መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

1ኛ ቆሮንቶስ 1

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በእግዚአብሔር ፈቃድ ሐዋርያ ሊሆን በክርስቶስ ኢየሱስ የተጠራ ጳውሎስና ወንድማችን ሶስቴንስ በቆሮንቶስ ላለች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ለተቀደሱት።
2የእነርሱና የእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በየስፍራው ከሚጠሩት ሁሉ ጋር ቅዱሳን ለመሆን ለተጠሩት ደግሞ እንጽፍላቸዋለን።
3ከአባታችን ከእግዚአብሔር ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
4ክርስቶስ ኢየሱስ ከሰጣችሁ ከእግዚአብሔር ጸጋ የተነሳ ሁልጊዜ ስለእናንተ አምላኬን አመሰግናለሁ።
5በነገር ሁሉ፤በንግግርና በዕውቀት ሁሉ ባለጸጋ እንድትሆኑ አድርጎአችኋልና።
6ስለክርስቶስ የተሰጠው ምስክርነት በመካከላችሁ እውነት ሆኖ እንደጸና ሁሉ ባለጸጎች አድርጎአችኋል።
7ስለዚህ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ በጉጉት ስትጠባበቁ አንድም መንፈሳዊ ስጦታ አይጎድልባችሁም።
8እርሱ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ያለ ነቀፋ እንድትሆኑ እስከ ፍጻሜ ድረስ ያጸናችኋል።
9ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው።
10ስለዚህ ወንድሞችና እህቶች ሆይ፤ ሁላችሁም በአንድ አሳብ እንድትስማሙ እንጂ በመካከላችሁ መለያየት እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ድርስቶስ ስም አሳስባችኋለሁ። እንዲሁም በአንድ ልብና በአንድ ዓለማ የተባበራችሁ እንድትሆኑ አሳስባችኋለሁ።
11በመካከላችሁ መከፋፈል እንደተፈጠረ የቀሎዔ ቤተ ሰዎች አስታውቀውኛል።
12ይህን የምላችሁ፦ እያንዳንዳችሁ፦ "እኔ ከጳውሎስ ጋር ነኝ፥ ወይም ከአጵሎስ ጋር ነኝ፤ ወይም እኔ ከኬፋ ጋር ነኝ፤ ወይም እኔ ከክርቶስ ጋር ነኝ" ትላላችሁ።
13ለመሆኑ ክርስቶስ ተከፍሎአልን? ጳውሎስስ ስለ እናንተ ተሰቅሎአልን? ወይም የተጠመቃችሁት በጳውሎስስ ስም ነውን?
14ከቀርስጶስና ከጋይዮስ በቀር ማናችሁንም ስላላጠመቅሁ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።
15ስለዚህ ማናችሁም በእኔ ስም እንደተጠመቃችሁ ለመናገር አትችሉም። (የእስጢፋኖስን ቤተ ሰብ ደግሞ አጥምቄአለሁ።
16ከዚህ ውጪ ሌላ ማንን አጥምቄ እንደሆነ አላውቅም።)
17ክርስቶስ ወንጌልን እንድሰብክ እንጂ እንዳጥምቅ አላከኝም። በሰው ጥበብ እንድሰብክ አልላከኝም፤ እንዲሁም የክርስቶስ መስቀል ኃይሉ ከንቱ መሆን ስለሌለበት በሰው የንግግር ጥበብ አልሰብክም ።
18ስለመስቀሉ ያለው መልእክት ለሚጠፉት ሞኝነት፤ ነገር ግን ለምንድን ለእኛ የእግዚአብሔር ኃይል ነው።
19"የጥበበኖችን ጥበብ አጠፋለሁ፤ የአስተዋዮችንም ማስተዋል ከንቱ አደርጋለሁ" ተብሎ ተጽፎአልና።
20ጥበበኛ ሰው የት አለ? ፈላስፋስ የት አለ? የዚህ ዓለም መርማሪስ የት አለ? እግዚአብሔር የዚህን ዓለም ጥበብ ሞኝነት እንዲሆን አላደረገምን?
21ዓለም በጥበብዋ እግዚአብሔርን ስላላወቀች በስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖአል።
22አይሁድ ታዓምራትን ይፈልጋሉ፤ የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ።
23እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን። ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለግሪክ ሰዎችም ሞኝነት ነው።
24ነገር ግን እግዚአብሔር ለጠራቸው ለአይሁዶችም ሆነ ለግሪክ ሰዎች የእግዚአብሔር ኃይልና ጥበብ የሆነውን ክርስቶስን እንሰብካለን።
25ምክንያቱም የእግዚአብሔር ሞኝነት የሚመስለው ነገር ከሰዎች ጥበብ ይበልጣል፤ እንዲሁም የእግዚአብሔር ድካም የሚመስለው ነገር ከሰዎች ብርታት ይበልጣል።
26ወንድሞችና እህቶች ሆይ፤ በእናንተ ያለውን የእግዚአብሔርን ጥሪ ተመልከቱ። ብዙዎቻችሁ በሰው መስፈርት ጥበበኞች አልነበራችሁም። ብዙዎቻችሁ ኃያላን አልነበራችሁም፤ ብዙዎቻችሁም ከመሳፍንት አልነበራችሁም።
27ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን ያሳፍር ዘንድ የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ። ብርቱንም ነገር ለማሳፈር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ።
28ዓለም እንደ ከበረ ነገር የምትቆጥረውን ከንቱ ለማድረግ እግዚአብሔ የዓለምን ምናምንቴ ነገር መረጠ። የተናቀውንና ያልሆነውን ነገር መረጠ።
29ይህን ያደረገው ማንም ሰው በእግዚአብሔር ፊት ለመመካት ምክንያት እንዳይኖረው ነው።
30በክርስቶስ ኢየሱስ ለመሆን የበቃችሁት ከእግዚአብሔር ሥራ የተነሳ ነው፤ እርሱም ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበባችን፤ጽድቃችንና ቅድስናችን ቤዛችንም ሆኖአልና።
31እንግዲህ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ ፦"የሚመካ በጌታ ይመካ" ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።