መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘጸአት 1

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እያንዳንዳቸው ቤተ ሰባቸውን በመያዝ፣ ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገቡት የእስራኤል ልጆች ስሞች እነዚህ ናቸው፦
2ሮሜል፣ ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣
3ይሳኮር፣ ዛብሎን፣ ብንያም፣
4ዳን፣ ንፍታሌም፣ ጋድና አሴር።
5ከያዕቆብ ዘር የተገኙት ሰዎች ሰባ ነበር። ዮሴፍ ቀድሞውኑ በግብፅ ውስጥ ነበረ።
6ከጊዜ በኋላ ዮሴፍ፣ ወንድሞቹ ሁሉና ያ ትውልድ በሙሉ ሞቱ።
7ነገር ግን እስራኤላውያን እየተዋለዱ ሄዱ፤ ቊጥራቸውም እጅግ ጨምሮ በጣም ብርቱዎች ሆኑ፤ ምድሪቱንም ሞሏት።
8በግብፅ ስለ ዮሴፍ የማያውቅ ዐዲስ ንጉሥ ተነሣ።
9ለሕዝቡም እንደዚህ አለ፤ “እስራኤላውያንን ተመልከቷቸው፤ ከእኛ ይልቅ በቍጥር በዝተዋል፤ እጅግም በርትተዋል።
10በቍጥር እየበዙ እንዳይሄዱ፣ ጦርነት ቢነሣም ከጠላቶቻችን ጋር ዐብረው እንዳይወጉንና ምድሪቱ ጥለው እንዳይሄዱ ኑ በዘዴ እርምጃ እንውሰድባቸው።”
11በከባድ ሥራ የሚያስጨንቋቸው አሠሪ አለቆችን በላያቸው ሾሙ። እስራኤላውያን ለፈርዖን ፊቶምና ራምሴ የተባሉ የንብረት ማከማቻ ከተሞችን ሠሩ።
12ግን ግብፃውያን እስራኤላውያንን ባስጨነቋቸው ቊጥር፣ እስራኤላውያን በቊጥር እየበዙና በምድሪቱ እየተስፋፉ ሄዱ። ስለዚህ ግብፃውያን እስራኤላውያን መፍራት ጀመሩ።
13ግብፃውያን እስራኤላውያንን በጥብቅ እንዲሠሩ አደረጓቸው።
14በሸክላ ሥራና ጭቃ በማስቦካት፣ በዕርሻ ውስጥም ሁሉን ዐይነት ከባድ ሥራ በማሠራት አስመረሯቸው (ሕይወታቸውን መራራ አደረጉባቸው) ። የሚጠበቅባቸው ሥራ ሁሉ ከባድ ነበር።
15ከዚያም በኋላ የግብፅ ንጉሥ ሲፓራና ፉሐ የሚባሉ ዕብራውያት አዋላጆችን እንዲህ አላቸው፤
16“ዕብራውያት ሴቶችን በማማጫው ላይ ስታዋልዱ፣ በሚወልዱበት ጊዜ ተመልከቱ። ወንድ ከተወለደ ግደሉት፤ ሴት ከሆነች ግን በሕይወት ትኑር።”
17ነገር ግን አዋላጆቹ እግዚአብሔርን ፈሩ፣ ንጉሡ ያዘዛቸውንም አልፈጸኩም፤ ትእዛዙን በመፈጸም ፈንታ ሕፃናት ወንዶችን በሕይወት እንዲኖሩ አደረጉ።
18የግብፅ ንጉሥ አዋላጆቹን ጠርቶ፣ “ለምን ይህን አደረጋችሁ፣ ሕፃናት ወንዶችንስ ለምን አልገደላችኋቸውም?” አላቸው።
19አዋላጆቹም ለፈርዖን፣ “ዕብራውያት ሴቶች እንደ ግብፃውያት ሴቶች አይደሉም። እነርሱ ብርቱዎች ናቸው፣ የሚወልዱትም አዋላጅ ወደ እነርሱ ከመምጣቱ በፊት ነው” በማለት መለሱለት፥
20እግዚአብሔር እነዚህን አዋላጆች ጠበቃቸው። ሕዝቡ በቍጥር በዙ፣ እጅግ ብርቱዎችም ሆኑ።
21አዋላጆቹ እግዚአብሔርን ስለ ፈሩ፣ እግዚአብሔር ቤተ ሰቦችን ሰጣቸው።
22ፈርዖን፣ “የተወለደውን ወንድ ልጅ ሁሉ ወንዝ ውስጥ ጣሉ፣ ሴትን ልጅ ግን በሕይወት እንድትኖር ታደርጋላችሁ” በማለት ሕዝቡን ሁሉ አዘዘ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።