት፥ ሬሳውንም በቤትሳን ከተማ የግንብ አጥር ላይ አንጠለጠሉት።
11የኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች ፍልስጥኤማውያን በሳኦል ላይ ያደረጉትን በሰሙ ጊዜ
12ተዋጊ የሆኑ ሰዎች ሁሉ ተነሥተው ሌሊቱን ሁሉ ተጉዘው የሳኦልንና የልጆቹን ሬሳ ከአጥሩ ላይ ወሰዱ። ወደ ኢያቢስ ሄዱ፥ በዚያም አቃጠሏቸው።
13ከዚያም አጥንቶቻቸውን በመውሰድ በኢያቢስ ባለው የአጣጥ ዛፍ ሥር ቀበሯቸው፥ ሰባት ቀንም ጾሙ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።