1አሁን ደግሞ ለአማኞች የሚሰበሰበውን ገንዘብ በተመለከተ፣የገላትያ አብያተክርስቲያናትን እንዳዘዝሁት ሁሉ፣እናንተም እንደዚሁ አድርጉ።
2እኔ ስመጣ ገንዘብ ከመሰብሰብ፣ በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን፣እያንዳንዳችሁ እንደቻላችሁት መጠን የተወሰነ ገንዘብ አጠራቅሙ።
3ወደ እናንተ በደረስሁ ጊዜ በመረጣችሁት ሰው በኩል ከደብዳቤ ጋር መባችሁን ወደ እየሩሳሌም እልከዋለሁ።
4የእኔም መሄድ አስፈላጊ ከሆነ ከእኔ ጋር ይሄዳሉ።
5ነገር ግን ወደ መቄዶንያ መሄዴ ስለማይቀር፣ በመቄዶንያ በኩል ሳልፍ ወደ እናንተ እመጣለሁ። በምሄድበት ሁሉ ለጉዞዬ እንድትረዱኝ፣
6ምናልባትም ከእናንተ ጋር ልቆይና ክረምቱንም ከእናንተ ጋር ላሳልፍ እችላልሁ።
7አሁን ግን ጊዜው ስለሚያጥር ላያችሁ አላስብም። ጌታ ቢፈቅድና ብመጣ ግን ከእናንተ ጋር ረዘም ላለ ጊዜ ለመቆየት ተስፋ አደርጋልሁ።
8ግን በኤፌሶን እስከ በዓለ ኅምሳ ቀን ድረስ እቆያልሁ፣
9ሰፊ በር የተከፈተልኝ ቢሆንም ብዙ ተቃዋሚዎች አሉብኝ።
10ጢሞቴዎስ ልክ እንደ እኔ የጌታን ሥራ የሚሠራ ነውና ወደ እናንተ ሲመጣ፣ያለ አንዳች ስጋት ከእናንተ ጋር እንዲቀመጥ አድርጉ።
11ማንም አይናቀው። ወደ አኔ ሲመጣ በሰላም እንዲሄድም እርዱት። ምክንያቱም ከሌሎች ወንድሞች ጋር እንዲመጣ እጠብቃለሁ።
12አጵሎስን በተመለከተ፣ከወንድሞች ጋር በመሆን እንዲጎበኛችሁ አበረታትቼው ነበር። አሁን ለመምጣት አልወሰነም፣ይሁን እንጂ ዕድሉን ሲያገኝ ይመጣል።
13ተጠንቀቁ፣በእምነትም ጸንታችሁ ቁሙ፣ቆራጦች ሁኑ፣በርቱ።
14የምታደርጉት ሁሉ በፍቅር ይሁን።
15የእስጢፋኖስን ቤተሰቦች ታውቃላችሁ። እነርሱ በአካይያ የመጀመሪያ አማኞች እንደሆኑና አማኞችን ለማገልገል ራሳችውን እንደሰጡ ታውቃላችሁ። ወንድሞች እና እህቶች
16እንደዚህ ላሉ ሰዎች፣ በሥራ እየረዱንና አብረውን እየደከሙ ላሉ ሰዎች ሁሉ እንድትገዙ አሳስባችኋለሁ።
17በእስጢፋኖስ፣በፈርዶናጥስ፣ እና በአካይቆስ መምጣት ተደስቼአልሁ። የእናንተን በዚህ ያለመኖር ጉድለት ሞልተውልኛል።
18የእኔን እና የእናንተን መንፈስ አድሰዋል። እንዲህ ላሉ ሰዎችን እውቅና ስጧቸው።
19በእስያ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። አቂላና ጵርስቅላ፣ እንዲሁም በቤታቸው ያለችው ቤተክርስቲያን በጌታ ስም ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
20ወንድሞች እና እህቶች ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። በተቀደሰ አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተለዋወጡ።
21እኔ ጳውሎስ፣ ይህን በእጄ ጽፌአለሁ።
22ማንም ጌታን የማይወድ ቢኖር፣ የተረገመ ይሁን። ጌታ ሆይ ና!
23የጌታ የኢየሱስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።
24በክርስቶስ ኢየሱስ ፍቅሬ ከሁላችሁ ጋር ይሁን።